ወደዚህ ክፍል ይለፉ:
በቋንቋ አገልግሎት ማግኘት ፕሮግራም ምንድን ነው? • በቋንቋ አገልግሎት ማግኘት ድንጋጌ ስር ያሉኝ መብቶች ምንድን ናቸው? • የቋንቋ እገዛ እንዴት መጠየቅ እችላለሁ? • የራሴን አስተርጓሚ መጠቀም እችላለሁ? • በቋንቋ አገልግሎት ማግኘት መብቶቼ ቢጣሱ ምን ማድረግ ይገባኛል? • የበለጠ የት መማር እችላለሁ?
በቋንቋ አገልግሎት ማግኘት ፕሮግራም ምንድን ነው?
ምንም ዓይነት ቋንቋ ቢናገሩ፣ ከዲሲ መንግሥት መረጃዎችን እና አገልግሎቶችን የማግኘት መብት አለዎት። በቋንቋ አገልግሎት ማግኘት ፕሮግራም ውስን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ለሚናገሩ ወይም ምንም የእንግሊዝኛ የቋንቋ ተንጋሪ ላልሆኑ (LEP/NEP) ነዋሪዎች፣ ሠራተኞች እና ጎብኚዎች ይህንን መብት እውን ለማድረግ ከዲስትሪክቱ ድርጅቶች ጋር ይሠራል። በ2004 የተቋቋመው በቋንቋ አገልግሎት ማግኘት ድንጋጌ ፕሮግራም በዲሲ የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ ሥር የተቋቋመ ነው።
በቋንቋ አገልግሎት የማግኘት ድንጋጌ ስር ያሉኝ መብቶች ምንድን ናቸው?
የ2004 በቋንቋ አገልግሎት ማግኘት ድንጋጌ፣ ሁሉም የዲሲ መንግሥት ድርጅቶች፣ መምሪያዎች፣ ፕሮግራሞች፣ ውል ተወያዮች እና እርዳታ ተቀባዮች ካለምንም ክፍያ የሚከተሉትን አገልግሎቶችን እንዲሰጡዎት ይጠይቃል፣
- ትርጉም (በቋንቋዎ የጽሁፍ መረጃዎችን)
- ማስተርጎም (በቋንቋዎ ማስተርጎም)
- ማስታወቂያ (በቋንቋዎ መረጃዎችን መለጠፍ)
የ2004 የዲሲ በቋንቋ አገልግሎት ማግኘት ድንጋጌን ያንቡ።
ትርጉም
የዲሲ መንግሥት ማንኛውንም ማወቅ የሚገባዎትን ወይም ለአገልግሎቶችና ፕሮግራሞች ለማመልከት የሚያስፈልጉዎትን የጽሁፍ ሰነዶችን እንዲተረጎም ይጠየቃል። እንደ የድርጅቱ ሁኔታ፣ ይህ መረጃ፤ ማመልከቻዎችን፣ ማስታወቂያዎችን፣ የስምምነት ፎርሞችን እና በህትመት እና በኤሌክትሮኒክ የተጻፉ ደብዳቤዎችን እና ሌሎችንም አስፈላጊ መረጃዎችን ሊጨምር ይችላል።
ማስተርጎም
ከዲሲ መንግሥት ጋር በግንባር ወይም በስልክ ሲነጋገሩ፣ ድርጅቱ ቋንቋዎን የሚናገር የሰለጠነ አስተርጓሚ እንዲያቀርብ ይጠየቃል። አስተርጓሚው፣ ሁለት ቋንቋ ተናጋሪ የሥራ ባልደረባ፣ በግንባር የሚቀርብ በሙያው የሰለጠነ አስተርጓሚ ወይም በሙያው የሰለጠነ በስልክ አስተርጓሚ ሊሆን ይችላል። የዲስትሪክቱ ሠራተኞች በመጀመሪያው ግንኙነት አስተርጓሚ ያቀርባሉ፣ እርስዎ ግን በማንኛውም ጊዜ አስተርጓሚ እንዲቀርብልዎ ሊጠይቁ ይችላሉ።
ማስታወቂያ
ሁሉም የዲሲ ድርጅቶች የደንበኛ ማስተናገጃ ቦታዎች፣ መምሪያዎች፣ ፕሮግራሞች፣ ውል ተዋዋዮች እና እርዳታ ተቀባዮች፣የትርጉም እና የተተረጎሙ ሰነዶችችን የማግኘት መብትዎን የሚገልጹ ማስታወቂያ ምልክቶች መለጠፍ አለባቸው። ማንኛውንም የዲስትሪክቱን ድርጅት ሲጎበኙ፣ በተለያዩ ቋንቋዎች የቋንቋ እርዳታ መጠየቅ እንደሚቻል የሚያስረዱ፣ መመሪያ ምልክቶችን ጨምሮ የሚያሳዩ የቋንቋ መለያ ካርድ ወይም የቋንቋ መለያ ዴስክቶፕ ማስታወቂያ፣ ምልክቶች ማየት ይገባዎታል።
የቋንቋ መለያ ካርድ
የቋንቋ መለያ ዴስክቶፕ ማስታወቂያ
በቋንቋ እርዳታ እንዴት መጠየቅ እችላለሁ?
የዲስትሪክቱ ሠራተኞች ለማንኛውን አገልግሎት ለሚፈልግ ደንበኛ የማስተርጎም እና የትርጉም አገልግሎትን በስልክም ሆነ በግንባር ለመስጠት ስልጠና ወስደዋል። አስተርጓሚውን ከማግኘታቸው በፊት የመጀመሪያ ቋንቋዎ ምን እንደሆነ ለማወቅ ጥያቄ በመጠየቅ ሉ፣ ወይም የቋንቋ መለያ ካርዱን ወይም ዴስክቶፕ ማስታወቂያውን ይጠቀማሉ።
ከዲስትሪክቱ ሠራተኞች ጋር ምን ቋንቋ እንደሚናገሩ በ“እናገራለሁ” ካርድ ለመነጋገርም ይችላሉ። በዲሲ የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ እነዚህን ካርዶች በኪስ ቦርሳ የሚያዙ፣ በአማርኛ፣ በአረብኛ፣ በቻይኒኛ፣ በፈረንሳይ፣ በኮሪያ፣ ፖርቹጋሊዝ፣ ራሺያን፣ ስፓኒሽ፣ ታጋሎግ እና ቬትናሚስ ቋንቋ የተዘጋጁ ያሰራጫል።
የእራሴን አስተርጓሚ መጠቀም እችላለሁ?
በዲስትሪክቱ የሚቀርቡትን በሙያው የሰለጠኑ አስተርጓሚዎች እንዲጠቀሙ ይመከራሉ። የእራስዎን አስተርጓሚ መጠቀም ከመረጡ ግን፣ መደበኛውን በቋንቋዎ የተጻፈውን የኃላፊነት የማስቀሪያ ስምምነት ቅጽ መፈረም አለብዎት። የማስቀሪያ ቅጹ በቋንቋዎ ከሌለ፣ ዲስትሪክቱ ስለቅጹ ይዘት የሚያስረዳዎ አስተርጓሚ መጠቀም አለበት። እባክዎን ሁሉም አስተርጓሚዎች እድሜያቸው ቢያንስ 18 ዓመት መሆኑን ያስተውሉ።
በቋንቋ አገልግሎት ማግኘት መብቶቼ ቢጣሱ ምን ማድረግ ይገባኛል?
በ2004 በቋንቋ አገልግሎት ማግኘት ድንጋጌ መሰረት፣ የዲሲ መንግሥት ድርጅቶች፣ መምሪያዎች፣ ውል ተዋዋዮች እና እርዳታ ተቀባዮች የእንግሊዘኛ ቋንቋ ባለመናገርዎ ምክንያት አገልግሎታቸውን መከልከል ህጋዊ አይደለም። እርስዎ ወይም ሌላ ሰው አስተርጓሚ ወይም በቋንቋዎ የተተረጎሙ ሰነዶች ከተከለከለ፣ለዲሲ የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ አቤቱታ ለማስገባት ያነጋግሩ፣
- 202-727-4559 ይደውሉ፤
- በኦንላይን አቤቱታ ያስገቡ (በእንግሊዘኛ)፣ ወይም
- የአቤቱታ ቅጽ በአማርኛ ሞልተው በሚከተለው አድራሻ በፖስታ ይላኩት ወይም በግንባር ይስጡ:
District of Columbia Office of Human Rights
Attn: Language Access Program
441 4th Street, N.W., Suite 570 North
Washington, DC 20001
የበለጠ የት መማር እችላለሁ?
ስለ በቋንቋ አገልግሎት ማግኘት ፕሮግራም የበለጠ ለመማር፣ የዲሲ የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ ያነጋግሩ፡
ኢሜል: [email protected]
ስልክ: 202-727-4559
(የስልክ አስተርጓሚ ይቀርብልዎታል)
ስለተወሰነ ድርጅት በቋንቋ አገልግሎት ማግኘት ለማወቅ ከፈለጉ የድርጅቱን የቋንቋ አገልግሎት አስተባባሪው ያነጋግሩ።
የቋንቋ አገልግሎት አስተባባሪውን መረጃዎችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ።