የዲሲ የሰባዊ መብቶች ቢሮ(OHR) ዜና መጽሔት - ልዩ የበዓል ህትመት
ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እንዲሁም ወዳጆች፦
ዓመቱ ወደ መጠናቀቅ ሲቃረብ ማህበረሰባችንን እና ተልእኳችንን የሚያንፀባርቁትን ፅናት፣ ርህራሄ እና ድፍረት በጥልቅ ምስጋና እያሰላሰልኩ አገኛለሁ። በ2025 የሰባዊ መብቶች ቢሮ(OHR) በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ውስጥ ለሚገኙ ሁሉም ነዋሪዎች የሲቪል እና ሰብአዊ መብቶችን ለመጠበቅ እና ለማስፋፋት ከነዋሪዎች፣ ተሟጋቾች እና አጋሮች ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ መስራቱን ቀጥሏል።
በዚህ ዓመት የቋንቋ ተደራሽነትን በማሳደግ ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ጥበቃን በማጠናከር፣ እና እያንዳንዱ ነዋሪ መብቶቹን እንዲያውቅ እና መብቶቹን ለመጠቀም አቅም እንዳለው እንዲሰማው ለማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራችንን በማስፋፋት ረገድ ትርጉም ያላቸው እመርታዎችን አድርገናል። እነዚህ ስኬቶች የኛ ብቻ አይደሉም - በከተማችን ውስጥ ለፍትህ የቆሙ ወገኖች ትጋት የተሞላበት ቅስቀሳ፣ ጽኑ ቁርጠኝነት እና የጋራ ጥረት ውጤቶች ናቸው።
መጪውን 2026 ዓ/ ም ስናስብ እድሎች በዘር፣ በጾታ፣ በአካል ጉዳት ወይም በማንኛውም ሌላ ማንነት የማይገደቡባት፣ የበለጠ አካታች ከተማ ለመገንባት ቃላችንን እናድሳለን። ስራው ይቀጥላል፣ ከእናንተ ጋር አብረን በመስራታችን ክብር ይሰማናል።
ያንን ቁርጠኝነት በማንፀባረቅ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ዓመታዊውን የሰብአዊ መብቶች የሽልማት ሥነ-ስርዓት በማዘጋጀታችን ኩራት ተሰምቶናል - ይህ በዲሲ የሰብአዊ መብቶች ሕግ ውስጥ የሰፈሩትን እሴቶች በተግባር ለሚያሳዩ አካላት የተደረገ የሽልማት ፕሮግራም ነው። የዘንድሮው መሪ ቃል “በዲስትሪክቱ ውስጥ ለሴቶች እና ለሕጻናት የሚደረገውን ተሟጋችነት ማስቀጠል” ስራቸው የሴቶችን እና የሕጻናትን መብቶች እና ደህንነት በጎላ ሁኔታ ያራመዱ ድርጅቶችን እና ግለሰቦችን እውቅና አሰጣጣችንን ቀርጾታል።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ ለሟቹ የተከበሩ ዋና የአስተዳደራዊ ሕግ ዳኛ Pierson መታሰቢያ የተሰየመውን የመክፈቻውን የErika L. Pierson Award/ ሽልማት/ ለወጣቶች ፍትህ እና ለሴቶች መብት ታታሪ ተሟጋች ለሆነችው ለBrittany Mobley አበርክተናል። Fatima Goss Graves በስነ ጾታ እኩልነት እና በሲቪል መብቶች ላይ ላሳየችው ሀገር አቀፍ አመራር Cornelius R. “Neil” Alexander Humanitarian Award ተቀብላለች። በተጨማሪም በOHR የወጣቶች ሰብአዊ መብቶች አምባሳደር ፕሮግራም አማካኝነት እኩዮቻቸው የሲቪል መብት ጥበቃዎችን በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ እና እንዲያገኙ የሚያግዙ ግብዓቶችን ያዘጋጁትን ሶስት አበረታች የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች — Verenize Tejada-Flores፣ Mecca Bey፣ እና Maia Burkhardt — አበረታተናል። በመጨረሻም የዋሽንግተን ዲሲ ዞንታ ክለብ በቅስቀሳ እና በትምህርት የሴቶችን እና የልጃገረዶችን መብቶች ለማራመድ ላሳየው የአንድ ክፍለ ዘመን ቁርጠኝነት የማህበረሰብ አገልግሎት ሽልማት ተሸልሟል። እነዚህ ተሸላሚዎች ሰብአዊ መብቶች የሚጠበቁት በፖሊሲ ብቻ ሳይሆን በዕለት ተዕለት የጀግንነት፣ የርህራሄ እና የአመራር ተግባራት ጭምር እንደሆነ ያስታውሱናል። ዓመቱን በምስጋና ስንዘጋ እና ወደፊት በተስፋ ስንመለከት ስራቸው ያነሳሳናል።
ይህ የበዓል ወቅት የሰላም፣ የጥሞና እና የተስፋ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። በሰብአዊ መብቶች ቢሮ ባለነው በሁላችንም ስም ስለ አብሮነታችሁ እና ለተሻለ ነገ ስላላችሁ እምነት ከልብ እናመሰግናለን!
በአጋርነት፣
ኤሊዛቤት ፎኽስ ሶሎሞን
Elizabeth Fox-Solomon

