የኦኤችአር ኦክቶበር ውር ወርሃዊ ዜና መጽሄት- የዳይሬክተሩ መልእክት
ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እና ወዳጆች፡-
የዲሲ የሰባዊ መብቶች ቢሮ (OHR) ኦክቶበር የነበሩ ስኬቶችንና ስራዎችን ወደኋላ ዞር ብሎ የመቃኛና አዲስ አስተሳሰብ ብቅ የሚልበት ጊዜ ነው። ባለፈው የበጀት ዓመት የተገኙ ስኬቶችንና እድገቶችን መለስ ብለን በመመልከት ያንን የእድገት ጅምር አዲስ እቅድ ለማሳካት እንጠቀምበታለን፣ ይህም የበለጠ ተጽዕኖ ለመፍጠር ባለን ቁርጠኝነት ላይ የተመሠረተ ነው።
ኦክቶበር የአዲሱን የበጀት ዓመት መጀመሪያ ከማስመዝገብ በተጨማሪ ሁለት አስፈላጊ በዓላትን ስለምናከብር ለቢሮአችን ልዩ ጠቀሜታ አለው፤ እነሱም ብሔራዊ የአካል ጉዳተኝነት ግንዛቤ ወር እና ብሔራዊ የጉልበተኝነትን መከላከል ወር ናቸው።
ብሔራዊ የአካል ጉዳተኞች የሥራ ግንዛቤ ወር (NDEAM) የአእምሮ ጤና ችግር ያለባቸውን እና ሌሎች ያልተለመዱ የአካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ለሥራ ቦታዎቻችን እና ለኢኮኖሚያችን ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ያከብራል። ሁሉም ሰው ሊበለጽግበት የሚችልበት ሁሉን አቀፍ እና ተደራሽ የሆኑ ቦታዎችን የመፍጠርን አስፈላጊነት ለማስታወስ ያገለግላል።
ብሔራዊ የጉልበተኝነት መከላከያ ወር የወጣቶች ጉልበተኝነትን ለመከላከል እና ደግነትን፣ ተቀባይነትን እና ተሳትፎን ለማሳደግ በመላ አገሪቱ የሚካሄድ ዘመቻ ነው። በተለይም በዲስትሪክቱ ውስጥ ከ2013 ጀምሮ ትርጉም ያለው ተጽዕኖ እያሳደረ ባለውየየዲሲ የሰባዊ መብቶች ቢሮ (OHR) የወጣቶች ጉልበተኝነት መከላከያ ፕሮግራም እኮራለሁ። የፕሮግራሙ ተልዕኮ ወጣቶችን፣ ቤተሰቦችን እና አስተማሪዎችን በትምህርት፣ በተሟጋችነት እና ተደራሽ በሆኑ የሪፖርት ማድረጊያ መሳሪያዎች ጉልበተኝነትን ለመከላከል እና ለመቀነስ ማብቃት ነው።
በዲስትሪክቱ ውስጥ የጉልበተኝነት ስጋቶች እንዴት እንደሚፈቱ በተሻለ ሁኔታ ለማቃለል የዲሲ የሰባዊ መብቶች ቢሮ (OHR) አዲስ የቅሬታ መጠይቅ ጀምሯል። አዲሱ ቅጽ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው ወይም ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ወክሎ ወላጅ ወይም አሳዳጊ በዲስትሪክቱ በሚደገፍ የወጣቶች አገልግሎት ሰጪ አካል ላይ መደበኛ ቅሬታዎችን እንዲያቀርብ ያስችለዋል፣ ይህም በዲስትሪክቱ በሚደገፍ የ2012 የወጣቶች ጉልበተኝነት መከላከያ ህግ ("ህጉን") በተሳሳተ አያያዝ፣ በአቤቱታ አቅራቢዎች ላይ በቀል ወይም አስፈላጊ ሂደቶችን ባለመከተል ሊሆን ይችላል።
ይህንን አዲስ የበጀት ዓመት ስንጀምር፣ ለማዳመጥ፣ ለመማር፣ ለመገኘት እና ከማህበረሰባችን ጋር ለመስራት ያለንን በከፍተኛ ቁርጠኝነት እናረጋግጣለን። ከኛጋር ያለዎትን ግንኙነት አጠናክረው እንዲቀጥሉ እንጋብዝዎታለን - ወደፊት በምናዘጋጃቸው የስልጠናዎች እና አውደ ጥናቶች ላይ ይሳተፉ ወይም እርስዎ ባሉበት ቦታ እንዴት መድረስ እንደምንችል ያሳውቁን። አብረን በጋር የዲሲ ክብሯን እና እሴቶቿን የሚያንፀባርቅ እና ለሁሉም ሰው እድል የምትፈጥር ከተማ መገንባታችንን እንቀጥላለን።
በህብረት
ኤሊዛቤት ፎክስ-ሰለሞን (Elizabeth Fox-Solomon)

