Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

ጋዜጣዊ መግለጫ - የቤት ውስጥ ሰራተኞች ከኦክቶበር 1፣ 2023 ጀምሮ በዲሲ የሰብዐዊ መብቶች ህግ መሰረት አድልዎ እንዳይደረግባቸው ጥበቃ ይደረግላቸዋል። (Amharic)

Tuesday, October 10, 2023

OHR Logo Color Transparent Background_TC_3.14.2013.png

ዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ የሰብዐዊ መብቶች ቢሮ

 

ጋዜጣዊ መግለጫ

 

ለአስቸኳይ መግለጫ፦

ሴፕቴምበር 29፣ 2023

ለበለጠ መርጃ

ጀምስ ዩ (OHR) - (202) 227-1681፤ [email protected]

 

የቤት ውስጥ ሰራተኞች  ከኦክቶበር 1፣ 2023 ጀምሮ በዲሲ የሰብዐዊ መብቶች ህግ መሰረት አድልዎ እንዳይደረግባቸው ጥበቃ ይደረግላቸዋል።

የዲሲ የሰብአዊ መብቶች ቢሮ አሁን የይግባኝ ጥያቄዎችን በመቀበል ለቅጥር ጥበቃዎች ዋስትና ይሰጣል

 

(ዋሽንግተን፣ ዲሲ) - ከኦክቶበር 1፣ 2023 ጀምሮ የቤት ሰራተኞች በዲሲ የሰብዐዊ መብቶች ህግ (DCHRA) መሰረት በ2022 የቤት ሰራተኞች የቅጥር መብቶች  ማሻሻያ ህግ (“ህጉ”) ውሳኔ ጥበቃ ይደረግላቸዋል። ህጉ በዲሲ ውስጥ ያሉ ሁሉም የቤት ሰራተኞች በሌሎች ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ካሉ አቻዎቻቸው ጋር ተመሳሳይ መብቶች እና ጥበቃዎች እንደሚደረግላቸው ያረጋግጣል፣ እንዲሁም በስራ ላይ እያሉ መብታቸው እንደተጣሰ የሚሰማቸው የቤት ሰራተኞች አሁን ለዲሲ የሰብዐዊ መብቶች ቢሮ (OHR) መድልዎ የተመለከቱ ጥያቄዎችን ማቅረብ ይችላሉ።

 

የቤት ሰራተኛ በግል መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በክፍያ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ሰራተኛ(ኞች) ተብሎ ይገለጻል። የቤት ሰራተኞች እንደ ሞግዚት ያሉ በመደበኛነት የቤት ውስጥ የልጅ እንክብካቤን የሚሰጡ ሰዎችን፤ የአረጋውያን እንክብካቤ ለምሳሌ መንከባከብ ወይም ሌላ የቤት ውስጥ ረዳት፤ የጽዳት አገልግሎቶች፤ ምግብ ማብሰል ወይም ምግብ ማዘጋጀት፤ እና ሌሎች ተዛማጅ የቤተሰብ አገልግሎቶች ሊያካትቱ ይችላሉ። ፍቺው የቤተሰብ አባላትን፤ እንደ ግንባታ ወይም የቧንቧ ስራ ያሉ የቤት ውስጥ ጥገናዎችን የሚያካሂዱ ሰዎችን፤ የቤት እንስሳትን የሚንከባከቡ ሰራተኞችን፤ ወይም መደበኛ ባልሆነ ወይም እንደ አስፈላጊነቱ አገልግሎት የሚሰጡ ሰዎችን አያካትትም።

 

ህጉ በቤታቸው ውስጥ የቤት ሰራተኞችን የሚቀጥሩ ሰዎችን ለማካተት የአሰሪዎችን ትርጓሜ ያሻሻለ ሲሆን የቤት ሰራተኞች በቅጥር ስር በተካተቱ በማናቸውም 18 ጥበቃ /ከለላ የሚደረግላቸው ባህሪያት ላይ ከተመሰረተ መድሎ ጥበቃ እንደተደረገላቸው ያረጋግጣል። አድሎአዊ ድርጊቶች አንድን ሰው አለመቅጠር እና አንድን ሰራተኛ ለማይመች የስራ አካባቢ ተጋላጭ ማድረግ ሲሆን፣ ይህም ጾታዊ ትንኮሳ እና ለOHR ቅሬታ በማቅረብ ምክንያት የሚደረግ የበቀል እርምጃን ይካትታል።

 

DCHRA ሁሉም አሰሪዎች በDCHRA መሰረት የሰራተኛቸውን መብቶች በሚመለከት በሚታይ ቦታ ማስታወቂያ እንዲለጥፉ ያስገድዳል። መለጠፍ የማይቻል ከሆነ ወይም በግል መኖሪያ ቤት ውስጥ ለመለጠፍ የማይመች ከሆነ፣ አሰሪዎች ከመለጠፍ ይልቅ ለቤት ሰራተኛቸው(ኞቻቸው) የማስታወቂያውን ግልባጭ ሊሰጡ ይችላሉ።

 

የ OHR እኩል የስራ እድል (EEO) ፖስተር እዚህ ይገኛል።

 

እነዚህን አዳዲስ የቤት ሰራተኛ ጥበቃዎች በጥልቀት ወቅ ከፈለጉ እባክዎ መርጃዎቻችንን እዚህይመልከቱ።

 

###

 

ስለ  ዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ የሰብዐዊ መብቶች ቢሮ

 

የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የሰብዐዊ መብቶች ቢሮ (OHR) የተቋቋመው አድልዎን ለማጥፋት፣ እኩል እድልን ለመጨመር እና በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ለሚኖሩ፣ ለሚሰሩ ወይም ለሚጎበኙ ሰዎች ሰብዐዊ መብቶችን ለመጠበቅ ነበር። ድርጅቱ አድልዎ ደርሶብናል ብለው ለሚያምኑ ሰዎች ህጋዊ ሂደት በማቅረብ የዲሲ የሰብዓዊ መብቶች ህግ ጨምሮ የአካባቢ እና የፌደራል የሰብዐዊ መብት ህጎችን ያስፈጽማል። እንዲሁም OHR በዳይሬክተሮች ጥያቄዎች አማካኝነት በዲስትሪክቱ ውስጥ ሰብዓዊ መብቶችን በትጋት ያስከብራል፣ ይህም አድሎአዊ ሊሆኑ የሚችሉ አሰራሮችን እና ፖሊሲዎችን ለመለየት እና ለመመርመር ያስችለዋል።