የዲሬክተር ማስታወሻ- ጁን (June) 2026
ፕራይድ ወር (Pride Month ) ወይም የኩራት ወር፤ የኤል ጂ ቢ ቲ ኪው + ( LGBTQ+) ማህበረሰብ የመቋቋም አቅም፣ የፈጠራ ችሎታና የተደረጉ አስተዋጽኦዎች የሚንጸባረቁበትና ኤል ጂ ቢ ቲ ኪው + ( LGBTQ+) ማህበረሰብን በተመለከተ የሚሰራው ስራ ው ገና እንዳልተጠናቀቀ ጎልቶ የሚያሳይ ክብረ በዓል ነው። የጁን ወር፤ እስከአሁን የተደረሰውን ዕድገት ለመረዳትና እያንዳንዱ ሰው የጾታ ዝንባሌው፤ የጾታ አመለካከቱና ማንነቱ ያም ሆነ ይህ፤ በስላም የሚኖርበት፣ የሚሰራበትና እውነተኛ ማንነቱን ጠብቆ ወደ ፊት ለመራመድ እንዳይችል የሚያደርጉ ገና ያልተወገዱ ጋሬጣዎችን ለይቶ ለማወቅ የሚችልበት ዕድል የሚሰጥ ነው።
በዲሲ ሰባዊ መብቶች ቢሮ (OHR) ውስጥ ፕራይድ(Pride) የተልእኮአችንን ዋና ቁምነገር ያንጸባርቃል። ይህም አድልዎን ማስወገድ እና የዲስትሪክቱ ነዋሪዎች፣ ሰራተኞች፣ ተማሪዎችና ጎብኚዎች እኩል ዕድል እንዲያገኙ ማድረግ ነው። በመላይቱ አገር ካሉት ሕጎች ውስጥ እጅግ ጠንካራ የሆነውን እ.ኤ.አ በ 1977 የጸደቀውን የዲሲ ሰብዓዊ መብቶች ሕግ (DC Human Rights Act) መሰረት በማድረግ፤ በመኖርያ ቤቶች፣ በህዝባዊ ተቋሞች፣ በመንግስት አገልግሎቶች እና በትምህርት አካባቢዎች፤ በጾታ ፤ በጾታ አመለካከትና በጾታ ማንነት ምክንያት አድልዎ እንዳይደረግ እንከላከላለን። በተጨማሪም እኤአ በ 2020 የተሻሻለው የኤል ጂ ቢ ቲ ኪው + ( LGBTQ+) አዛውንት እና በኤች አይ ቪ (HIV) የሚሰቃዩ ሰዎችን የሚንከባከብ ሕግ (Care for LGBTQ Seniors and Seniors with HIV Amendment Act) በስራ ላይ መተርጎሙንና የረጂም ግዜ እንክብካቤ ተቋሞች ስልጠናና እገዛ እንዲያገኙ በማድረግ በኩል የኤል ጂ ቢ ቲ ኪው+ (LGBTQ+) አዛውንትና የኤች አይ ቪ( (HIV) ታማሚዎች የሚያስፈልጋቸው ሁሉ እንዲጠናከሩ እንሰራለን።
እነኚህን የኤል ጂ ቢ ቲ ኪው( LGBTQ) ጉዳዮችን በተመለከተ ከከንቲባዋ ጽ /ቤት ጋር የምናደርገው ትብብር፤ ሁሉን አቀፍ የቋንቋ አገልግሎቶች በዲስትሪክቱ ውስጥ እንዲጠናከሩ አግዟል። በመሆኑም በመተባበር፤ እያንዳንዱ ግለሰብ የሚከበርበትና ከሌሎች ጋር የሚካተትበት የቋንቋ እገዛ ለማድረግ ትምህርታዊ ምንጮች እንዲጠናከሩ አድርገናል። ማህበረሰባችን በእድገት ጎዳና በሚጓዝበትና እውቀታችን ጥልቀት እያሳየ በሚሄድበት ወቅት ይህ እገዛ እያደገ ይመጣል።
በዚህ ወር ውስጥ፤ የኦ ኤች አር (OHR) የወጣቶች የትንኮሳ ማስወገጃ ፕሮግራም (Youth Bullying Prevention Program)፡ የኤል ጂ ቢ ቲ ኪው+(LGBTQ+)ማህበረሰብ ትንኮሳ ሲባል ምን እንደሚያጠቃልል በበለጠ እንዲረዳ፣ ትንኮሳ ሲያጋጥም መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎችና እርዳታ ካስፈለገ ከማን እርዳታ ማግኘት እንደሚቻል የሚያስረዳ፤ በኤል ጂ ቢ ቲ ኪው +(LGBTQ+)ማህበረሰብ ላይ የሚፈጸም ማንነትን ዒላማ የሚያደርግ ትንኮሳን ለማስወገድ የሚያስችል ቀላጣፋ መመርያ (When Bullying Targets Who You Are: A Quick Guide to Bullying Prevention for the LGBTQ+ Community) በሚል ርዕስ አዲስ አንቀጽ በማውጣት በዚህ መስክ የሚሰራውን ስራ ለማጠናክር ችሏል። ምንጩ በተጨማሪ፤ ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች፣ ትምህርት ቤቶች እና ወጣቶችን የሚያገለግሉ ፕሮግራሞች ምክርና ድጋፍ ለማግኘት ከ ኦ ኤች አር (OHR) የወጣቶች የትንኮሳ ማስወገጃ ፕሮግራም (Youth Bullying Prevention Program) ጋር እንዴት ግንኙነት መፍጠር እንደሚችሉ ያስረዳል።
ፕራይድ ወር (Pride Month) በዲሲ የሚገኙ የኤል ጂ ቢ ዪ ኪው+ (LGBTQ+) ተቀማጮች፣ ሰራተኞች፣ ተማሪዎችና ጎብኚዎች ሰለ አሏቸው መብቶችና ጥበቃዎች በበለጠ እውቀት እንዲያገኙ ዕድል የሚሰጥ ነው። ስለዚሁ ጉዳይ በበለጠ ለመረዳት OHR’s LGBTQIA+ Resource Portal ይጎብኙ።
ይህንን ፕራይድ ( Pride) በምናከብርበት ግዜም፤ ለእነኝያ የኤል ጂ ቢ ቲ ኪው+ ግለሰቦች እኩል ዕድል እንዲያገኙ ከፍተኛ ጥረት ላደረጉት ሃላፊዎቻችን፣ የማህበረሰቡ አባላትና የሰባዊ መብትተሟጋቾች ምስጋናችንና ከበሬታችንን ናቀርባለን። በጋራ በመሆን ማንኛውም ሰው በሕጉ መሰረት ፍትህና ከበሬታ በተመላበት ሁኔታ የሚስተናገድበት ዲስትሪክት ለመፍጠር የምናደርገውን ጥረት እንቀጥላለን።

