Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የOHR የጁላይ 2026 ጋዜጣ - የዳይሬክተሩ መልእክት (Amharic)

Tuesday, July 21, 2026

የOHR የጁላይ 2026 ጋዜጣ - የዳይሬክተሩ መልእክት

ይህ የበጋ ወቅት የአገራችንን ታሪክ እንዲሁም ፍትህና እኩልነት ለሁሉም እንዲዳረስ የምናደርገውን ስራ ለማንጸባርቅ ዕድል የሚሰጠን ነው። ያለፉት 250 ዓመታት የዕድገትና ፈታኝ ግዜያቶች የነበሩ ሲሆኑ፤ ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ማድረግ  ቀጣይ ስራና ቁርጠኛነት የሚያስፈልገው መሆኑን ያስተውሱናል።

ዕለታዊ ስራችን የሚመራው በዲሲ የሰብዓዊ መብቶች መስርያ ቤት (DC Office of Human Rights ( ኤች አር OHR) ቁርጠኛነት ነው። የምንሰራው  ስራ፤  የዲሲ ነዋሪዎች ተማሪዎች እና ጎብኚዎች ከአድልዎ ነጻ በሆነ ሁኔታ መኖር፣ መስራትና መማር የሚያስችላቸውን ዕድል እንዲያገኙ ማድረግ ነው። ስራ፣ የመኖሪያ ቤት፣ የህዝብና የመንግስት አገልግሎቶችንና የትምህርት ተቋሞችን በማግኘት በኩል የእኩልነት መብትን በመጠበቅ፣ ተልእኮአችን፣ በጣም ቀላል ግን ዘላቂ የሆነውን- እያንዳንዱ ግለሰብ በአክብሮት፣ ፍትህና ሰብዓዊ ክብር በተመላበት ሁኔታ መያዝ አለበት የሚል   መርሃችንን ያንጸባርቃል።

የአሜሪካ ታሪክ ሁሉንም ሰው በእኩልነት የሚያካትት አኗኗር ለማጠናከር የዕድገት እንቅፋቶችን በተጋፈጡ ሰዎች የተገነባ ነው። የእነዚህ ሰዎች ጥረት ማህበረሰባችንን አጠናክሯል፣ ሁሉም ሰዎች በእኩልነት ሙሉ በሙሉ የሚሳተፉበትን ማህበረሰብ ለመፍጠር ወደሚያስችል ዘላቂ ዕድገት እንዲደረስ ያበረታታል፤ ይመራልም። የዲሲ ሰባዊ መብቶች ቢሮ (OHR ) ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኛነትና በዲስትሪክቱ ያሉት ሰዎችም የእኩልነት መብት ዕድላቸው እንዲረጋገጥ እገዛውን እንደሚያደርግ አሳይቷል።  

 የጁላይ ወር የሰብዓዊ መብቶች ህግ ታሪካዊ መለያ (landmark) የሆነውና አገራችን በአካል ጉዳተኞች ላይ ያላትን አቀራረብና አስተያየት ለመቀየር ያስቻለና እነኚህ መብቶች በሕግ እንዲደነገጉና የአካል ጉዳተኞች በማንኛውም ማህበራዊ ህይወት ውስጥ እኩል መሳተፍ እንዲችሉ የሚያደርግ  አካል ጉዳት ላለባቸው አሜሪካውያን የወጣው ህግ (Americans with Disabilities Act ( ADA) 36 ዓመት የሚከበርበት ወር ነው። 30 በላይ ዓመታት  በኋላ አሜሪካ የአካል ጉዳተኝነት ህግ (ADA)  ተደራሽነት፣ አካታችነት እና ሙሉ ተሳታፊነት ሕጋዊ ግዴታዎች ብቻ ሳይሆኑ፤ አካባቢያችንን፣ የስራ ቦታዎችን፣ ትምህርት ቤቶቻችንና ህዝባዊ ቦታዎችን የሚያጠናክሩ የጋራ መሰረታዊ እሴቶች መሆናቸውን ማስታወሱን እየቀጠለ ነው።

ይህንን አስፈላጊ ምዕራፍ ለማክበር ኦ ኤች አር (OHR) አካል ጉዳተኝነት መብቶች መስር ቤት (Office of Disability Rights) ከዲሲ ስነ ጥበብና ሰብዓዊ ጥናቶች ኮሚሽን ( DC Commission on the Arts and Humanities) ከዲሲ የህዝብ ቤተ መጻህፍት ( DC Public Library) እና ከስነ ጥበብ ያስችላል (Art Enables) ጋር በመተባበር   የራስን ሓሳብ የመግለጽ ዕድል፤ በዲሲ ሁሉን አካታች ስነ ጥበብ (Access to Expression: Inclusive Arts in the District) ለማቅረብ ችሏል። ይህ ልዩ የማህበረሰብ ዝግጅት፤ በሚደረገው የስነ ጥበብ ኤግዚቢሽን፤ የውይይት ግዜ፣ ተሳትፎን በሚያበረታቱ የስነ ጥበብ እንቅስቃሴዎች እና ከማህበረሰቡ ምንጮች ጋር በሚያገናኙ ዕድሎች አማካኝነት፤ የአካል ጉዳተኛ ስነ የሰነ ጥበበብ ባለሙያዎች  ፈጠራ፣ አመለካከት እና የሚደርጓቸውን አስተዋጾዎች ያስተጋባል።  በዚህ የኤ ኤን (ADA) ዘላቂ ቅርስ በምናከብረበትና በበለጠ አካታችና ተደራሽ የሆነ ዲስትሪክት ለመገንባት የጋራ ቁርጠኛነታችንን በድጋሚ በምናረጋግጥበት ዝግጅት ከእኛ ጋር አብረው እንንዲሆኑ እንጋብዛለን።   

መጪውን ግዜ በምንቃኝበት ወቅት ቃል የተገባለት የእኩልነት ዕድል በዲስትሪክቱ ውስጥ ለሚኖሩ፣ ለሚሰሩ፣ ለሚማሩና ዲስትሪክቱን ለመጎብኘት ለሚመጡ ሰዎች በተግባር እንዲተረጎም በአንድነት መስራታችንን እንቀጥል።