የዳይሬክተሩ አጭር መልእክት
ኤፕሪል ወር ለሁሉም በፍትህ፣ በክብር እና ለሁሉም እድል ላይ የተመሰረቱ ማህበረሰቦችን የመገንባት የጋራ ኃላፊነታችንን የሚያሳይ ቁልፍ ማሳሰቢያ ነው። በዚህ ወር፣ ፍትሃዊ የቤቶች ወርን ፣ የዲሲ የቋንቋ ተደራሽነት ወርን እና የዳግም እድል ወርን - የሰብአዊ መብቶች ቢሮ (OHR) ዋና ተልዕኮን እና በየቀኑ ለማክበር የምንጥራቸውን እሴቶች የሚያንፀባርቁ ሶስት በዓላትን በማክበር ላይ ነን።
ፍትሃዊ የቤቶች ወር በ1968 የወጣውን የፍትሃዊ ቤቶች ህግ መፅደቁን ያስታውሳል፤ ይህም የመኖሪያ ቤቶች አቅርቦትን በተመለከተ መድልዎ እንዳይፈጸም የሚከለክል ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የፌዴራል ህግ ነው። ከአምስት አስርት ዓመታት በኋላ የተስፋ ቃላቸው ሙሉ በሙሉ ከግብ አልደረሰም። በዲስትሪክቱ ውስጥ የሰባዊ መብቶች ቢሮ (OHR ) ኮሙኒቲስ ኦፍ ከለር የተሰኙትን ማህበረሰቦችን፣ የአካል ጉዳተኞችን፣ ቤተሰቦችን እና ሌሎች ጥበቃ /ከለላ /የሚደረግላቸውን ቡድኖችን ከቀጣይ ቤቶችን በተመለከተ መድልዎ ጥበቃ/ ከለላ/ የሚደረግላቸውን የአካባቢ እና የፌዴራል የቤቶች ህጎችን ማስፈጸሙን ቀጥሏል። ፍትሃዊ ቤቶችን ማራመድ ሕጉን ማስፈጸም ብቻ ሳይሆን ነዋሪዎችን የቤት አቅራቢዎችን እና ባለድርሻ አካላትን ስለ መብቶቻቸው እና ኃላፊነቶቻቸው ማስተማርን - እና በቤቶች ስርዓቶቻችን ውስጥ የሚቀጥሉ የስርዓት እንቅፋቶችን ለማፍረስ በጋራ መስራትን ይጠይቃል። በዚህ ወር OHR በዲስትሪክቱ ውስጥ ስለሚገኙ የመኖሪያ ቤቶች መብቶች እና ሀብቶች መረጃ ለማጋራት “ፍትሃዊ የቤቶች ወንር በተመለከተ በመጪውአርብ ወርክሾፕ እያዘጋጀ ነው። በዚህ ወር የOHR ከእኩል እና ፍትሃዊ መብቶች ማዕከል፣ ከዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ የቤቶች እና የማህበረሰብ ልማት መምሪያ እና ከዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ኮሎምቢያ ዲስትሪክት የአረጋውያን እና የማህበረሰብ ኑሮ መምሪያ ጋር በመተባበር በዲስትሪክቱ ውስጥ ስለሚገኙ የመኖሪያ ቤቶች መብቶች እና ሀብቶች መረጃ ለማጋራት “ፍትሃዊ የቤቶች ወር አርብ” የሚባለውን ወርክሾፕ አዘጋጅተናል።
የዲሲ የቋንቋ ተደራሽነት ወር ሁሉም ነዋሪዎች - የምንናገረው ቋንቋ ምንም ይሁን ምን - አስፈላጊ የመንግስት አገልግሎቶችን እና መረጃዎችን ማግኘት እንዲችሉ ለማረጋገጥ ያለንን ቁርጠኝነት ያጎላል ። በ2004 በወጣው የቋንቋ ተደራሽነት ሕግ መሠረት፣ ዲስትሪክቱ ሁሉም ነዋሪዎች የዲስትሪክቱን መንግሥት ሙሉ በሙሉ መረዳትና ከእነሱ ጋር መተባበር እንዲችሉ የቋንቋ እንቅፋቶችን ለመቀነስ ትርጉም ያለው እርምጃ ወስዷል። በተጨማሪም፣ የቋንቋ ተደራሽነት ፕሮግራማችን በመላው ዲስትሪክት ውስጥ ባሉ መስሪያ ቤቶች በስራ ሰአት በማካሄድ የትርጉም አገልግሎቶችን እና ሌሎች የሚገኙ የቋንቋ ተደራሽነት ግብዓቶችን ማግኘት ላይ መረጃ ለማጋራት ችሏል።
የሁለተኛ ዕድል ወር ከእስር ቤት ዳግም ወደ ነበረው ህይወታቸው ሚመለሱ ዜጎችን በክብር እና በድጋፍ ህይወታቸውን እንደገና ለመገንባት መንገዶችን መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ያጎላል። የOHR ከእስር ቤት የተመለሱና ዳግም ወደ ነበረው ህይወታቸው ሚመለሱ ዜጎችን መብቶች የጥበቃ/ ከለላ/ የሚደረግላቸውን ሁለት ቁልፍ ህጎችን ያስፈጽማል፤ እነሱም ብዙውን ጊዜ “ቦክሲንግ ባን” ተብሎ የሚጠራው የፍትሃዊ የወንጀል መዝገብ ማጣሪያ ማሻሻያ ህግ እና የፍትሃዊ የቤቶች መዝገብ ማጣሪያ ህግ ናቸው።
የOHR ሰራተኞች ወደ ሀገራቸው ለሚመለሱ ዜጎች አላስፈላጊ እንቅፋቶችን በመቀነስ የስራ እድልን እና የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ለማስፋፋት መስራቱን ይቀጥላል። OHR ሐሙስ ኤፕሪል 30 555 12th St NW በሚገኘው ሰከንድ ቻንስ ኤክስፖ ላይ ከከንቲባዋ ከእስር ቤት የተመለሱ ዜጎች ጉዳዮች ቢሮ (MORCA) ጋር ይቀላቀላሉ። በፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍለ በነፃ እዚህ መመዝገብ ይችላሉ።
እነዚህ በዓላት አንድ ላይ ሆነው ስርዓቶች እንዴት ማግለልና ኃይል መስጠት እንደሚችሉ -- እና እኛ እንደ የሕዝብ አገልጋዮችና የማኅበረሰብ አባላት የለውጥ ወኪሎች እንዴት መሆን እንደምንችልና ምን ማደረግ እንዳለብን ያሳስቡናል ። ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ማረጋገጥ፣ ለመንግስት አገልግሎቶች የቋንቋ እንቅፋቶችን ማስወገድ ወይም ከእስር ቤት የተመለሱ ዜጎቻጎችንን ዳግም ሁለተኛ ዕድል መስጠት ይሁን - ስራችን ሆን ተብሎ፣ እርስ በርስ የሚቆራኙ እና በፍትህ ላይ የተመሰረቱ መሆን አለባቸው።
በዚህ ወር እና በየወሩ ማንነታችን፣ አስተዳደጋችን ወይም ቋንቋችን ሳይለይ ሁሉም ሰው ፍትሃዊ እና ትርጉም ያለው የተሳካ እድል የሚያገኝበት ዲስትሪክት ለመፍጠር ያለንን ቁርጠኝነት እናድስ።
በአጋርነት እና በዓላማ፣

