Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

To find support and resources for federal workers, visit fedsupport.dc.gov.

-A +A
Bookmark and Share

የዲሲ ሰባዊ መብቶች ቢሮ (OHR) የኤፕሪል ወር( April ) የዜና መጽሄት (Newsletter) – የዲሬክተሩ መልእክት

Tuesday, April 22, 2025

የተወደዳችሁ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እና ጓዶች፤

የሚያዝያ ወር (April) የተልእኮአችንን ዋና ዓላማዎችን የምናስታውስበት፣ የምናከብርበትና ከተልእኮችን በመነሳት ላደረግናቸው እርምጃዎች እውቅና የምንሰጥበት ወር ነው። እያንዳንዱ የምናከብረው በዓል በማህበረሰባችን ውስጥ አንዱ ከሌላው ሳይለይ ነዋሪነታቸው ወይም ተቀማጭነታቸው ዲስ የሆኑትን በሙሉ በእኩልነት የሚያይ ህብረተሰብ ለመፍጠር የምናደርገውን ጥረት አጉልቶ ያሳያል።

በዚህ ወር ላይ ከምናከብራቸው በዓላት አንዱና እጅግ አስፈላጊ የሆነው የዲሲ የቋንቋ ተደራሽነት ወር (DC Language Access Month) በዓል ሲሆን ይህ በዓል እንግሊዘኛ ቋንቋ የማይችሉ ወይንም እንግሊዘኛ ቋንቋ አነስተኛ ዕውቀት ያላቸውን፤ ሌሎች ያገኙትን ዕድል በእኩልነት እንዲያገኙ የምናደርገውን ጥረት በበለጠ የሚያረጋግጥ ነው። ይህ ኤእአ በ2004 የወጣው የዲሲ የቋንቋ ተደራሽነት ወር ህግ (DC Language Access Act of 2004) መንግስት የሚሰጣቸው መስረታዊ አገልግሎቶች በቋንቋ እጥረት ምክንያት ለሁሉም እንዳይደርሱ የሚያደርገውን ዕንቅፋት የሚያስወግድ ነው።

ሮዛ ካሪዮ (Rosa Carrillo)፤ የዲሲ ሰባዊ መብቶች ቢሮ  የቋንቋ ተደራሽነት ፕሮግራም (Language Access Program) ዲሬክተር፤ “በቋንቋ እጥረት ምክንያት የሚነሱ እንቅፋቶችን ለማስወገድና ቀደም ሲል በቋንቋ እጥረት ምክንያት ከማህበረሰብ ተነጥለው የነበሩትን ሁሉ  ለማቀፍ አስፈላጊውን ጥረት እያደረገች ባለች ከተማ ውስጥ በመሆናችን ኩራት ሊሰማን ይገባል” እያደረገች ብለዋል። የሳቸው ቡድን በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ የሚገኙት  የመንግስት ተቋማት የሚሰጡት አገልግሎት በሙሉ ለሁሉም ነዋሪነታቸው ወይም ተቀማጭነታቸው ዋሽንግተን ዲሲ  የሆኑትን በሙሉ በእኩልነት እንዲያቀርቡ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት በመካሄድ ላይ መሆኑን በማሳየት ባለፈው ዓመት ከማህበረሰብ አባላት፡ ለእኩልነት ከቆሙ ሁሉና ከመንግስታዊ ተቋሞች ጋር የህጉን 20ኛ ዓመት በዓል አክብረዋል።

መኖርያ ቤት ማግኘት መሰረታዊ የሆነ ሰብዓዊ መብት ነው። በዚህ በኤፕሪል ወርም ኦ-ኤች-አር (OHR)፤ የተመሰረተውን ዲሲ ፌይር ሃውሲንግ ፍራይዴይ (#DCFairHousingFridays) በመባል የሚታወቀውን ድርጅት ህልውና በከፍተኛ ደስታ እያስተዋወቀ በዲሲ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ተቋሞች ጋር በመተባበር፤ የዲሲ ፍትሃዊ የመኖርያ ቤቶች (Fair Housing Month)ን ወር ለማክበር በቅቷል። በኤፕሪል ወር ውስጥ ባለው በየሳምንቱ አርብ አርብ በተለያዩ ተቋሞች የሚገኙ የመኖርያ ቤቶች ባለሙያዎች ለምሳሌ በቤቶችና የማህበረሰብ እድገት ዲፓርትመንት ( Department of Housing and Community Development) እንዲሁም በአካል ጉዳትና መብቶች መስርያ ቤት(Office of Disability Rights) ውስጥ ያሉ ባለሞያዎች ትምህርታዊ ምንጮችን እንዴት እንደሚያገኙ፤ ፍትሃዊ ቤት የማግኘት መብቶች ህግን በተመለከተ ምክር በመስጠት እና ተቀማጮች በዚህ በዲሲ ሰብዓዊ መብቶች ህግ (DC Human Rights Act) ስር ደህንነታቸው እንዴት እንደሚጠበቅ ገለጻዎችን ይሰጣሉ። ኦ-ኤች-አር (OHR)፤ የዲሲ ተቀማጮች ካለ ምንም አድልዎ ቤት የመከራየትም ሆነ ቤት የመግዛት ዕድል እንዲያገኙ ጠንካራ ትምህርት በመስጠት የሚያደርገውን ጥረት ይቀጥላል።

ባን ዘ ቦክስ አክት (Ban-the-Box Act) በመባልም የሚታወቀው ፍትሃዊ  የወንጀል መዛግብት የመመርመር ህግ በመተላለፉ ኦ-ኤች-አር (OHR) ህጉ በደንብ በስራ ላይ እንዲተርጎምና ከእስር የተለቀቁ ዜጎች ወደ ተለመደ ኑሮ እንዴት ሊመለሱ እንደሚችሉ ድጋፍ በመስጠት ካለ እረፍት ሲሰራ ቆይቷል። ፌይር ቻንስ ኢኒሸቲቨ (Fair Chance Initiative) በሚባለው ህግ መሰረት፤ የከንቲባዋ ጽህፈት ቤት ወደ ማህበረሰቡ ተመላሽ የሆኑ ዜጎች ጉዳይ (Mayor’s Office on Returning Citizen Affairs (MORCA) እንደመሳሰሉት ባለድርሻ አካላት (stakeholders) ጋር በመተባበር ወደማህበርሰብ ለመመለስ ያሉትን እንቅፋቶችንና አሉታዊ አስተሳሰቦችን ለማስወገድ ሲሰራ ቆይቷል። ‘ሰከንድ ቻንስ መንዝ’ በመባል የሚታወቀው (Second Chance Month)በዚህ ጉዳይ ላይ ተስፋ ሰጪና አንጸባራቂ በመሆኑ፤ ይህ ስራችን በኤፕሪል  ወር ብቻ ሳይተኩር ከሚያዝያ ወር ውጪ ባሉት ሌሎች ወራትም ወደ ማህበረሰቡ የሚመለሱ ዜጎቻችን በህይወታቸው ሰኬታማ ለመሆን እንዲችሉ የእርዳታ ምንጮችንና  እርዳታ እንዲያገኙ በትኩረት መስራታችንን እንቀጥላለን።

ከዚህ ወር በተጨማሪ መስማት ፍጹም የማይችሉና የመስማት ችግር ያለባቸው ሰዎች ያደረጉትን እድገት በማክበርና ላስገኟቸው የተደራሽ መብቶች እውቅና በመስጠት “ብሔራዊ መስማት የተሳናቸው ሰዎች ታሪክ ወር” (National Deaf History Month)ንም በማክበር ላይ እንገኛለን። ኦ-ኤች-አር (OHR) የመስማት ችግር ያለባቸው የዲሲ ተቀማጮች ሲኒማ ቤት ሲገቡ ተዋንያዎቹ የሚናገሩትን መስማት የተሳናቸው ትያትር ቤቶች ተዋንያዎቹ የሚናገሩት በጽሁፍ ተቀርጾ እንዲገባ (captioning)የሚያዘው ህግ ( the DC Open Movie Captioning Requirement Amendment Act  እንዲጠናከር በመስራት ላይ ይገኛል። ለመብት ጠበቃ ከቆሙ ቡድኖች፣ በከንቲባዋ ዋጽ ቤት ከሚገኙት መስማት የተሳናቸው መስማት የተሳናቸው  ዓይነስውር የሆኑ እንዲሁም የመስማት ችግር ያለባቸው ሰዎች ቢሮ (MODDH) ጋር በመተባበር ለብዙ አስፈላጊ ነገሮች ተደራሽነት እንዲኖራቸው በመስራት ላይ ይገኛል።

የኤፕሪል ወር (April) በዓል የማክበር ወር ብቻ አይደለም። እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ የሚቀርበበት ወርም ነው። እነኚህ በዓላት ምን ያህል መልካም ስራ እንደተሰራ የሚያስታውሱንና ወደፊትም አጠናክረን እንድንቀጥልበት የሚጋብዙን ናቸው። ስልጠና ትምህርት ለማግኘትና በመላው ዲሲ አዎንታዊ ለውጦችን ማምጣት በተለያዩ ጉዳዮችና ውይይቶች ላይ ለመካፈል የዲሲ ሰባዊ መብቶች ቢሮን (OHR) ይቀላቀሉ። ማህበረሰቦችንን እናክብር፣ በመላው ዲሲ ገና በመከናውን ላይ ላሉ አዎንታዊ ጉዳዮች እውቅና እንስጥ!