የዲሲ ሰብአዊ መብቶች ቢሮ (OHR) የሜይ ወር(MAY ) ዜና መጽሄት (Newsletter) – የዳይሬክተሩ መልእክት
ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እና ወዳጆች፡-
ኤፕሪል ለዲሲ የሰብአዊ መብቶች ቢሮ (OHR) ስራ የበዛበት ወር ነበር፤ ምክንያቱም በዲስትሪክቱ ውስጥ ላሉ ነዋሪዎች ሁሉ የእኩል ተጠቃሚነት እና የመኖሪያ ቤት መብቶችን ለማረጋገጥ ያለንን ቁርጠኝነት ያስማሰከርንባቸው ሁለት ጉልህ ክስተቶች ማለትም የዲሲ የቋንቋ ግንዛቤ ወር እና ፍትሃዊ የቤት ወርን ማክበር መቻላችን ነው። ወደ ሜይ ወር ስንገባ የተለያዩ ማህበረሰቦቻችንን ከፍ ለማድረግ እና ለማክበር ባለን ቁርጠኝነት እና የሲቪል መብቶች ለሁሉም የማዳረስ ተልእኳችን ላይ በጽናት እንደቆምን ነው።
በዚህ ወር፣ በከተማችን እና በዙሪያው የሚኖሩ የ AANHPI ማህበረሰቦች አስደናቂ አስተዋጾ ላይ ትኩረት በማድረግ የእስያ አሜሪካዊ፣ የሃዋይ ተወላጅ እና የፓሲፊክ ደሴት (AANHPI) ታሪክ ወርን ለማክበር ተዘጋጅተናል። እነዚህ 6% የሚሆነውን የዲስትሪክቱን ህዝብ የሚወክሉ ማህበረሰቦች ለከተማችን የዳበረ የባህል፣ የቋንቋ እና የታሪክ ግብአት መጨመር ጉልህ አስትዋጾ አላቸው። የእነሱ ጽናት፣ አመራር እና ቆራጥነት በዕለት ተዕለት ህይወታችን ውስጥ አዎንታዊ ተጽኖ መማምጣት ከተማችንን አበልጽጎታል።
የሜይ ወር የአእምሮ ደህንነትን አስፈላጊነት እና የፍሃዊ አገልግሎት ተደራሽነት ግንዛቤን ለማያሳደግ የሚሰራበት የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ማስጨበጫ ወርም ነው። የሲቪል መብቶች ተሟጋቾች እንደመሆናችን፣ የአእምሮ ጤና ጉዳዮች የስራ ስምሪት መድልዎ እና ወሳኝ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያግዱ እንቅፋት ጨምሮ ከተለያዩ መድልዎ ዓይነቶች ጋር የተገናኙ እንደሆኑ እንገነዘባለን።
በOHR ውስጥ እያንዳንዱ ድምጽ እንዲሰማ እና ዋጋ እንዲሰጠው በማስቻል ከማህበረሰባችን ጋር ላለን ቀጥተኛ ግንኙነትን ቅድሚያ ትኩረት ሰጥተን እንሰራልን፤ ይህንን ታሳቢ በማድረግ በዎርድ 6 እና 7 ውስጥ ካሉ ነዋሪዎች ጋር በስትራተጂ እቅድ መርሃ ግብራችን ላይ ያላቸውን ግንዛቤ እና አስተያየት ለመሰብሰብ ተገናኝተን ነበር። ይህ የስትራተጂ እቅድ ተደራሽነትን፣ አፈጻጸምን እና የማህበረሰብ ተሳትፎን ለማሻሻል ያለንን ግቦች ይዘረዝራል። ይህንን እቅድ በመቅረጽ ረገድ የእርስዎ ተሳትፎና ግብአት ወሳኝ ነው። እነዚህ ውይይቶች ቅድሚያ የምንሰጣቸውን ነገሮች ለመወሰን እና ተደራሽነታችንን እንድናሳድግ ረድተውናል።
በቀጣይም የዋርድ 8 ነዋሪዎችን እና ሰፊውን የዲሲ ማህበረሰብ በሜይ 29 በአናኮስቲያ ቤተ መፃህፍት የሚቀርበውን ቀጣዩን የስትራተጂ እቅድ የማዳመጥ ዝግጅታችን የእንዲገኙና በመገኘት በንቃት እንዲሳተፉ በአክብሮት ጋብዘንዎታል። የእርስዎ ሃሳቦች እና አስተያየቶች የወደፊት ስትራተጂዎቻችንን በመቅረጽ ረገድ ወስኝ ሚና ይኖራቸዋል፣ ይህም የስትራራተጂ እቅዳችን የበለጠ ተደራሽ እና ውጠታማ ያደርገዋል።
ስለቀጣይ ዝግጅቶቻችን የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድህረ ገጻችንን ወይም ማህበራዊ ሚዲያን በየጊዜው እንድትመለከቱ አበረታታለሁ። እነዚህ መድረኮች በአዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች የዘመኑ ናቸው ፤ በተጨማሪም ከርስዎ ለመስማት በጉጉት እንጠባበቃለን!
ከአብሮነት ጋር፣
ኬኔት ሳውንደርስ