የOHR የበዓል መጽሄት - የዳይሬክተሩ መልዕክት
ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እና ጓደኞች፦
ወደ 2024 ፍጻሜ ስንቃረብ፣ እያንዳንዳችሁ አመቱን በሙሉ ያሳያችሁትን የጋራ ጥንካሬ፣ መሰጠት እና የማያወላውል ቁርጠኝነት አስታውሳለሁ። ኖቬምበር እና ዲሴምበር በጥልቀት ለማሰብ፣ ለምስጋና እና ለክብረ በዓል ጊዜዎችን ይሰጣሉ - የደረስንበትን እድገት እውቅና የምንሰጥበት እና ወደፊት ባለው ስራ ላይ እይታዎቻችንን የምናሰናዳበት ጊዜ ነው።
በዚህ ወቅት፣ በመላው ዲስትሪክት ሰብዓዊ መብቶችን፣ ፍትሃዊነትን እና አካታችነትን በማሳደግ ረገድ የአንድ አመት የስራ ክንውኖቻችንን እናከብራለን። ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ የማህበረሰብ ሽርክናዎች እና ትምህርታዊ ፕሮግራሞች ጀምሮ የጸረ መድልዎ ህጎችን በንቃት እስከማስፈጸም ድረስ ድርጅታችን ለፍትህ እና ለድጋፍ ምልክት ሆኖ ቆሟል። እነዚህ ወሳኝ ጊዜዎች የቡድናችንን እና የአጋሮቻችንን የትብብር መንፈስ እና ያልተቆጠቡ ጥረቶች ያሳያሉ። በተለይም፣ ከማህበረሰብ ተሟጋቾች፣ ከንግድ ስራዎች እና ከሀገር በቀል ድርጅቶች ጋር ያለን ጠንካራ አጋርነቶች እንዲሁም የተለያዩ ቁልፍ ውጥኖች እድገት በተለይ በዚህ አመት ተጋላጭ ማህበረሰቦችን በማብቃት ረገድ ትርጉም ያለው ነበር።
የበለጸገውን ታሪክ፣ ባህል እና የአገሩ ተወላጅ ማህበረሰቦችን አስተዋጾ በማክበር የአሜሪካ ተወላጆች ቅርስ ወርን በኖቬምበር እንመለከታለን። ይህ ጊዜ ባህሎቻቸውን፣ ቋንቋዎቻቸውን እና ታሪኮቻቸውን የሚያከብሩበት እድል ሲሆን ይህም ቅርሶች ለቀጣይ ትውልዶች መስፋፋታቸውን ያረጋግጣል። በዚህ የኖኔምበር ወር እና አመቱን በሙሉ፣ የአሜሪካ ተወላጆች እና የአላስካ ተወላጆች ማህበረሰቦች የሃገራችንን ማንነት እና እሴቶች እንዴት እንዳዳበሩ እናውቃለን።
ዲሴምበር የበዓል ወቀት ልባዊ ስሜት የሚያመጣ ሲሆን፣ የርህራሄ እና የአንድነት መንፈስን ያጎለብታል። ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር እንደገና የምንገናኝበት እና አካታች ማህበረሰብ ለመገንባት ያለንን ቁርጠኝነት የምናድስበት ጊዜ ነው። እንዲሁም ዲሴምበር ብሄራዊ የሰብዓዊ መብቶች ሲሆን በዚህ የሰብዓዊ መብቶች ቀን፣ ዲሴምበር 10፣ 2024፣ ሰብዓዊ መብቶች ለመፍትሄዎች፣ እንደ መከላከያ፣ ተከላካይ እና ለበጎ ነገር የለውጥ ሃይሎች ሆነው ለማገልገል በጣም አስፈላጊ መንገዶች መሆናቸውን በድጋሚ እናረጋግጣለን።
ሰብዓዊ መብቶችን የመጠበቅ እና የማስተዋወቅ ስራችን ቀጣይነት ያለው ሲሆን ለምታደርጉት የማያወላውል ድጋፍ ከልቤ አመሰግናለሁ። የዲሲ የሰብዓዊ መብቶች ህግ የሁሉም ሰው አካታችነትን እና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ 23 ባህሪያትን በመጠበቅ የጸረ መድልዎ ጥበቃዎችን ለስፋት ያለንን የማያወላውል ቁርጠኝነት ያሳያል። የእርስዎ መሰጠት ትርጉም ያለው እድገትን የሚደግፍ ሲሆን ለሁሉም የዋሽንግተን ነዋሪዎች የበለጠ አካታች እና ፍትሃዊ የወደፊት ህይወትን ያነሳሳል። የማህበረሰባችንን ግንኙነቶች ለማጠናከር፣ ግለሰቦችን ስለ መብቶቻቸው እና ጥበቃዎቻቸው ለማስተማር ጥረቶችን ለማስፋት እና በ2025 የጋራ ተልኳችንን የበለጠ የሚያሻሽሉ አስደሳች ውጥኖችን ለማሳየት ተስፋ አደርጋለሁ።
የ OHR ወሳኝ ስራ እና ጥረቶች አካል በመሆንዎ እናመሰግናለን። አስደሳች የበዓል ወቅት እና ለ2025 በተስፋ የተሞላ ጅምር እንዲኖርዎት ለእርስዎ እና ለቤተሰብዎ እመኛለሁ!
በአንድነት፣
ኬነዝ ሳውንደርስ