የተከበራችሁ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች፣ እንዲሁምወዳጆች፦
ወደ ማርች ወር ስንገባ አዲስ ወቅቶችን መቀበል ብቻ ሳይሆን በታሪክ ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍ የሆነውን - የሴቶች ታሪክ ወርን እናከብራለን። ይህ ጉልህ በዓል በየዘመናቱ ለፍትሃዊነት፣ ሁሉን አካታችና እና ለብዛሃነት በመፋለም ውስጥ ፈር ቀዳጅ ለነበሩ ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ሴቶች እውቅና ለመስጠት እና ለማክበር በዝግጅት ላይ ነን።
በመጀመሪያ በሳንታ ሮሳ፣ ካሊፎርኒያ እንደ የአካባቢ በዓል ሆኖ የተመሰረተው የሴቶች ታሪክ ወር በ1978 የሴቶች ታሪክ ሳምንት ሆኖ ተጀመረ። ንቅናቄው በመላ ሀገሪቱ ጎልቶ የወጣ ሲሆን የተለያዩ ማህበረሰቦች እና ክልሎች የየራሳቸውን የሴቶች ታሪክ ሳምንት በዓል በሚቀጥለው አመት ማክበር ጀመሩ። በ 1980፣ የሴቶች ቡድኖች እና የታሪክ ተመራማሪዎች ጥምረት፣ በብሔራዊ የሴቶች ታሪክ ፕሮጀክት መሪነት በተሳካ ሁኔታ ብሔራዊ እውቅና እንዲሰጥ በማለት ተሟግተዋል ። በፌብሯሪ 1980 ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር የማርች 8 ቀን 1980 ሳምንትን እንደ ብሄራዊ የሴቶች ታሪክ ሳምንት በማለት የመጀመሪያውን የፕሬዝዳንት አዋጅ ደንግ ገዋል።
ለሴቶች ድምጽ መስጠት መብት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ከታገሉት መራጮች እስከ የህብረተሰቡን ህግጋት ለተቃወሙ፣ ጣሪያ የሰበሩ እና ፍትሃዊና ለእኩል እድሎች ከሚሟገቱ ደፋር መሪዎች - እንደ ሜሪ ቸርች ቴሬል፣ ሱዛን ቢ. አንቶኒ፣ ሴፕቲማ ፖይንሴት ክላርክ እና ኤላ ቤከር - በታሪክ የነበረችው እያንዳንዷ ሴት በእድገት ጎዳና ላይ የማይረሳ አሻራ ጥለዋል።
ስኬቶቻቸውን ስናሰላስል በማህበራዊ ሚዲያ ቻናሎቻችን በመላው ማርች ወር ውስጥ ለልዩ ልዩ ልምዶቻቸው፣ ባህሎቻቸው እና ስኬቶቻቸው እውቅና በመስጠት ልዩ የሆኑ ሴት መሪዎችን በሰብአዊ መብቶች ቢሮ ውስጥ መግለጽ እና ማስተዋወቅ እፈልጋለሁ። ታሪካቸው፣ ለብዘሃነት እና አካታችነት ማዳበር በጉልህ አስተዋጽኦ በማድረግ፣ ፍትሃዊነትን በጽናት ካረጋገጡ ስፍር ቁጥር ከሌላቸው ሌሎች ሴት ጀግኖች ጋር ያስተጋባል።
ላለፉት ሴቶች እውቅና በመስጠት፣ ለትሩፋታቸው ክብር ከመስጠት ባለፈ የአሁኑም ሆነ መጪው ትውልድ ይበልጥ አሳታፊ እና ፍትሃዊ የሆነ ማህበረሰብን ለማምጣት የሚያደርገውን ጉዞ ለማስቀጠል እንደምናነሳሳ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ ።
በመጨረሻም፣ ወደ ዘጠኝ አመታት የሚጠጋ የህዝብ አገልግሎት ከሰብአዊ መብቶች ቢሮ ጋር ከሰራሁ እና አገልግሎት ከሰጠሁ በኋላ የዲስትሪክቱ ውጭ ወደ ሆነ ሌላ መስሪያ ቤት ልዛወር መሆኑን ላካፍላችሁ እፈልጋለሁ። የዲሲ ነዋሪዎችን ማገልገል ፍጹም ክብር ነበር። በዲስትሪክቱ በነበረኝ ቆይታ በጉዳይ ማስፈጸም ሂደት መሻሻል፣ በሰዎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ፣ እና በሰባዊ መብቶች ቢሮ (OHR) መሠረተ ልማት ግንባታ ላይ አተኩሬ ነበር። በጣም ኩሩ ስኬቶቼ ጥልቅ የአመራር መሰረቶችን ማቋቋም፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የቴክኖሎጂ እና የመረጃ ድጋፍንለኤጀንሲው ማስተዋወቅ፣ ቀጣይነት ያለው የጉዳይ አቀራረብ መጠንን ሂደትን ስኬታማ ማድረግ፣ የህግ ክስ ጥንካሬን ማሳደግ፣ ከፍተኛ የንግድ ስራ ተገዢነትን ማረጋገጥ፣ እና የOHR ጠንካራ የEEO ስልጠና ፕሮግራም ማጠናከርን ያካትታሉ። እንዲሁም፣ የዲስትሪክቱን የተለያዩ ህጎች እና ፖሊሲዎች ለመቅረጽ የሚረዱ እድሎች መፈጠራቸውን ሳላደንቅ አላልፍም። ከምንም በላይ ይህን ስራ እንዲካሄድ ላደረጉት ከንቲባ ሚዩሪየል ቦውዘር፣ የስራ ባልደርቦቼን፣ መንግስታችንን እና የማህበረሰብ አጋሮቻችንን ከልብ አመሰግናለሁ!
ከምስጋና ጋር