የOHR የጁላይ ወርሃዊ ዜና መጽሄት – የዳይሬክተሩ መልዕክት
ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እና ውዳጆች፦
መልካም የፕራይድ ወር፣ ዲሲ!
ጁን በ2025 የአለም አቀፍ የፕራይድ ከየከንቲባዋ እና ከማህበረሰባችን ጎን ለጎን ለመስሪያ ቤታችን አስደሳች ወር ነበር። የፕራይድ ወር በቀጠለ ቁጥር ቡድናችን ከሀገር ውስጥ እና ከአለምአቀፍ አካላት ጋር በተለያዩ ተፅዕኖ ፈጣሪ ክስተቶች ማለትም የብላክስ ፕራይድ ፣ ትራንስ ፕራይድ ፣ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ፣ የማህበረሰብ ውይይቶች ሰሚት እና ዓመታዊ የዲሲ የፕራይድ ፕሬድን ጨምሮ በንቃት በመሳተፍ ላይ ይገኛል። የኛን የፕራይድ እና ደህንነ ፖስተር /Protecting Your Pride and Safety poster/ ወይም የቡድን OHR መጋራትን እና የተደራሽነት መረጃን የማጋራት በተንን አይተው ይሆናል!
በጁን የሚከበረው የፕራይድ ወር፣ መነሻውን በ1969 በኒውዮርክ ከተማ ከነበረው የስቶንዋል አመፅ ጋር የተያያዘ ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ፣ በLGBTQIA+ ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ልዩ ልዩ ማንነቶችን የምናከብርበት እና ማህበረሰቡ የሚያጋጥሙትን ቀጣይ ተግዳሮቶች ግንዛቤ በማሳደግ ላይ ነው። የዘንድሮው ፕሬድ፣ ሰልፎች እና ሌሎች ባህላዊ ዝግጅቶች ተጠናቀው ሊሆን ቢችልም፣ ለLGBTQIA+ ማህበረሰብ አባላት ጥበቃ እና መብቶች ሁል ጊዜም እንዳሉ በድጋሚ ማረጋገጥ እፈልጋለሁ። በዲሲ ውስጥ ስለተጠበቁ ባህሪያት ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለማግኘት የእኛን የመረጃ ፖርታል ማሰስዎን ያረጋግጡ።
በዚህ ወር ጁን 10 የዲሲ ሰባዊ መብቶች ቢሮን በጀት በተመለከት በዲሲ ካውንስል ፊት ኦፊሴላዊ ምስክርነት አቅርበያለሁ። የኤጀንሲያችንን ስራ ተፅእኖ በማጉላት ማህበረሰባችንን ለማገልገል፣ ነዋሪዎችን በእውቀት እና በመረጃ ለማብቃት ያለንን ቁርጠኝነት ማረጋገጥ ምንጊዜም ክብር ነው። ችሎቱን እንደገና ለመጎብኘት ከፈለጉ፣ በኦንላይን ሊመለከቱት ይችላሉ ወይም በድረ-ገፃችን ላይ የእኔን ኦፊሴላዊ ምስክርነት ያንብቡ።
በጀቱን በምቅረብ ረገድ በሰጥሁት ማርጋገጫ ምስክርነት ላይ አፅንዖት እንደሰጠሁት፣ ምንም እንኳን ሌላ ፈታኝ የበጀት አመት ቢገጥመንም እና ዋና አገልግሎቶችን አስጠብቆ ለማስቀጠል ከባድ ውሳኔዎችን ብንወስድም አስፈላጊ ተልእኳችን ሁሌም ይቀጥላል። ምንም አይነት መሰናክሎች ቢኖሩም የቡድናችን ቁርጠኝነት ነዋሪዎች መረጃ እንዲያገኙና ስልጣን እንዲኖራቸው እንደሚያደርግ ሙሉ እምነት አለኝ።
በማህበራዊ ድህረ-ገፆች ላይ ከእኛ ጋር እንደተገናኙ ይቆዩ፣ ስለ መጪ የውይይት ዝግጅቶች እና የስልጠና እድሎች ማሻሻያ - እርስዎን ለማየት በጉጉት እንጠባበቃለን!
በአንድነት፣
ኬነዝ ሳውንደርስ