Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የOHR የኦገስት ወርሃዊ ጋዜጣ  – የዳይሬክተር መልዕክት

Wednesday, August 21, 2024

የOHR የኦገስት ወርሃዊ ጋዜጣ  – የዳይሬክተር መልዕክት

የትምህርት አመቱ አጀማመር የተሃድሶና እና የክህሎት ጊዜ ሲሆን ተማሪዎች በትምህርት ላይ ሚሳተፉበት፣ አዳዲስ ክህሎቶችን የሚያዳብሩበት እንዲሁም ከእኩዮቻቸው እና ከአስተማሪዎቻቸው ጋር ትርጉም ያለው ግንኙነት የሚገነቡበት ነው። በመላው ዲስትሪክ ያሉ ተማሪዎች ለአዲሱ የትምህርት አመት በሚዘጋጁበት ጊዜ እኛን የወጣቶችን ጥቃት የመከላከል ፕሮግራም አጉልቼ ማሳየት በመቻሌ ኩራት ይሰማኛል። ይህ ፕሮግራም ደጋፊ እና አክብሮት የተሞላበት የትምህርት ቤት ማህበረሰብን ለማስፋፋት የሚያሳይ ያለን ቁርጠኝነት መሰረት ነው።

ጥቃት-አካላዊ፣ የቃልም ሆነ ኦንላይን የላይ- የተማሪውን ደህንነት እና የትምህርት ብቃት ላይ ጥልቅ የሆነ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። ፕሮግራማችን በትምህርት፣ በድጋፍ እና በመከላከያ ስልቶች ጥምረት አማካኝነት ጥቃትን ለመዋጋት ቁርጠኛ ነው። የሌሎች ችግር እንደራስ ማየትን፣ መከባበርን እና መረዳትን ከፍ የሚያደርጉ ስልጠናዎችን እና መርጃዎችን ለመስጠት ከዲስትሪክቱ ትምህርት ቤቶች፣ ወላጆች እና ተማሪዎች ጋር በቅርበት እንሰራለን። የወጣቶች የሰብዓዊ መብቶች አምባሳደር ፕሮግራም መጀመርን ጨምሮ የቅርብ ጊዜ ኢኒሼቲቮች ከተማሪዎች ጋር ለማሳተፍ እንዲሁም በማህበረሰባችን ውስጥ መሪ እንዲሆኑ ለማስቻል ያለንን ንቁ አቋም ያመለክታሉ። ተጨማሪ መረጃ እና ተጨማሪ መርጃዎችን ለማግኘት እባክዎ የፕሮግራም ስራ አስኪያጅ ኤርነስት የሆኑትን ሼፐርድን በ[email protected] ያነጋግሩ።

እንዲሁም ኦገስት ብሄራዊ የጥቁር የንግድ ስራ ወር ሲሆን በጥቁር ባለቤትነት ስር ያሉ የንግድ ስራዎች በኢኮኖሚያችን እና በባህላችን ላይ ስላመጡት ጥንካሬ፣ ፈጠራ እና ተጽዕኖ ታላቅ ተጽዕኖ ያለውኛ አስታዋሽ ነው። ጥቁሮች ስራ ፈጣሪዎች የካፒታል፣ የመርጃዎች እና የእድሎች ስልታዊ እንቅፋቶችን ጨምሮ ወሳኝ የሆኑ ተግዳሮቶች በታሪክ የገጠሟቸው ሲሆን መጋፈጣቸውን ቀጥለዋል። እነዚህ መሰናክሎች ቢኖሩም ተግተው መስራታቸው እና ፈጠራቸው ማህበረሰባችንን የሚያበለጽጉ እና ወደ ኢኮኖሚያዊ እድገትን የሚያመሩ የሚያበለጽጉ የንግድ ስራዎችን አስገኝቷል።

እኩል እድሎችን እና አካታችነትን ለማስፋፋት ቁርጠኛ እንደሆነ መስሪያ ቤት፣ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እይታዎችን ማዳበር ግለሰብ ስራ ፈጣሪዎችን መጥቀም ብቻ ሳይሆን መላውን ማህበረሰባችንን እንደሚያጠናክርም እንገነዘባለን። በዚህ ወር እና ከዚያም ባሻገር ሁሉም ሰው በመግዛት፣ መልዕክቱን በማሰራጨት ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ከእነዚህ የንግድ ስራዎች ላይ በመሳተፍ በአካባቢው የሚገኙትን በጥቁር ባለቤትነት ስር ያሉ የንግድ ስራዎችን እንዲደግፍ አበረታታለሁ። እንዲሁም እባክዎን በአሜሪካ ውስጥ በዲስትሪክቱ ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ በጥቁር ባለቤትነት ስር ስላሉ የንግድ ስራዎች ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ የበለጠ ለማወቅ በጥቃቅንና አነስተኛ እንዲሁም በአካባቢ የንግድ ስራዎች እድገት መምሪያ ካሉት አጋሮቻችን ይህንን የመረጃ ድረገጽ ይመልከቱ። ጥቁር ስራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ የተነደፉ ጠቃሚ መርጃዎች ያግኙ እንዲሁም እርስዎ የሚሰጡት ድጋፍ እነዚህን የንግድ ስራዎች እንዴት እንደሚያግዝ ይወቁ።

ይህንን አዲስ የትምህርት አመት ስንጀምር እና የጥቁር ስራ ፈጣሪዎች ከፍተኛ ውጤቶች ስናከብር ሁሉም ሰው ማደግ የሚችልበት እና ስኬታማ የሚሆንበት አስተማማኝ እና የበለጠ ፍትሃዊ የሆነ አካባቢን ለማስፋፋት በሚደረገው ጥረት ሁላችንም በድጋሚ ቁርጠኛ እንሁን!

 

በአንድነት፣

 

ኬነዝ ሳውንደርስ

ዋና ዳይሬክተር