Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

To find support and resources for federal workers, visit fedsupport.dc.gov.

-A +A
Bookmark and Share

የዲሲ ሰብአዊ መብቶች ቢሮ(ኦ ኤች አር) የማርች 2025 ወርሃዊ ጋዜጣ ፣ የዳይሬክተር መልእክት

Thursday, March 27, 2025

የዲሲ ሰብአዊ መብቶች ቢሮ(ኦ ኤች አር) የማርች 2025 ወርሃዊ ጋዜጣ ፣ የዳይሬክተር መልእክት


ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እና ወዳጆች፡-


ምንም እንኳን አንዳንድ ጊዜ እርግጠኛ ባልሆኑ ነገሮች እና ፈተናዎች የተከበብን ቢሆንም የእኔ የስራ ባልደረቦች አባላት እና እኔ
በምናምንበት የማዳረስ እና የማስፈጸም ጥረታችን ወደፊት ማስኬድ እንቀጥላለን፣ ከናንተ በኩል አስፈላጊ የሆኑ መርጃዎችን
እግብአቶችን እና ተስፋን ይስጡን።
የማርች ወር ለሴቶች መብት ተሟጋቾች ጽናት፣ ጥንካሬ እና እሴቶችን ያስታውሰናል። በሴቶች የታሪክ ወር ውስጥ እውቅና ያላቸው
እና እውቅና የሌላቸው መስራቾች ስኬቶችን እንዲሁም ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች እናከብራለን። ዋሽንግተን ዲሲ እንደ ሜሪ
ቸርች ቴሬል፣ ባርባራ ሌት ሲሞንስ፣ አና ሁልያ ኩፐር፣ ዶሮቲ ሃይት፣ እና ሌሎችም ያሉ ለሴቶች እኩልነት የሚታገሉ በርካታ ታሪካዊ
ሰዎች መገኛ ነች። የእነሱ ረጅም ጊዜ በዋጋ ሊተመን የማይችል ጉዞ ጥረታችን ቀጣይነት ያለው መሆን እንዳለበት የማያቋርጥ
ማሳሰቢያ ሆኖ ያገለግላል፣ እና በጊዜ የተገደበ መሆን የለበትም።


ኦኤች አር ባለፉት ተሟጋቾች በተነሳው ቀጣይነት ያለው ልማት አካል ሆኖ ጉልህ እድገቶችን በማስመዝብ ስራውን ቀጥሏል።
ከማርች በኋላ ማህበረሰባችንን ወደ ሰፊ የሥልጠና እና የማስተዋወቅ ክፍለ ጊዜዎች ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን እንጋብዛለን። በዚህ
ጊዜ ከ (ኦኤች አር) ሰራተኞች ጋር በቀጣይcበሚኖሩ የቢሮ ሰዓቶችና የስልጠና ክፍለ ጊዜዎች በቀጥታ በመገናኝት ቅሬታዎች
በሚቀርቡበት ወቅት የሚታዩ ከአድሎ ጋር የተያያዙ ያመመሪያዎችን በሚመለከት መረጃ ማግኘት ይችላሉ። ስለመድረኮቻችን
ዝርዝር እና ወቅታዊ መረጃ ከፈለጉ የማህበራዊ ሚዲያ ቻናሎቻችንን ይከታተሉ፣እንዲሁም መብቶችዎን ይወቁ የሚለውን እዚህ
በመጫን መጠየቅ ይችላሉ።


ከእርስዎ ጋር ለመስራት እና እርስዎን ለመረዳት ያለን ቁርጠኝነት፣በቅርበት መስራት ፣ እንዲሁም በአስቸጋሪ ወቅት መረጃ መያዝ
ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ያመለክታል። የኦኤች አር የስልጠና እና የማዳረስ ፕሮግራሞች ማህበረሰባችንን ለማጠናከር እና
ለአዳዲስ ስራዎች ለሚመጡ ፈተናዎች ለመዘጋጀት ስለሚረዳን እባኮትን ንቁ ተሳትፎ ያድርጉ። እኔን እና የኦኤች አር ቡድንን
በመቀላቀል ትብብር እና ግንዛቤን ለመገንባት እንዲሁም በማህበረሰባችን መካከል የመረዳዳት ባህልን ለማጠናከር አብረውን
ይስሩ። ደተባባሪ ማህበረሰብ ለሁሉም!


በህብረት
ኬኔት ሳውንደርስ