This page contains information about DC Office of Human Rights services for Amharic speakers.
የኤፕሪል (April) የቋንቋ የቋንቋ ተደራሽነት ወር ነው !
___________
-የኮሎምብያ ዲስትሪክት የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ የተመሠረተው አድልዎን ለማጥፋት፣ የእኩልነት መብትን ለማስፋፋትና የኮሎምብያ ዲስትሪክት ኗሪዎችንና ጎብኝዎችን ስብዓዊ መብቶች ለማስጠበቅ ነው። ኤጀንሲው አድልዎ ለደረሰባቸው ነፃ የሕግ አገልግሎት በመስጥት የዲ.ሲ. የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌን ጨምሮ የአካባቢውንና የፌደራል ሕጎችን ያስከብራል። በተጨማሪም የስብዓዊ መብቶች ቢሮ አድሎ የሚያደርሱ የአሠራር ዘዴዎችንና ፖሊሲዎችን ለይቶ ለማወቅና ለመመርመር በሚያስችል በዲሬክተሩ በኩል በሚደረጉ ምርመራዎች የዲስትሪክቱን የሰብዓዊ መብቶች ያስከብራል።
በራስ ቋንቋ አገልግሎት የማግኘት ፕሮግራም
የስብዓዊ መብቶች ቢሮ ውስን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ለሚናገሩ ወይም ምንም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ ላልሆኑ የዲስትሪክቱ ነዋሪዎች በዲስትሪክቱ የሚሰጡ መረጃዎችንና አገልግሎቶችን በእኩልነት እንዲያገኙ በሚያደርገው በራስ ቋንቋ አገልግሎት የማግኘት ፕሮግራም የታቀደበት ቢሮ ነው። በ2004 በራስ ቋንቋ አገልግሎት የማግኘት ድንጋጌ መሠረት የከተማው መጠነኛ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የመንግሥት አገልግሎቶች በሚያገኙበት ጊዜ የማስተርጎም ወይም የተተረጎሙ ሰነዶችን ማግኘት አለባቸው። በራስ ቋንቋ አገልግሎት የማግኘት ፕሮግራም ሠራተኞች ሕብረተስቡን በሰፊው ያስተምራሉ፣ ውስን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ለሚናገሩ ወይም ምንም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ ላልሆኑ ነዋሪዎች አገልግሎት የሚሰጡ ኤጀንሲዎችን በማስተማርና የቴክኒካል እርዳታ በመስጠት፣ እንዲሁም በየዓመቱ የዲስትሪክቱን አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ውጤታማ አገልግሎት መስጠት ይገመግማሉ። .
የከተማ አቀፍ ወጣቶችን የማንጓጠጥ መከላከያ ፕሮግራም
በሰኔ 2013 የተመሠረተው የከተማ አቀፍ ወጣቶችን የማንጓጠጥ መከላከያ ፕሮግራም ዓላማ የማንጓጠጥ ሁኔታዎችን ለመከላከል ዘዴዎችን በመፍጠር በመላው በከተማ ውስጥ የማንጓጠጥ ሁኔታዎችን ለመቀነስ ነው። ፕሮግራሙ ወጣቶችን የማንጓጠጥ ተከላካይ ግብረ ኃይል በሥራ ላይ ያዋለውን ምርጥ የአሠራር ዘዴዎች በሥራ ላይ መዋል ለማረጋገጥ ለወጣቶች አገልግሎት ከሚሰጡ የመንግሥት ድርጅቶች፣ ከዲስትሪክቱ ትምህርት ቤቶችና ከመንግሥት ዕርዳታ ከሚያገኙ ለወጣቶች አገልግሎት ከሚሰጡ ድርጅቶች ጋር ይሠራል። ምርጥ የአሠራር ዘዴዎቹ በጥር 2013 በታተመው በግብረ ኃይሉ የከተማ አቀፍ የማንጓጠጥ መከላከል ፖሊሲ ሞዴል ላይ ሰፍረዋል። የፕሮግራሙ ሠራተኞች ውጤታማ ትምህርቶችን ያቀነባብራሉ፣ ካሪኩለም የሚያዘጋጁ ተሳታፊዎችን ምክር ይሰጣሉ፣ እንዲሁም የማንጓጠጥ መከላከያ ለመስጠት የታቀዱ ውጥኖችን ይገመግማሉ።
የአድልዎ ወይም በራስ ቋንቋ አገልግሎት አለማግኘት አቤቱታ አቀራረብ
የሥራ፣ የመንግሥት መኖሪያ ቤቶች፣ የቤቶች ወይም የትምህርት መስጫ አቋሞች የአድልዎ መመዝገቢያ ቅፆችን ሞልቶ ለስብዓዊ መብቶች ቢሮ በማስገባት አቤቱታ ማቅረብ ይቻላል። በራስ ቋንቋ አገልግሎት አለማግኘት አቤቱታ ለማቅረብ በራስ ቋንቋ አገልግሎት አለማግኘት አቤቱታ ቅፆችን በመሙላት አቤቱታ ማቅረብ ይቻላል።
የመንግሥት መኖሪያ ቤቶች መጠይቅ (ኦንላይን) (በእትም)
የትምህርት ተቋሞች መጠይቅ (ኦንላይን) (በእትም)
በቋንቋ አገልግሎት አለማግኘት አቤቱታ ቅፅ (ኦንላይን) (በእትም)
23 በዲሲ ሰብዓዊ መብቶች አዋጅ ስር ጥበቃ የሚደረግላቸው ባህሪያት
የእርስዎ የ ቋንቋ ተደራሽነትን የተመለከቱ መብቶች
በኢንተርኔት ያልቀረቡ ጥያቄዎችን በአካል ወይም በፖስታ በሚከተለው አድራሻ መላክ ይቻላል፤
DC Office of Human Rights
441 4th Street NW, Suite 570N
Washington, DC 20010
ሰለ የዲ.ሲ የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ፣ በራስ ቋንቋ አገልግሎግት ማግኘት ፕሮግራም ወይም የከተማ አቀፍ ወጣቶችን የማንጓጠጥ መከላከያ ፕሮግራም ጥያቄ ካለዎት በስልክ ቁጥር (202) 727-4559 ይደውሉልን። ወደ ቢሮአችን ሲመጡ ወይም ከደወሉ የድርጅታችን ባልደረባ ከአስተርጓሚ ጋር ያገናኝዎታል።
ተጨማሪ የተተረጎሙ ጠቃሚ ሰነዶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፣