Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

መጋቢት 2023 (Amharic)

Tuesday, March 14, 2023

የስራ አስኪያጅ ማስታወሻ- ማርች 2023

 

ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች፣ እንዲሁም ወዳጆች

በ1964፣ ከሌሎች ነገሮች መካከል የሲቪል መብቶች ህግ ርዕስ VII በዘር፣ በቀለም፣ በሃይማኖት፣ በትውልድ ሃገር ና በጾታ ላይ የተመሰረተ የቅጥር አድልዎን ይከለክላል፣ ነገር ግን “ጾታ” በኋላ ላይ እንደ ተጨማሪ ታክሏል። እንደ አለመታደል ሆኖ፣ ከ60 አመታት ገደማ በኋላ፣ ጾታዊ ትንኮሳን ጨምሮ፣ የጾታ መድልዎ፣ በተለይም በስራ ቅጥር እና በተወሰኑ ወንዶች በብዛት በሚገኙባቸው የስራ ዘርፎች አሁንም አለ። 

በ2017፣ የ “እኔም” እንቅስቃሴ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ዘመናዊ እና በማደግ ላይ ያለ እንደነበር በምናስበው ማህበረሰብ ውስጥ የጾታዊ ትንኮሳ መስፋፋትን አጉልቶ አሳይቷል።  በዲስትሪክቱ ውስጥ፣ ማንኛውንም አይነት ጾታዊ ወይም ጾታዊ ትንኮሳ አለመፈጸምን ጨምሮ፣ ሁሉንም ሰው እኩል በሚያስተናግዱ የDC እሴቶቻችን እናምናለን።  በዲሴምበር 2017፣ ከንቲባ ቦውሰር በዲስትሪክቱ መንግስት ውስጥ ትንኮሳን ሪፖርት ለማድረግ ግልጽ አሰራርን ያስቀመጠ እና ምንም አይነት ጾታዊ ትንኮሳ በስራ ቦታ ላይ ፈጽሞ ተቀባይነት እንደሌለው ግልጽ መልዕክት የሚያስተላልፍ፣ አዲስ ይበልጥ ጠንካራ የሆነ የጾታዊ ትንኮሳ ፖሊሲ አውጥተዋል  ፣ በቅርቡበኦክቶበር 2022፣ ዲሲበህጉ ውስጥ ትንኮሳ እና ጾታዊ ትንኮሳ ምን እንደሆነ በመጻፍ ትንኮሳን የሚከለክል የራሳችንን የሆነ የጸረ መድልዎ ህግ እንዲኖር ጉልግ አስተዋጾ አድርጋለች።  እነዚህ አዳዲስ ድንጋጌዎች ስራ ላይ በዋሉበት ወቅት፣ OHR የበለጠ ለማብራራት የማስፈጸሚያ መመሪያን በስራ ላይ ያዋለ መመሪያውን እዚህ ማግኘት ይችላሉ።

ሌላው ማስታወሻ ሴቶች በቅጥር ሂደት ወቅት ተገቢ ያልሆኑ ወይም ህገወጥ ጥያቄዎች ያጋጥሟቸዋል፣  እንዲያውም አንዳንዶች የጋብቻ ቀለበታቸውን ማድረግ ይኖርባቸው እንደሆን እንደገና ያስባሉ።  ፣  የሚከተሉትን መሰል ጥያቄዎች ያካትታሉ፦ 1) ልጆች አሉዎት? ስንት አመታቸው ነው?  ሞግዚት አለዎት? ወይም ምን አይነት የልጅ እንክብካቤ እቅድ አለዎት? 2) አግብተዋል?  ባለቤትዎ/አጋርዎ ምን ይሰራሉ?  የስራ እድሎችን ለመከልከል ወይም ለመገደብ ጥቅም ላይ ከዋሉ ወይም ለሴት አመልካቾች ብቻ የሚቀርብ ከሆነ እነዚህ ጥያቄዎች ተገቢና ህጋዊ ላይሆኑና እና ለጾታዊ መድልዎ የይገባኛል ጥያቄ ሊፈጥሩ ይችላሉ።  በዲሲ የሰብዐዊ መብቶች ህግ መሰረት፣ ከጾታዊ መድልዎ በተጨማሪ፣ ሁለተኛውን የሚመስሉ ጥያቄዎች፣ የስራ እድሎችን ለመከልከል ጥቅም ላይ ከዋሉ፣ እንዲሁም በአንድ ሰው የጋብቻ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ መድልዎ ሊፈጠር ይችላል።

OHR ብዙ የተለያዩ የአካባቢ እና የፌደራል ህጎችን ይጣቅሳል ይወስናል፣ ይከሳል፣ በመሆኑም በዲስትሪክቱ ውስጥ ያለዎትን መብቶች ማወቅዎ አስፈላጊ ነው። የሰብዐዊ መብቶች ህጎችን፣ ደንቦችን፣ እና ፖሊሲዎችንየ OHR ተፈላጊ መረጃ የያዙ መመሪያዎችን እንዲሁም OHR ማስፈጸሚያ መመሪያዎችን በመጎብኘት እራስዎን ከእነዚህ ህጎች ጋር ማስተዋወቅ ይችላሉ፣  ሌሎች የዲስትሪክቱ የመንግስት መርጃዎችበከንቲባዋ የሴቶች የፖሊሲ  እና ኢኒሸቲቨጽህፈት ቤትን ያካትታሉ።  / ቤታችን የሚሰራቸውን ስራዎች በተመለከተ  እዚህ ማግኘትይችላሉ።

ምንም እንኳ ቀጣይ ተግዳሮቶች ቢኖሩም፣ ሴቶች በትጋት ሰተዋል እንዲሁም በብዙ ህብረተሰባችን የአሰራርች ሁኔታዎች ውስጥ ጉልህሚና አላቸው።  በዚህ ወር በሁሉም የመገናኛ ብዙሃን እና ታሪኮችን በመንገር ወይም በመጻፍ ተግባር ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያደረጉ ሴቶችን  በ ዲሲ እንደ ሜሪ ፒ. ቡሪል (1881-1946)፣ አፍሪካዊ አሜሪካዊቷ በሃርለም ህዳሴ ወቅት የቲያትር ጸሃፊ፤ በ DC የአደን ወፎች፣ ባትገርል ላይ በአስቂኝ ስራዎች፣ እና በወንደር ዉማን ላይ ለረጅም ጊዜ የቀጠለች ሴት ጸሃፊ በመሆን በደንብ የምትታወቀው፣ ጌይል ሲሞን፤ የዋሽንግተን ፖስት ዋና አዘጋጅ፣ ሳሊ ቡዝቢ፣ የዋሽንግተን ናሽናል ኦፔራ የጥበብ ባለሙያ ዳይሬክተር፣ ፍራንሴሳ ዛምቤሎ፤ ዘፋኝ፣ ዳንሰኛ፣ እና በብሮድዌይ ኢን ዌስት ሳይድ ታሪክ፣ ቺካጎ እና ኪስ ስፓይደር ዉማን ላይ መሪ ተዋናይ የነበረችው፣ ቺታ ሪቬራ፤ የኦፔራ ዘፋኝ ዴኒስ ግሬቭስ፤ ተዋናዮች ጎልዲ ሃውን፣ ታራጂ ፒ. ሃንሰን፣ ሬጂና ሃል፤ እና እንደ ሞሪን ቡንያን፣ ሬኔ ፑሴይንት፣ ጂሲ ሃይዋርድ፣ እና የአካባቢውን ቴሌቪዥን የቀየረችው ሜሪል ኮሜር ያሉ ፈር ቀዳጅ ሴቶችን ታሪክ እንዘክራለን።

ዘወትር እርስዎን ለማገልገል ዝግጁ ነን፣