የዲሲ የሰብ አዊ መብቶች ጽህፈት ቤት (DC Office of Human Rights) ጥራዝ (Volume) XXXVVI | ሚያዝያ (April) 2022
የኤፕሪል (April) የቋንቋ የቋንቋ ተደራሽነት ወር ነው !
ይህንን የቋንቋ የቋንቋ ተደራሽነት ወር የሚባለውን የኤፕሪል ወር በጋራ አብራችሁኝ በማክበር ላይ ስለሆናችሁ አመስግናለሁ። ይህ የቋንቋ ተደራሽነት ህግ (Language Access Act (ኤል-ኤ-ኤ LAA) የተደነገገው ኤፕሪል 21 ቀን 2004 ነው። በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምብያ ውስጥ ይህ ህግ ገና ሲደነገግና በቋንቋ ተደራሽነት ዙሪያ ያስከተለውን አጀማመርና የረጅም ጊዜ አዎንታዊ ተጽዕኖ እውን መሆኑን ለመመስከር በመብቃቴ ዕድለኛ ነኝ። ይህ ህግ በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ከወጡት ፍትሃዊና አቀፍ ህጎች ውስጥ አንዱ ሲሆን፤ ከንቲባ ባውዘር (Mayor Bowser) አንድ ህብረ ብሄራዊ፣ ፍትሃዊ ና አካታች አስተዳደር ለመገንባት የሚያደርጉት ጥረት አንድ የስራ ሂደት አካል ነው። ይሄውም የተወሰነ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ያላቸው (ኤል-ኢ-ፒ LEP) እና ምንም የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ የሌላቸው (NEP) የዲስትሪክቱ ነዋሪዎች ከመንግስት ጋር ለሚኖራቸው ግንኙነት ድልድይ በመሆን የሚያገለግል ህይወት የሚለውጥ እንዲሁም እኩል ተሳታፊነት እንዲኖራቸው የሚያስችል የመንግስት አገልግሎት ነው።
ይህ የኦ-ኤች-አር (OHR) የቋንቋ ተደራሽነት ፕሮግራም፤ በግለሰቦችና በዲሲ መንግስት፤ አነስተኛ ውክልና ያላቸውን (ኤል-ኢ-ፒ LEP) እና (ኤን-ኢ-ፒ-NEP) የዲሲ ነዋሪዎችን ለመርዳት በሚደረገው ጥረት፤ ግንባር ቀደም በመሆን ሲያገለግል ቆይቷል።
የኦኦኤች አር የቋንቋ ተደራሽነት ፕሮግራም በተገልጋዩ ማህበረሰብና በመንግስት መካከል ግንባር ቀደም ድልድይ በመሆን የማህበረሰብ ክፍል ፍላጎት በማሟላት ድጋፍ እየሰጠ ይገኛል። ይህ ፕሮግራም የዲሲ ነዋሪዎች፣ ሰራተኞችና ጎብኝዎች ምንም ቋንቋ ይናገሩ ማንኛውንም ከዲሲ መንግስት ማግኘት የሚገባቸውን መረጃ ያለምንም ችግር እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። የዚህ ፕሮግራም ዳራ ከህዝብ ጋር የሚያገናኛቸው በዲስትሪክቱ የሚገኙ ልዩ ልዩ መስሪያ ቤቶች፣ እንዲሁም ለነኝህ መስሪያ ቤቶች መልካም ተሞክሮዎች፣ እንዲሁም የመንግስት መስሪያ ቤቶች አገልግሎቶቻቸውን የተወሰነ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ላላቸው (ኤል፡ኢ፡ፒ LEP) እና ምንም የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ለሌላቸው (ኤን፡ኢ፡ፒ NEP) የዲስትሪክቱ ነዋሪዎች በተሻለ መልኩ እንዲሰጡ የሚያግዝ የጽሁፍና የትርጉም የተክኒክ እገዛ የሰጣል።
ይሄው ፕሮግራም የዲሲ ነዋሪዎች፣ ሰራተኞችና ጎብኚዎች፤ ማንኛውንም ቋንቋ ይናገሩ፤ ከዲሲ መንግስት ሁሉም ሰው የሚያገኘውን መረጃና አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችል ፕሮግራም ነው። ይህ ፕሮግራም ከህዝብ ጋር ግንኙነት ያላቸው በዲስትሪክቱ ውስጥ የሚገኙ ተቋማት በሙሉ ለሚያገለግሉት የእንግሊዝኛ ቋንቋን በተመለከተ የተወሰነ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ላላቸው (ኤል፡ኢ፡ፒ LEP) እና ምንም የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ለሌላቸው (ኤን፡ኢ፡ፒ NEP) የህብረተሰብ ክፍል የጽሁፍና የቃል ትርጉም ማበረከት እንዲችሉ አስፈላጊውን የቴክኒክና የትምህርት ድጋፍ ያደርግላቸዋል። ይህ የቋንቋ አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኘነትና የምናደርገው ያላሰለሰ ድጋፍ የቋንቋ አቀራረብ ዕቅዶች እንዲጎለብቱ፡ ስለዚህ ጉዳይ ያለው እውቅና እንዲሻሻልና በቋንቋ ምክንያት ድምጻቸውን ማሰማት ለማይችሉ ወገኖች ድምጽ የሚሆን ሰብኣዊ መብት መሆኑን፤ በከተማችን ላይ ህይወት በመዝራት ላይ ባለው ማህበረሰብ ውስጥ ንቃት ፈጥሯል።
ከሰላምታ ጋር
ሮዛ ካሪሎ
የቋንቋ ተደራሽነት ፕሮግራም ዲሬክተር
የ 2021 የቋንቋ ተደራሽነት ኮምፕሊያንስ ሪቪው (Language Access Compliance Review)
ከታች በ2021 የቋንቋ ተደራሽነት የአሃዝ ከለሳን ወይም ግምገማን በተመለከተ የሚወጣው አጭር ዝርዝር ምን እንደሚመስል ያመለከታል። ይሄው በአሃዝ የተደገፈ አጭር የቋንቋ ተደራሽነት ፕሮግራም ዝርዝር በ 2021 የዲሲ ነዋሪዎች፤ ሰራተኞችና ጎብኚዎች ምን ያህል ጠቀሜታ እንዳገኙ በግልጽ ያሳያል።
የዲስትሪክቱ ተቋሞች የቋንቋ ተደራሽነትን በተመለከተ የሰሩት ስራ
ይህንን የቋንቋ ተደራሽነት ወርን በተመለከተ ማክበር የምንፈልገው፤ በዲስትሪክቱ ያሉት ተቋሞች ምን ያህል ከፍተኛ ስራ እንደሰሩ ትኩረት በመስጠት ነው። የበለጠ ለመረዳት ከታች ያለውን አንብቡ።
የእርጅና እና የማህበረሰብ ኑሮ መምሪያ (ዲፓርትመንት ኦፍ ኤጂንግ ኤንድ ኮሙኒቲ ሊቪንግ (DACL))
የሲኒየር ፔት ኮኔክት የስፓንኛ ቋንቋ ስብሰባ
በሜይ 11, 2021፣ የDACL፣ HRA ሰራተኞች፣ እና በግምት 20 የሚሆኑ የቪዳ አረጋውያን (ቪዳ ሲኒየርስ) የዙም መድረክ በመጠቀም ቨርቿል የሲኒየር ፔት ኮኔክት ዝግጅት ላይ ተሳትፈዋል። ይህ ዝግጅት በስፓንኛ-ተናጋሪ HRA ሰራተኞች በስፓንኛ ነው የተደረገው እና ቪዳ ሲኒየርስ'ን እንደ ውሾች፣ ድመቶች፣ እና ዶሮዎች ላሉ ለተለያዩ የጓደኝነት እንስሳቶች አስተዋውቋል። የሲኒየር ፔት ኮኔክት ፕሮግራም ከሰውነት አድን ትብብር (ሁማን ሬስኩይ አሊያንስ) ጋር በመጣመር የተጋራ የቤት እንስሳቶች ፍቅር ላይ በእድሜ የገፉ አዋቂዎችን ከማህበረሰባቸው ጋር በማሳተፍ ማህበራዊ መገለልን ለመቀነስ የተቀየሰ ነው።
ዲሲ ሄልዝ (DC Health)
የኮኖቫይረስ/COVID-19 የከተማ አዳራሽ ስብሰባዎች እና ቴሌቫይዝድ የመረጃ ክፍለ-ጊዜያት
DC Health ከሶስት የከንቲባ የብሔር ይዘት ቢሮዎች ጋር ትብብር አድርጓል፥ የላቲኖ ጉዳዮች ቢሮ (ኦፊስ ኦን ላቲኖ አፌይርስ (MOLA))፣ የአፍሪካ ጉዳዮች (አፍሪካን አፌይርስ (MOAA))፣ እና የአሲያ እና ፓሲፊክ አይላንደር ጉዳዮች (አሲያን ኤንድ ፓሲፊክ አይላንደር አፌይርስ (MOAPIA)) እንዲሁም የከንቲባ ዋና ስራ አስፈጻሚ ቢሮ (ኤክስከቲቭ ኦፊስ ኦፍ ዘ ሜየር (EOM)) እና የዲሲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች (ዲሲ ፐብሊክ ስኩልስ (DCPS)) የኮሮናቫይረስ/COVID-19 ምርመራ ጣቢያዎች እና የመከላከያ እርምጃዎችን በተመለከተ ለLEP/NEP ህዝብ ፍትሃዊ የመረጃ ተደራሽነትን ለማቅረብ የታሰበ በበየነ-መረብ የታገዘ የከተማ አደራሽ ስብሰባዎችን ለማድረግ።
እንዲሁም DC Health ስፓንኛ-ተናጋሪ LEP/NEP ማህበረሰብን ስለ HIV መድሃኒት ተደራሽነትን፣ የፋርማሲ ጥቅማጥቅሞች ሮል-አዎት ኢኒሺየቲቭ፣ የኮሮናቫይረስ/COVID-19 መከላከል፣ እና ህክምና በተመለከተ ለማሳወቅ ስድስት የተላለፉ (አየር ላይ የዋሉ) ቃለ-መጠይቆችን ከቴሌሙንዶ ጋር አድርጓል። እነዚያ ማሳወቂያ ዝግጅቶች ማሻሻያዎች በጣም ወሳኝ በነበሩበት ጊዜ ላይ የተለያዩ የኋላ-ታሪክ ያላቸው የዲስትሪክት ኗሪዎች በፍጥነት-ስለሚለዋወጡ የወረርሽኝ ምላሾች እንዲያውቁ አድርገዋል።
የሥራ-ቅጥር አገልግሎቶች መምሪያ (ዲፓርትመንት ኦፍ ኢምፕሎይመንት ሰርቪስስ (DOES))
የDOES “en español” ድረገጽ
ስፓንኛ ተናጋሪ ደንበኞች ስለ DOES ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች በስፓንኛ ቋንቋ መረጃ እንዲያገኙ የሚፈቅድ ነው። DOES “en español” በኮሎምቢያ ዲስትሪክት የመጀመሪያ የሙሉ-አገልግሎት ስፓኒሽ መንግስት ድረገጽ እና በስፓንኛ የሚሰራ የመጀመሪያ ብሄራዊ የሰው ኃይል ኤጀንሲ ድረገጽ ነው የሆነው። የስፓንኛ ቋንቋ ተናጋሪ ግለሰቦች በኤጀንሲው ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች (እንደ UI፣ የደመወዝ-ሰዓት፣ MBSYEP)፣ ጋዜጣዊ መግለጫዎች፣ የሠራተኛ ስታቲስቲክስ እና ሌሎች ላይ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
የሜትሮፖሊታን ፖሊስ መምሪያ (ሜትሮፖሊታን ፖሊስ ዲፓርትመንት (MPD))
የላንጊየጅ ላይን ሶሉሽንስ (Language Line Solutions) መተግበሪያን መተከል
MPD የላንጉየጅ ላይን ሶሉሽን የሞባይል መተግበሪያን በሁሉም የቢሮ ስልኮች ላይ መትከልን በተሳካ ሁኔታ ፈጽሟል። በመላው ከተማው ህግ አስከባሪዎች የተለያዩ የኋላ አመጣጥ ታሪክ ያላቸውን ሰዎች እየረዱ ባሉበት ጊዜ፣ ይህ እርምጃ አንድ ተጨማሪ የመግባቢያ እንቅፋትን ይሰብራል።