ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እና ጓደኞች፣
ምንም እንኳን ሁላችንም ከበዓላት በኋላ ወደ ሥራ መመለስን የምንፈራ ቢሆንም፣ ጃንዋሪ ለእያንዳንዳችን እንደገና ለመጀመር፣ ድጋሜ ለመጠናከር፣ እንዲሁም ለራሳችን፣ ለማህበረሰባችን እና ለኛ አስፈላጊ ለሆኑት አላማዋችን ዳግም ቁርጠኝነት ለማቅረብ ሌላ እድል ትፈጥርልናለች። ለሰብአዊ እና ህዝባዊ መብቶች፣ እና በሰፊው ለመደመር እና ለፍትሃዊነት የሚደረገው ትግል፣ የአይምሮ፣ የአካል፣ እና የስሜት ጉዳት ልያደርስብን ይችላል። የዶ/ር ኪንግን ስራ እንድንቀጥል ለማስቻል፣ በዚህ አመት ለጤናችን ቅድሚያ መስጠት ቀዳሚ ስራችን ሊሆን ይገባል።
ዶ/ር ኪንግ ከመሞታቸው በፊት፣ የተለያዩ ድህረ-ታሪክ ላላቸው ድሆች እና ላብ-አደር አሜሪካውያን የመኖሪያ ቤት፣ የስራ እና የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ጥብቅና ለመቆም የድሆችን ዘመቻ አደራጅቷል። ምንም እንኳን እሳቸው በተለምዶ አፍሪካን- አሜሪካውያንን በመወከል ለዘር እኩልነት ከመታገል ጋር የተያያዙ ቢሆኑም፣ በህይወታቸው መጨረሻ ገደማ፣ ኪንግ ሁሉም ሰዎች በሕይወት ለመትረፍ የሚያስፈልጋቸውን ነገር እንዲኖራቸው አስፈላጊ መሆኑን ተገንዝቧል። ቃላቶቻው አሁንም ቢሆን በእ.ኤ.አ. በ1967 የነበራቸው አስፈላጊነት እንደጠበቁ ናቸው፦ “አሁን የምሳ ቆጣሪን ለማዋሃድ እየታገልን አይደለም። ቆጣሪው ላይ ስንደርስ ሃምበርገር ወይም ስቴክ ለመግዛት የሚያስችለን የተወሰነ ገንዘብ ለማግኘት እየታገልን ነው።” ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የኑሮ ውድነት፣ ስራ አጥነት፣ ቤት እጦት፣ ወዘተ በዲስትሪክቱ እና በመላው ሀገሪቱ ወሳኝ ጉዳዮች ሆነው ቀጥለዋል።
በጃንዋሪ 16 (የማርቲን ሉተር ኪንግ ጁንዬር አገልግሎት ቀን) የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት በመስጠት፣ የዶ/ር ኪንግ ህይወት እና ውርስ ማክበር እና ለማህበረሰቦቻችን መልሰን መስጠት እንችላለን። አድልዎ ለማጥፋት፣ ጭፍን ጥላቻን ለመቀነስ፣ እና ግንዛቤን ለመጨመር በመሥራት ዓመቱን በሙሉ ሊያከብሩት ይችላሉ።
ደስተኛ፣ ጤናማ እና የብልጽግና አዲስ ዓመት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
መልካሙን ሁሉ እመኝልዎታለው፣
Hnin Khaing
ተጠባባቂ ዳይሬክተር