Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የስራ አስኪያጅ ወርሃዊ መልዕክት- ሜይ 2026 (Amharic)

Thursday, May 28, 2026

የስራ አስኪያጅ ወርሃዊ መልዕክት- ሜይ 2026

ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እና ወዳጆች፦
 

ይህ ሜይ ስለ ጤና፣ ደህንነት እና ፍትሃዊነት እያሰላሰለ ቅርስን ለማክበር አስፈላጊ አጋጣሚ ይሰጣል። የእስያ አሜሪካዊ፣ የሃዋይ ተወላጅ እና የፓሲፊክ ደሴት ተወላጅ (AANHPI) የቅርስ ወር እና ብሔራዊ የሴቶች ጤና ወርን ስናከብር፣ የAANHPI ማህበረሰቦችን ታሪክ እና አስተዋጽኦ እያከበርን ለሁሉም ሴቶች ተደራሽ፣ ፍትሃዊ እና በባህል ረገድ ምላሽ የሚሰጥ የጤና አጠባበቅ አስፈላጊነትን እናረጋግጣለን።

የ AANHPI የቅርስ ወር የዲስትሪክታችን የ AANHPI ማህበረሰቦች ሰፈሮቻችንን፣ የስራ ቦታዎቻችንን፣ ተቋሞቻችንን እና ማህበረሰቦቻችንን የቀረጹባቸውን በርካታ መንገዶች እንድናስብ ይጋብዘናል። ቀጣይነት ባለው መልኩ ከተማችንን ለማጠናከር አመራር፣ ፈጠራ እና ጽናት የምናከብርበት ጊዜ ሲሆን፣ እንዲሁም ራሳችንን ለጥልቅ ግንዛቤ እና የበለጠ ፍትሃዊ እርምጃ የምንወስድበት ጊዜ ነው።

ሜይ ወር ውስጥ በጥልቀት ለመሳተፍ ለሚፈልጉ፣ በዲስትሪክቱ ውስጥ ካሉ ማህበረሰቦች ጋር ለማክበር፣ ለመማር እና ለመገናኘት የተለያዩ ዝግጅቶች እና እድሎችን ለማግኘት የከንቲባ ን የእስያ እና የፓሲፊክ ደሴት ጉዳዮች ቢሮ እንዲከተሉ አበረታታችኋለሁ።

ብሔራዊ የሴቶች የጤና ወር በተመሳሳይ ሁኔታ እያንዳንዱን ቤተሰብ እና ማህበረሰብ ነክ ጉዳይ ላይ ትኩረት ያደርጋል። የሴቶች ጤና ከቤተሰቦቻችን፣ ከስራ ቦታዎቻችን እና ከአካባቢያችን ደህንነት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው። ግንዛቤን በማሳደግ፣ የመረጃ እና የጋራ ተደራሽነትን በማስፋፋት እና እንክብካቤን እና ደህንነትን የሚያበረታቱ ፖሊሲዎችን እና ልምዶችን በመደገፍ ለሁሉም ጤናማ እና የበለጠ ደጋፊ ማህበረሰቦችን ለመገንባት እንረዳለን።

እነዚህ ሁለት በዓላት የጋራ እውነታንም ይናገራሉ፤ ሰዎች ጤናንና እንክብካቤን በተለየ መንገድ ያጋጥማቸዋል፣ በመሆኑም እነዚያ ልምዶች ብዙውን ጊዜ በቋንቋ፣ በባህል እና በተደራሽነት የተቀረጹ ናቸው። ለዚህም ነው ውክልና እና እምነት በተለይ ሰዎች መረጃ፣ ድጋፍ እና እንክብካቤ በሚፈልጉባቸው ቦታዎች ላይ አስፈላጊ የሆኑት። ክብር ሲሰጣቸውና ለሎች ሲረዷቸው በእውቀት ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለመስጠት እና የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ ለማግኘት የተሻለ ቦታ ይኖራቸዋል።

ብሔራዊ የሴቶች ጤና ወርን ለማክበር የዲሲ የሰብአዊ መብቶች ቢሮ እና የከንቲባ የሴቶች ፖሊሲ እና ተነሳሽነት ጽ/ቤት በእርግዝና ጥበቃዎች፣ በሴቶች የስራ ቦታ ጤና እና በዲስትሪክቱ ውስጥ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና የበለጠ አመቺ የስራ ቦታዎችን የሚደግፉ ሀብቶች ላይ ምናባዊ አውደ ጥናት አዘጋጅተዋል። ዝግጅቱ ቢጠናቀቅም መረጃው እርጉዝ ለሆኑ፣ ወላጅ ለመሆን ለሚያቅዱ ወይም የሥራ ቦታ መብቶቻቸውን በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት ለሚፈልጉ ሁሉ ጠቃሚ ሆኖ ይቀጥላል። አንባቢዎች የተቀረጸውን ቪዲዮ እዚህ እንዲመለከቱ እና ሌሎች እኛጋ የሚገኙ ጠቃሚ የሆኑ ሀብቶቻችንን እንዲቃኙ እናበረታታለን።

በዚህ ወር፣ እርስ በርሳችን መማማርን እንቀጥል፣ ለእንክብካቤ እንቅፋቶች  የሆኑ ለማስወገድ እንጣር እና ልዩነትን እንዲሁም የጤና እኩልነትን የሚያደንቁ ማህበረሰቦችን እንገንባ። በጋራ መግባባት፣ አጋርነት እና ቀጣይነት ባለው ተሳትፎ ሁሉም ነዋሪዎች የተከበሩበት፣ የሚደገፉበት እና እንዲበለጽጉ የሚያስችል ዲስትሪክት ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት ልናግዝ እንችላለን።