የ ዲሲ ሰባዊ መብቶች ቢሮ (OHR) የሴፕቴምበር ወር ዜናመጽሄት – የዳይሬክተር መልእክት
ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እና ወዳጆች፦
ሴፕቴምበር ለእኛ አስደሳች እና ስራ የሚበዛበት ወር ነው፤ ይህም የበጀት አመትን ዘግተን የሰራንውን ወደምንሰበስብበት ወቅት ልንገባ ነው። በመሆኑም ደስ ብሎን እውቅና ከምንሰጣቸው በአላት ውስጥ አንደኛው ብሔራዊ የሂስፓኒክ ቅርስ ወር ነው! በፕሬዝዳንት ሊንደን ጆንሰን በ1968 የተጀመረው ይህ በአል የሂስፓኒክ አሜርካውያን በሀገራችን ታሪክ፣ ባህል እና ውጤታማነት ላይ ያሳደሩትን ተጽእኖ እና ሚና የሚያከበር በአል ነው።
ሂስፓኒክ እና ላቲኖ የሆነው የማህበረሰብ ክፍል የዋሺንግተን ዲሲን ባህል፣ ኢኮኖሚ እና ማህረባዊ አቅጣጫ በመቅረጽ ጉልህ የሆነ ሚና ተጫውቷል። በቅርብ ጊዜ የተሰበሰበው ዳታ እንደሚያመለክተው ከሆነ ይህ ማህበረሰብ የከተማውን 12% የሚሆን የህዝብ ብዛት የሚሸፍን ነው። ዲሲ ሰፊ የሆነ የላቲኖ ማህበረሰብ መኖሪያ ስትሆን እንደ ኤልሳልቫዶር፣ ጓቲማላ፣ ሜክሲኮ እና ዶሚኒካን ሪፐብሊክ ካሉ ሀገራት ጠንካራ የሆነ ውክልና አለው። እነዚህ አስተዋጾዎች ዲሲ እያደገ የመጣውን የባህል ስብጥርና ባህላዊ ድምቀቱን፣ ፣ የኢኮኖሚ ጠቀሜታና ማህበራዊ ሂደቶቸ ዲስትሪክቱን ያጎለበቱ ሲሆን፣ የኢኮኖሚ መነቃቃትን እና ማህበራዊ እድገቱን ጨምሮ አሉታዊ ተጽእኖ እንዲይኖራቸው ያደርጋል።
በመሆኑም ይህ ጠንካራ እና ብዝሀ የሆነ ማህበረሰብ የከተማውን ባህላዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅጣጫን መቅረጽ ብቻ ሳይሆን ፖሊሲዎቹንም የሚያካትት ነው ነው። የዲሲ ቋንቋ ተደራሽንት አዋጅ (The DC Language Access Act) በ2004 የጸደቀ ሲሆን ከተማው ለሁሉም ነዋሪዎቹ ማለትም ዝቅተኛ የእንግሊዘኛ ችሎታ ላላቸውም ጭምር ማለት ነው፣ ፍትሃዊነ የመንግስት አገልግሎት ተደራሽነት እንዲኖራቸው ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው። ዲሲ ውስጥ ካለው ሂስፓኒክ ማህበረሰው ውስጥ አብዛኣኛው ስፓኒሽን እንደ አፍ መፍቻ ቋንቋ ከመጠቀማቸው አንጻር ይህ አዋጅ በሲቪል ህይወት ውስጥ እንዲሳተፉ በማስታጠቅ ትልቅ የሆነ ሚና አለው፣ ይህም ዲሲ ሁሉን አካታች እና ለሁሉም ነዋሪዎቹ እሴት ለመስጠት ያለውን አስተዋጾዎች ዲሲ እያደገ የመጣውን የባህል ስብጥር፣ የኢኮኖሚ ጠቀሜታና ማህበራዊ ሂደቶቸ አሉታዊ ተጽእኖ እንዲይኖራቸው ያደርጋል። የ ዲሲ ሰባዊ መብቶች ቢሮ (OHR) ይህንን ህግ በማስተዋወቅ፣ በተግበር እና ለዚህ ህግ በመገዛት ላይ ለተጫወተው ሚና እኔ በግሌ በጣም ኩራት ይሰማኛል።
በመላው የሴፕቴምበር ወር ዲስትሪክቱ የላቲኖ ቅርስን የሚያከብር ሲሆን ይህም የማህበረሰቡን ትልቅ የሆነ ታሪክ እና ሚና በሚያከብሩ የተለያዩ ኩነቶች የሚከበር ይሆናል። የሀገሪቱ ትልቁ የላቲኖ ክብረ በአል Fiesta DC ሴፕቴምበር 28 ላይ የሚካሄድ ሲሆን በከንቲባዋ ቢሮ ውስጥ ያሉ የላቲኖ ጉዳዮች ጓደኞቻችን Mi Pequeño El Salvador Festival ሴፕቴምበር 15 ክብረ በአልን ሲያከብር የሳልቫዶራውያን ማህበረሰቦች ለከተማችን የሚያበረክቱትን አስተዋጾ እውቅና በመስጠት ነው።
እነዚህን በአላት ስናከበር ብዝሀነትን የሚያከብር እና ከፍ አድርጎ የሚያይ ማህበረሰብን መገንባት ምን ያክል ወሳኝ እንደሆነ እናስታውሳለን። ቢሯችን ሁሉም ነዋሪዎች ከጀርባ ታሪካቸው ጋር በማይገናኝ መልኩ እድሎችን ለማግኘት እኩል እድል እንዳላቸው እና የጋራ የወደፊት ህይወታችንን በማነጽ ላይ ድምጽ እንዳላቸው ለማረጋገጥ ቁርጠኛ ነው። በጋራ የሂስፓኒክ እና ላቲኖ ማህበረሰቦቻችንን አስተዋኦ በማሰብ በዚህኛውም ሆነ በሁሉም ወራት እናክብር!
በአንድነት፣
ኬነዝ ሳውንደርስ