የኦ-ኤች-አር (OHR) የጁላይ (July) ወርሃዊ የዜና መጽሄት- የዳይሬክተሩ መልእክት
የተከበራችሁ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶችና ጓደዶች፤
እነሆ ሰመር /በጋ / ገባ! ሙቀቱና ወበቁ ወደ ኋላ ሊጎትቱን ቢቃጡም ኦ-ኤች-አር (OHR)፤ የበጋው ወራት የማጠናከርያና የማህበረሰብ ተሳትፎ ግንባታ ስራ የበዛባቸው ወራት እንዲሆኑ በይበልጥ እየሰራ ነው። በዲስትሪክታችን ሰብዓዊ መብቶችን ለማስጠበቅና ለማጠናከር እንዲሁም የጀመርነውን ስራ ለማስቀጠል ዝግጁዎችና ደስተኞች ነን። ይህንን ግን ካለእናንተ ተሳትፎ በፍጹም ልናሳካው አንችልም።
እውቅና ካገኙት የማሰልጠኛ ፕሮግራሞቻችን አንዱ የሰብዓዊ መብቶች ሊያዞን ስልጠና (Human Rights Liaison Training) ሲሆን ይህ ስልጠና በአሁኑ (EmPOWERed Training) የስራችን ዋና መሰረት ወደ ሆነው ወደ ዲሲ ሰብዓዊ መብቶች ህግ (DC Human Rights Act) በምናመራበት ግዜ የእርሶ በስልጠናው መገኘትና አስተያየትዎን መስጠት እጅግ አስፈላጊ ነው። በዚህ ስልጠና ኦ-ኤች-አር (OHR) በዲስትሪክቱ ውስጥ ሰብዓዊ መብቶችና የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃዎች እንዴት በስራ ሊተረጎሙ እንደሚችሉ ለውይይት ያቀርባል። የዲስትሪክቱን የተጠበቁ /ከለላ የተሰጣቸው/23 ባህርያትን በጥልቀት የሚመለከቱ፤ እንደእነዚህ የተጠበቁ የ23 ባህርያት ስልጠና (23 Protected Traits Training) የመሳሰሉ ሌሎች ተጨማሪ ስልጣናዎችንም እንሰጣለን፤ መብቶችዎን ይወቁ (Know Your Rights Training) የተሰኘ ስልጣናም እንሰጣለን። በተጠየቅንበት ወቅትም መረጃ-አዘል አርእስቶችን ለማቅረብ ዝግጁ ነን።
በዚህ የበጋ ወቅትም የኦ-ኤች-አር (OHR) የስራ ሰዓታትን መልሰን እያመጣን ነው። እነዚህ የስልጠና ክፍለ-ግዜያቶች ከከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ለመገናኘት፣ ጥያቄ ለመጠየቅ፣ አድልዎን ለማስወገድ፣ መብቶችዎን ለማጠናከርና ቅሬታ እንዴት ማቅረብ እንደሚቻል ለመረዳት አመቺ ዕድል የሚፈጥሩልዎት ናቸው። ጽህፈት ቤቶች ክፍት ሆነው የሚቆዩባቸው ግዜያት ኦገስት እስከ ሰፕተምበር ሲሆን በከተማዋ ባሉት በተለያዩ የህዝብ ቅርንጫፍ መጻህፍት ቤቶች ይከናወናሉ። የዚህን ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቀጥሎ ይመልከቱ።
የአሜሪካ አካል ጉዳተኝነት ህግ (Americans with Disabilities Act (ኤ-ዲ-ኤ ADA) የጸደቀበትን 35ኛ ዓመት ማክሰኞ ጁላይ (July) 22 ቀን ለማክበርም ከአካል ጉዳተኝነት መብቶች ጽ/ ቤት (Office of Disability Rights) ጋር በትብብር በመበመስራታችን ደስተኞች ነን። በተቻለ መጠን እንደ አንድ አካታችነትና ተደራሽ ለማድረግ እንዲጎለብቱ የሚሰራ ድርጅት መጠን ይህ ዕለት ትርጉም ያለው፣ ያለፉ ስራዎች በጥሞና የሚገመገሙበትና የሃሳብ ልው ውጥ የሚደረግበት የሚኖርበት በዓል ይሆናል። እባክዎን ከእኔና ከዲሲ የአካል ጉዳተኝነት ምክር ቤት እንዲሁም ከከንቲባዋ መስማት የተሳናቸው፣ የማይናገሩና ማየት የተሳናቸው አካል ጉዳተኝነት ጽህፈት ቤት ውስጥ ከሚሰሩ ሌሎች መናገር የሚችሉ አካላት ጋር በመገናኘት ለከፍተኛ ተደራሽነትና አካታችነት ዕድገት አብረውን ይስሩ። ከታች የሚገኘውን በራሪ ወረቀት ይመልከቱና ዛሬውኑ ተመዝገቡ!
በመጨረሻም የርሶ ተሳትፎ እጅግ አስፈላጊ ነው። ከእኛ ጋር የሚገናኙት ለስልጠናም ሆነ በማህበረሰብ ኩነቶች ለመሳተፍ ወይም በመደበኛ የስራ ሰዓታት ለመገኘት የሚሰጡን አስተያየት አገልግሎታችንና ድጋፋችንን ቅርጽ ያስይዝልናል። ስለዚህ አሁን ከመለያየታችን በፊት እባክዎን ከታች ተያይዞ የቀረበውን መሪ ዕቅድ ጥናት (Strategic Action Plan) ለማጠናቀቅ ትንሽ ደቂቃዎች ይውሰዱ። የርሶን ሃሳብና አስተያየት በጉጉት እጠብቃለን::
በጋራ
ኬነት ሶንደርስ (Kenneth Saunders)
ዋና ዲሬክተር