Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Amharic (አማርኛ)

This page contains information about DC Department of Human Resources services for Amharic speakers.


የድርጀቱ ስም:    የዲ.ሲ. የሰው ኃይል መምሪያ 

ተልዕኮ:    የዲ.ሲ. የሰው ኃይል መምሪያ (DCHR) ተልዕኮ የግለሰብና ድርጅታዊ አፈፃፀሞችን በማጎልበት የዲ.ሲ. መንግሥት የተለያየ በደንብ ብቁ የሆነ የሰው ኃይልን መሳብ፣ ማዳበርና ማቆየት ነው።  

ዋና ዋና ፕሮግራሞች/የመምሪያው ዝርዝር፡  DCHR የሚከተሉትን አሰተዳደራዊ መዋቅሮች ያካትታል፡ 

የዲሬክተሩ ቢሮ - የአመራር አስተዳደርና ምልመላን፣ የፖሊሲ መምሪያ፣ የስትራቴጂያዊና የገንዘብ ዕቅድ፣ የሕዝብ ግንኙነቶችን፣ የሀብት አስተዳደር፣ እንዲሁም የሰው ኃይልን በተመለከተ ለDCHR ድጋፍ እና ለከንቲባውና ለካቢኔው ምክር ይሰጣል።  የሥራ ክፍፍሎችን በመቆጣጠርና በማከፋፈል እንዲሁም የመምሪያውን ዓላማዎች በሥራ ላይ ለማዋል በማስተናበር የኤጀንሲው ግብና ዓላማዎች መሳካታቸውን ያረጋግጣል።   

ፖሊሲ እና የቅጥር አገልግሎቶች -  የዲስትሪክቱ የመንግሥት ሠራተኞች አስተዳደር ፕሮግራምን የሚመለከቱ መጠነ ሰፊ የሆኑ የህግ፣ የድንጋጌ እና የደንብ ሰንዶችን የማጥናት፣ የመመርመር፣ የማዋሃድ፣ የማሳደግና የማከፋፈል ኃላፊነት አለው።     

የስው ኃይል እድገት - የኮሎምብያ ዲስትሪክት ሠራተኞችን ዕውቀት፣ ችሎታንና ብቁነትን ለማሳደግና ከፍተኛና ጥራት ያላቸውን ብዙ ገንዘብ የማያስወጡ አገልግሎቶች እንዲሰጡ ሥልጠና፣ የሠራተኞች ዕቅድና ድርጅቶችን የሚያሳድጉ ፕሮግራሞችና እንቅስቃሴዎችን ያዘጋጃል።  አስተዳደሩ የሚከተሉትን ክፍሎች ያካተታል፡ የፕሮግራም ዕቅድና ተግባሮች፣ ልዩ ፕሮግራሞችና የሰው ኃይል ዕቅድ።        

ጥቅማጥቅሞችና ጡረታ  - ለጥቅማጥቅሞች በቂ ለሆኑ 32,000 ሠራተኞችና ጡረተኞች የዲስትሪክቱን የጥቅማጥቅሞች ፕሮግራምና ፖሊሲዎች አገልግሎት አሰጣጥ ኃላፊነት አለው።  ይህም የዕቅድ አስተዳደር፣ ኮንትራትና ሁሉንም የጤና፣ የበጎ ፈቃድና የጡረታ ፕሮግራሞችን ያጠቃልላል።   

የማካካሻ ክፍያና ድልድል - ለኮሎምብያ ዲስትሪክት የመንግሥት ድርጅቶች የሥራ ማዕረግ አስተዳደር፣ ድልድል፣ የማካካሻ ክፍያና የሥራ ዕቅድ አፈፃፀም ትብብርን ይሰጣል።  ይፋ የሆኑ ድልድሎችና መግለጫዎችን ይመሰርታል፣ የክፍያ ሰሌዳዎችን ነድፎ በሥራ ላይ ያውላል፣ የድልድል/ክፍያ/ የሥራ ዕቅድ አፈጻፀም ፖሊሲዎች፣ መመሪያዎችና ድንጋጌዎች ያዘጋጃል። ለዲስትሪክቱ የመንግሥት ድርጅቶች ድልድል፣ ሙሉ የማካካሻ ክፍያ፣ የክፍያ አሠራርን፣ የሜሪት ክፍያ፣ የክፍያና የድልድል ፖሊሲዎችን፣ የሥራ ዕቅድ አፈፃፀም ዘዴዎችን፣ FLSA እና የምልመላ/የማቆየትን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ሙያዊ ምክር ይሰጣል።  

የዋናው አማካሪ ቢሮ - የበታች ድርጅቶች ብቁ የሆነ የሠራተኞች ኃይል ለመሳብ፣ ለማዳበርና ለማቆየት እንዲችሉ ለሚያደርገው ለዲ.ሲ. የሰው ኃይል መምሪያ፣ የህግ እርዳታ ይሰጣል። የዋናው አማካሪ ቢሮ የዲ.ሲ. የሰው ኃይል መምሪያ ዓላማን ለማስፈፀም  ለዲሬክተሩና ለድርጅቱ አመራር፣ አስተዳዳሪዎች እና ሠራተኞች በተለያዩ የተወሳሰቡ ህግ ነክ ጉዳዮች የህግ ምክር ይሰጣል።,  

የፖሊስና የእሳት አደጋ የጡረታ እና እፎይታ ቦርድ -  የፖሊስና የእሳት አደጋ የጡረታና እፎይታ ቦርድ በሁሉም በጡረታና ከአደጋ በተረፉ ጥቅማጥቅም ጥያቄዎችና ጉዳዮች ላይ የመለየትና ውሳኔ የመስጠት ሥራ ይሠራል። ቦርዱ የዲ.ሲ. ፖሊስና የእሳት አደጋ መከላከል ክፍል፣ የዩ.ኤስ. ሴክሬት ሰርቪስ፣ ዪኒፎርምድ ክፍልን እና የዩ.ኤስ. ፓርክ ፖሊስ አባላትን በተመለከተ በእነኝህና መሰል የእፎይታ ጉዳዮች ላይ ቃል የመስማትና የአመራር ስብሰባዎችን ያከናውናል።   

አገልግሎቶች፡ የዲ.ሲ. የሰው ኃይል መምሪያ (DCHR) ለሠራተኞች የሚከተሉትን አገልግሎቶች ይሰጣል፡ 

  • ጥቅማጥቅሞች
  • ጡረታ
  • ድልድል
  • ፖሊሲ ማውጣትና ማስተዳደር
  • ለዲስትሪክቱ ነዋሪዎች የረዙሜ አጻጻፍና የሥራ ቃለመጠይቅ ክህሎቶችን ጨምሮ ነጻ ስልጠናዎችን ይሰጣል።                             

የማስተርጎም አገልግሎት፡ የዲ.ሲ. የሰው ኃይል መምሪያን በተመለከተ ጥያቄዎች ካሉዎት ቢሮአችንን በ(202) 442-9700 ደውለው ማናገር ይችላሉ። ወደ ቢሮአችን ሲደውሉ ወይም በአካል ሲመጡ የክፍላችን ሠራተኛ ለዕርዳታ በቀጥታ ካስተርጓሚ ጋር ያገናኝዎታል።

አድራሻ፡

DC Department of Human Resources
1015 Half Street, SE
9th Floor
Washington, DC 20003
Phone: (202) 442-9700