Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የዲሲ ሰበዊ መብቶች ቢሮ(OHR) የጁላይ ወርሃዊ ጋዜጣ –የዳይሬክተሩ መልዕክት 

Monday, July 22, 2024

የዲሲ ሰበዊ መብቶች ቢሮ(OHR) የጁላይ ወርሃዊ ጋዜጣ –የዳይሬክተሩ መልዕክት 

ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እና ጓዶች፦  

በጋውን እያጋመስን ስንሄድ፣ ስላደረግነው እድገት እና የሰብዐዊ መብቶች ቢሮ (OHR) እያመጣን ስላለው ለውጥና ወደፊት ሰለሚጠብቀን ስራ  ሳስብ ተስፋን በመሰነቅና በኩራት በመሞላት ነው። የጁላይ ወር ራስን የመቻል መንፈስን የሚገልጽ ሲሆን ለሁሉም የዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ  ነዋሪዎች እኩልነትን እና ፍትህን ለሚያረጋግጠው ተልኳችን ዋጋ ይሰጣል። 

ይህ ወር የአካል ጉዳተኛ ግለሰቦችን መብቶች በከፍተኛ ደረጃ ያሳደገ ዋና የህግ ክፍል የሆነውን የአሜሪካ አካል ጉዳተኞች ህግ (ADA)፣ አመታዊ ክብረ በአልን ያሳያል። የአሜሪካ አካል ጉዳተኞች ህግ በሁሉም የህይወት ዘርፎች የተደራሽነትን እና የአካታችነትን አስፈላጊነትን ያስታውሰናል። በ  የዲሲ ሰብአዊ መብቶች ቢሮ(OHR) ለመድልዎ መፍትሄ በመስጠት እና በሁሉም የስራ ዘርፎች ለሁሉም እኩል እድሎችን በማሳደግ እነዚህን መርሆች ለማስከበር ቁርጠኛ ነን። 

እንዲሁም ጁላይ የማህበረሰብን ተሳትፎ እና ግንዛቤን ማሳደግ ላይ ያለሙትን  ኢኒሼቲቮቻችንን ያስቀጥላል። በቅርቡ የሰብአዊ መብቶች ግንኙነት 2.0 ስልጠና ያካሄድን ሲሆን በከንቲባዋ የእስያ እና የፓስፊክ ደሴት ጉዳዮች በተዘጋጀው በ ቻይና ታውን ፌስቲቫል ከነዋሪዎች ጋር በመሳተፍ እና መድልዎ ለመቅረፍ ማህበረሰባችንን እውቀት እና መሳሪያዎች በማስታጠቅ ተሳትፈናል። በተጨማሪ በአካባቢ እና በፌደራል የሰብዐዊ መብት ህጎች ስር ያለዎትን መብቶች እና ግዴታዎች ግንዛቤ ለማሳደግ ተከታታይ የስራ ሰአታት ክፍለጊዜዎችን በተለያዩ የህዝብ ቤተመጽሃፍት ቅርንጫፎች የምናዘጋጅ ይሆናል። ስለእነዚህ ፕሮግራሞች ዝርዝር ማብራሪያዎች በጋዜጣችን ግርጌ ላይ ማግኘት ይችላሉ። 

የዲሲ ሰብአዊ መብቶች ቢሮ የስራ ቡድን መርጃዎቻችን እና ሂደቶችን ነዋሪዎች መብቶቻቸውን በተሻለ መልኩ እንዲደርሱ እንዲያግዟቸው በትጋት እየሰራ ቆይቷል። የእነዚህ ጥረቶች አካል እንደመሆኑ ለ ዲሲ አለማቀፍ የሚከፈልበት ፈቃድ እና ለ አረጋውያን እንክብካቤ ህግ አዲስ የመቀበያና መመዝገቢያማስገቢያ ቅጾችን ማዘጋጀት ጀምረናል:: ይህም ማንኛውንም መድልዎ ሪፖርት ለማድረግ እንዲሁም የፕሮግራም ጥቅማጥቅሞችን ይበልጥ በተስተካከለ መልኩ እና ያለጥላቻ መድረስን ለማረጋገጥ ነው። እነዚህ አዳዲስ ቅጾች ሁሉም ግለሰቦች አስፈላጊ በሆኑ አገልግሎቶች ውስጥ ያለውን ተደራሽነትን እና አካታችነትን ለማሳደግ ያለንን ቁርጠኝነት አጽንዖት ይሰጣሉ።  

በዚህ ወር የሃገራችንን የነጻነት ቀን ስናከብር ስናከብር እውነተኛ እኩልነት እና ፍትህ ለማግኘት የሚደረገው ትግል ቀጣይነት ያለው መሆኑንም እንዲሁ እናስታውስ። እያንዳንዳችሁ በዲስትሪክት አቀፍ ዝግጅቶች ላይ እንድትሳተፉ፣ ስለመብቶቻችሁ መረጃ እንዲኖራችሁ እና ሁሉም ሰው መድሎን ሳይፈራ የሚበለጽግበት ጠንካራ ማህበረሰብ በመፍጠር ተልዕኳችን እንድትቀላቀሉ አበረታታለሁ። 

በአንድነት፣ 

ኬኔት ሳውንደርስ  

ዳይሬክተር