የዲሲ የሰብአዊ መብቶች ቢሮ(OHR) የኦገስት(August) ወርሃዊ የዜና መጽሄት- የዲሬክተር መልእክት
ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶችና ወዳጆች
ቀደም ሲል በዚህ ዓመት፤ የሰብዓዊ መብቶች ጽህፈት ቤት (OHR) አጠቃላይ አማካሪ በመሆን መስርያ ቤቱን የመቀላቀል ዕድል ማግኘቴን ማስታወቄ ይታወሳል። አሁን ደግሞ ጊዜያዊ ዲሬክተር በመሆን በ ከንቲባ ባውዘር (Mayor Bowser) በመመረጤ ከፍተኛ ኩራትና ደስታ ይሰማኛል። ቀደም ሲል የነበሩት ዲሬክተራችን ኬነት ሶንደርስ (Kenneth Saunders) ለረዥም ዓመታት የሚመሰገን የህዝብ አገልግሎት ከሰጡ በኋላ በቅርቡ ጡረታ ወጥተዋል። ኬነት ሶንደርስ በስራ ላይ በነበሩበት ዓመታት ብዛት ባላቸው የተለያዩ የስራ ዓይነቶች የተሳተፉ ሲሆኑ የሁሉም ሰዎች የእኩልነት መብት እንዲጠናከርና ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ በርካታ ጥረት አድርገዋል። በእሳቸው የ አመራር ዘመን ኦ-ኤች-አር (OHR) የስራ አፈጻጸም ጥረቶቹን እንዲያጠናክር፤ አሰራሮቹን እንዲያመቻችና እንዲያስተካክል እንዲሁም የተለያዩ ማራኪ የሆኑ ፕሮግራሞችን በማቅረብ የማህበረሰብ ተሳትፎ እንዲጨምር አድርገዋል።
ምንም እንኳን የዲሬክተር ሶንደርስን አመራርንና ቁርጠኛነትን የምንናፍቅ ብንሆንም፤እኛ ለኦ-ኤች-አር (OHR) ተልእኮ ያለንን የተባበረ የስራ ተነሳሽነትና ቁርጠኛነታችንን በድጋሚ ማረጋገጥ እወዳለሁ።
በጋራ በመሆን ኦ-ኤች-አር (OHR) በዲስትሪክቱ ውስጥ ሰብዓዊ መብቶች በስራ የሚተረጎሙበትን መንገዶች አጠናክረን እንቀጥላለን፤ ለሁሉም ተደራሽ የሆነ የትምህርት አገልግሎት እናጠናክራለን፣ ንቁ የሆነ የህዝብ ተሳትፎ እንዲኖር እናደርጋለን፣ ህዝቡ የደረሰበትን ደረጃ ተረድተን ድምጹን ለመስማት ቁርጠኛነታችን እንገልጻለን።
ከእስር ለተለቀቁ ዜጎች ጠቃሚ የሃብቶች ምንጮችን የማግኛ ፖርታል (Returning Citizens Resource Portal)
ባለን የሃብቶች ምንጮችን የማግኛ ፖርታል ላይ በተጨማሪ በቅርቡ ያደርግነው ይህ አገልግሎት እነኚህ ከእስር የተለቀቁ ዜጎችን ለመርዳት የምናደርገውን ቁርጠኛነት የሚያሳይ ነው። ይህ የሃብቶች ምንጭ የማግኛ አገልግሎት በዲስትሪክቱ ቀደም ብለው በእስር የነበሩት ዜጎች ከህብረተሰብ ጋር የሚቀላቀሉበትን መንገድ የሚያሳይና ይህ የሽግግር ጉዞአቸው ቀላልና ሊኖሩ የሚችሉ እክሎች እንዲቃለሉ የሚያግዝ ነው። ቀደም ሲል የነበረውን የመኖርያ ቤቶችንና የኤል-ጂ-ቢ-ዪ-ኪው-አይ-ኤousingLGBTQIA+resources. ጉዳይ የሚያጠናክር ነው።
ዲስትሪክቱ፤ ለአዲስ የትምህርት ዘመን በመዘጋጀት ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት፤ ኦ-ኤች-አር(OHR)ም በበኩሉ ተማሪዎችንና ቤተሰቦችን የማገዝ ድርሻውን እየተወጣ ነው። አዲስ የወጣት ጉልበተኛነትን ለማስወገድ የሚደረግ የአቤቱታ የማቅረቢያ ጥያቄና መልስ ፎርም (Youth Bullying Prevention Act Complaint Questionnaire) በማዘጋጀትና ስራ ላይ በማዋል ላይ ይገኛል። ይህም በትምህርት ቤቶች ውስጥ ያለውን ከጉልበተኛነት ጋር የተገናኘ ጥያቄ ወይም ቅሬታ በእንዴት ዓይነት ሁኔታ በበለጠና በተሻለ መመከት እንዲሚቻል የሚያሳይና በመንግስት የገንዘብ እገዛር ወጣቶችን የሚያገለግሉ ተቋማትን ለማቋቋም የሚያስችል ነው። ይህ አዲሱ ዘዴ ጉልበተኛነት ምን ያህል በከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጠው እንደሚታይና በሚያጋጥምበት ወቅት ተገቢው መልስ እንዴት እንደሚሰጠው ያመለክታል።
እስከአሁን ድረስ እየተከናወነ ባለው አንገብጋቢ ስራ በጣም ተነቃቅቻለሁ፣ ወደፊት በሚደረግ ተነሳሽነትም ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል። በመሆኑም ከእኛ ጋር ግንኙነት እንድተፈጥሩ እጋብዛለሁ፤ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ለማወቅ በህዝብ የዜና ማሰራጫዎች ተከታተሉን፣ ለህዝብ በምናቀርባቸው ስብሰባዎች በመገኘት ሃሳብዎንና አስተያየቶን ያካፍሉን ወይም በመንግስት የስራ ሰአት በስራ ሰዓቶች ወደ መስርያ ቤታችን በአካል በመምጣት ከእኛ ጋር ይወያዩ። ይህ ሁሉ መረጃ በዚሁ የዜና መጽሄት ላይ ይገኛል። የምናደርገው ማንኛውም ተጽእኖ የሚጠናከረው ከእርሶና ከምናገለግለው ህዝብ ጋር በአጋርነት ተባብረን ስንሰራ ብቻ ነው።
በህብረት፣
ኤሊዛቤት ፎክስ-ሰለሞን (Elizabeth Fox-Solomon )
ዋና ዲሬክተር