Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

OHR የጃንዋሪ ወሃዊ ጋዜጣ - የዳይሬክተሩ መልእክት

Wednesday, January 29, 2025

ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እና ወዳጆች

መልካም አዲስ አመት!

ጃንዋሪ ሲገባ ለአዲስ ጅማሮ እና እስካሁን ያሳካነውን እድገት ቆም ብለን እንድናይ እንዲሁም ወደፊት ለሚጠበቁት ወሳኝ ስራዎች መሳካት ድጋሚ እድል ይሰጠናል፡፡ የዲሲ የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ (OHR ) ይህንን አዲስ ዓመት ይበልጥ አሳታፊ እና ፍትሃዊ አድርገን ለመቀጠል ያለንን ቁርጠኝነት ለማደስ እንደ መልካም አጋጣሚ አድርገን እንቀበለዋለን።

በ 2024 ከማህበረሰቦች ጋር ተፅእኖ በሚኖረው መልኩ የማህበረሰብ ተደራሽነት መርሃ ግብሮች በዲሲ የሰብአዊ መብት ህግ መሰረት አስፈላጊ የሆኑ ጥበቃዎችን በማስከበር ድረስ ጉልህ ስኬቶችን ስናሳካ ቆይተናል፡፡ እነዚህ ስራዎች የተከናወኑት በቡድናችን የማያወላውል ቁርጠኝነት፣ በማህበረሰብ አጋሮቻችን ትብብር እና በኩራት በምናገለግላቸው ነዋሪዎች እምነት አማካኝነት ነው።

2025ን ስንመለከት በሁሉም ሁኔታዎች ላይ የሚደርሱ መድልዎችን ለመቅረፍ እና በከተማችን ውስጥ የሚገኙትን እያንዳን ግለሰብ በአክብሮት እንዲታ ለማድረግ ባለን ቁርጠኝነት ፀንተን እንገኛለን። ነገር ግን ይህ ስራ ቀጣይነት ያለው እንዲሆን እና ለዘላቂ ለውጥ የመላው ማህበረሰባችንን የጋራ ጥረት የሚጠይቅ መሆኑን እናውቃለን። ተፅዕኖአችንን ለማስፋት የእርሶን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እና ንቁ ተሳትፎ እንፈልጋለን። ማንውም ሰው ማንነንቱ ሳይለይ  የሚገባውን መብቶች እና ጥበቃዎች እንዲያገኝ ማድረግ የምንችለው በጠንካራ አጋርነት እና በጋራ ቁርጠኝነት ብቻ ነው፡፡ ሁላችሁም በዚህ ተልእኮ ከእኛ ጋር በመተባበር፣ በማስተባበርም ሆነ ግንዛቤዎችን በማስፋፋት እንድትሳተፉ እጋብዛችኋለሁ።

በዚህ አመት፣ ስራችንን ተደራሽ የማድረግ ጥረታችንን ለማስፋፋት የዘር ፍትሃዊነት ተነሳሽነትን ለማጎልበት እና ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ህዝቦች የመሟገት ስራችንን ለመቀጠል በጉጉት እየጠበቅን እንገኛለን፡፡ ዲሲ ኦፐን ሞቪ ካፕሽኒንግ (DC Open Movie Captioning ) መስፈርቶች ህግን ከማስከበር ጀምሮ የወጣቶች ስርአተ አልበኝነትን መከላከል ፕሮግራምን እስከመደገፍ እንዲሁም ለሁሉም የፍትህ ተደራሽነትን ከማስፋት ጀምሮ ፍትሃዊ እና ጠንካራ ከተማን የመገንባት የጋራ ራዕያችንን ለማሳካት ቁርጠኞች ነን።

ስለዚህ ይሄንን አመት ከእኛ ጋር በማህበራዊ ሚዲያ፣ በተለያዩ ፕሮግራሞቻችን ላይ ወይም ማህበረሰቦች ስለ ብቶቻቸው ያላቸውን እውቀት እንዲያጎለብቱ በምናቀርባቸውን ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አበረታታለሁ፡፡ በጋራ ለዋሽንግተን ዲሲ ብሩህ የሆነ የወደፊት ተስፋ እንዲፈጠር ማድረግ እንችላለን::

አመቱ በተስፋ፣ በእድገት እና በማህበረሰብ የተሞላ እንዲሆን እመኛለሁ!

 

ህብረት

ኬነዝ ሳውንደርስ

 ዲሬክተር