Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የOHR የኦክቶበር ወር ጋዜጣ - የዳይሬክተሩ መልዕክት

Wednesday, October 30, 2024

የOHR የኦክቶበር ወር ጋዜጣ - የዳይሬክተሩ መልዕክት

ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እና ጓደኞች፦

በዚህ የኦክቶበር ወር፣ ስለ የአካታችነት ሃይል እና ይበልጥ ሃቀኛ እና ፍትሃዊ ማህበረሰብን በመገንባት ስለምንጋራው የጋራ ሃላፊነት እናስታውሳለን። ብሄራዊ የጥቃት መከላከል ወር፣ ብሄራዊ የአካል ጉዳተኞች የስራ ስምሪት የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር እና የ LGBTQIA+ ታሪክ ወርን ስንመለከት የጋራ በሆነ አላማ የተጣመሩ ሶስት የሚታወሱ ምክንያቶችን እናከብራለን፦ ሁሉም ሰው አስተዳደጉ ምንም ይሁን ምን መበልጸግ እና በአክብሮት መስተናገድ መቻሉን ማረጋገጥ።

ብሄራዊ የጥቃት መከላከል ወር ወጣቶቻችንን በተለይም በትምህርት ቤቶቻችን እና ማህበረሰቦቻችን ውስጥ የሚገኙትን ዘላቂ ከሆነ የጥቃት ጉዳት የመጠበቅን አስቸኳይ ፍላጎት አጉልቶ ያሳያል። በዲሲ የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ፣ ለእኛ የወጣቶች የጥቃት መከላከል ፕሮግራም፣ ለሁሉም ተማሪዎች አስተማማኝ እና ደጋፊ ቦታዎችን ለመፍጠር ከትምህርት ቤቶች፣ ቤተሰቦች እና የማህበረሰብ ቡድኖች ጋር በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ ነን። በፕሮግራሙ፣ እያንዳንዱ ወጣት እንደሚታይ፣ እንደሚደመጥ እና ጥበቃ እንደሚደረለት እንዲሰማው ማድረጋችንን፣ ጥቃት ወይም አድልዎን ሳይፈራ የሚበለጽግበት አካባቢ መስፋፋቱን ለማረጋገጥ ጥረት እናደርጋለን።

በብሄራዊ የአካል ጉዳተኞች የስራ ስምሪት የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር መንፈስ፣ እውነተኛ ኢኮኖሚያዊ ፍትሃዊነት የሚመሰረተው በአካታች የስራ ልምዶች ላይ መሆኑን እናስታውሳለን። አካል ጉዳተኛ ግለሰቦች ከአድልዎ ነጻ የሆኑ የስራ ቦታዎች የማግኘት መብቶቻቸው እንዲከበሩ እና ልዩ ተሰጦዎቻቸውን እንዲያበረክቱ በኩራት እንደግፋለን።

በተጨማሪ፣ የ LGBTQIA+ ታሪክ ወርን ስናከብር፣ ለእኩልነት እና ለፍትህ የታገሉ አዳዲስ ሃሳብ ያመነጩ ሰዎችን የምናሳይ ሲሆን ለተለያዩ የጾታ ማንነቶች እና የጾታ ዝንባሌዎች ሰፋ ያለ ተቀባይነት እንዲኖር መንገድ ይከፍታል። የ LGBTQIA+ መብቶችን የማሳደግ ስራችን የሚቀጥል ሲሆን የእኛን አዲስ አካታች የቋንቋ መመሪያ ለመጀመር ጓጉተናል። ከከንቲባው የሌዚቢያን፣ የግብረሰዶም፣ ሁለት ጾታ ያለው፣ ጾታ የቀየረ እና ስለ ጾታ ማንነታቸው ጥያቄ ያላቸው ጉዳዮች ቢሮ (MOLGBTQA) ጋር በመተባበር መመሪያው ለሁሉም የጾታ ማንነት እና አገላለጽ አይነቶች ጥለቅ ያለ ግንዛቤን እና አክብሮትን ለማዳበር ያለመ ነው።

ይበልጥ አካታች የሆነ ማህበረሰብን ለማፍራት ቀጣይነት እንዳለው ቁርጠኝነታችን አካል፣ አዲሱን የፊልም መግለጫ ጽሁፍ አቅርቦት መስፈርት ማሻሻያ ህግንም እንዲሁ በኦክቶበር 18 ተግባራዊ ማድረግ ጀምረናልን። ይህ ህግ በዲስትሪቱ ውስጥ ያሉ ቲያትሮች በየሳምንቱ ትንሽ ቁጥር ያላቸውን የመግለጫ ጽሁፍ የተካተተባቸው ትዕይንቶች እንዲያቀርቡ ያስገድዳል። ይህ የህግ ማስፈጸም ተደራሽነትን እና አካታችነትን ለማሻሻል ወሳኝ እርምጃ የሚያመለክት በመሆኑ ኩራት ይሰማኛል። የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ይበልጥ ለማጠናከር፣ ቲያትሮች ለህጉ ተገዢ እንዲሆኑ ለመርዳት እና ማህበረሰቦቻችን ያለምንም እንቅፋት በሲኒማ ተሞክሮዎቻቸው ሙሉ በሙሉ ደስ መሰኘታቸውን ለማረጋገጥ ከከንቲባው መስማት የተሳናቸው፣ መስማት እና ማየት የተሳናቸው እና ለመስማት የሚቸገሩ ቢሮ (MODDHH) ጋር በመተባበር እየሰራን ነው። ስለ ህጉ እና ህጉን በማስፈጸም OHR ያለውን ሚና በሚመለከት የበለጠ ለማወቅ ድረገጻችንን ይጎብኙ።

እነዚህ ስርዓቶች እንደ መመሪያ ያገለግላሉ። አካታችነትን በመደገፍ፣ ኢፍትሃዊነትን ተቃውሞ በመቆም እና ዋሽንግተን ዲሲን የአዎንታዊ ለውጥ ተምሳሌት የሚያደርገውን ስፊ ብዝሃነት በማክበር-በማህበረሰቦቻችንን፣ በስራ ቦታዎቻችን እንዲሁም በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ የለውጥ አራማጆች በመሆን እንቁም።

የማህበራዊ ሚዲያ ሰርጦቻችንን በመከታተል ለሚመጡ ስልጠና እና የስርጭት ዝግጅቶችን ለማግኘት ከእኛ ጋር እንደተገናኙ ይቆዩ እንዲሁም የኖቬምበር እና የዲሴምበር ጉዳዮችን አጣምሮ የያዘውን ልዩ የበዓል እትም ጋዜጣችንን ይጠባበቁ!

 

በአንድነት፣

ኬነዝ ሳውንደርስ