Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

To find support and resources for federal workers, visit fedsupport.dc.gov.

-A +A
Bookmark and Share

 የተከበራችሁ ተቀማጭነታችሁ በዲሲ የሆነ፣ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶችና ወዳጆች፤ (Amharic)

Monday, September 29, 2025

የዲሲ የሰባዊ መብቶች ቢሮ (OHR) የሰፕቴምበር ወር (September) የዜና መጽሄት - የዲሬክተሯ/ሩ መልእክት

 

 የተከበራችሁ ተቀማጭነታችሁ በዲሲ የሆነ፣ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶችና ወዳጆች፤

ሰፕቴምበር ወር (September) የሽግግር ወቅት ነው-፣  ተማሪዎች ወደየ ትምህርት ቤታቸው የሚመለሱበት፣ መደበኛ ስራዎች ዳግም የሚጀመሩበት እና የአየር ሁኔታም ወደ ብርዳማነት የሚቀየርበትወር ነው።  በዚህ የነጸብራቃዊና የተሃድሶ መንፈስ በሰፈነበት ወቅት የሰብዓዊ መብቶች ጽህፈት ቤት (Office of Human Rights -ኦ-ኤች-አር OHR) በመገናኛ ብዙሃን በኩል የምናደርገውን ተነሳሽነት (ጥበቃና ከለላ የሚሰጣቸው ባህርይ-#ProtectedTraitTuesday) እንዲጠናክር መስራቱን  ይቀጥላል።  ከተማችን በተደጋጋሚ የሚያጋጥሙ  ፈተናዎችን መጋፈጧን በመቀጠል ማህበረሰባችን ጠንካራ እንዲሆንና ስላሙና ደህንነቱ ከህግ አንጻር ጥበቃና ከለላ ያገኝ ዘንድ  የተቀመጡትን ባህርያችንን በበለጠ እናሰምርበታለን።

በእነዚህ ጎልተው የሚታዩ ሳምንታዊ ክስተቶች ውስጥ፤ በዲሲ ሰብዓዊ መብቶች ህግ (DC Human Rights Act)ውስጥ ሰፍረው ከሚገኙት (ጥበቃና ከለላ የሚሰጣቸው ባህርያት 23 ባህርያት ውስጥ ለምሳሌ የዘር፣ የስንክልና፣ የቤት-አጥነት፣ የጾታ ማንነት ወይም አገላለጽ  ከመሳሰሉት ጉዳዮች ውስጥ አንዱን እናስተዋውቃለን። በህግ በኩል የእያንዳንዱ መብት ጥበቃ ምን እንደሚመስልና እነኚህ ጥበቃዎች  በቤቶች፣ በስራ አቀጣጠር፣ በህዝባዊ ጉዳዮችና በትምህርት በኩል እንዴት በስራ እንደሚተረጎሙ ማስረጃ ይሰጣል። እያንዳንዱ ሰው በዲስትሪክቱ ውስጥ ያሉት መብቶችና ጥበቃዎች ምን እንደሆኑ በማስታወስ፤ እያንዳንዱ ዘመቻ፤ ማህበረሰቡ በዲስትሪክቱ ውስጥ ስላሉት መብቶችና ጥበቃዎች፤ ህዝቡ ንቁ ተሳትፎ እንዴት ሊያደረግና ጥንካሬ እንዴት  ሊያገኝ እንደሚችል የሚረዳ ትምህርት ይሰጣል። የበለጠ ለመማርና ለማወቅ፣ አዳዲስ መረጃዎችንና የስልጠና ዕድሎችን ለማግኘት በኦንላይን ወደ@dchumanrights በመግባት ይመልከቱ።

ሰፕቴምበርወር (September) በተጨማሪ ብሄራዊ የማይሰሙና የመስማት ችግር ያለባቸው ሰዎች ወር (National Deaf Awareness Month) የምናከብርበትም ወር ነው። ይህም ማለት የማይሰሙና የመስማት ችግር ያለባቸው ሰዎችን ባህል፣ ታሪክና ተሞክሮ በበለጠ የሚጠናበት ወር ነው ማለት ነው። የዲሲ የሰባዊ መብቶች ቢሮ (OHR) በአጠቃላይ የመስማት ችግር ያለባቸው የዲሲ ተቀማጮች፤ ሲኒማ ቤት ገብተው የሚታየው ፊልም እንዲገባቸው ለማድረግ፤ ትያትር ቤቶች የፊልሙ ተዋንያን የሚናገሩት ሁሉ በጽሁፍ ተጽፎ በስክሪኑ ላይ እንዲታይ (captioning) የሚያዘውና ጥቅምት (October) 2024 በስራ ላይ እንዲውል የተደረገው የዲሲ ህግ ( the DC Open Movie Captioning Requirement Amendment Act  እንዲጠናከር ሚና በመጫወት ላይ በመሆናችን የሚያኮራን ነው። ይህ ህግ የመስማት ችግር ያለባቸው ሰዎች የሚያዩት ፊልም እንዲገባቸው የተዋንያኖቹን ንግግርም ሆነ የሙዚቃ አቀራረብ፤ በስክሪኑ ላይ በጽሁፍ እንዲቀርብ የሚያዝ ህግ ነው።

ይህ የፊልም ንግግር በጽሁፍ መቅረብ አለበት የሚለው ህግ ሁሉም እንዲያውቀው መስርያ ቤታችን ለመብቱ መከበር  ከቆሙ ቡድኖችና  በከንቲባዋ ጽህፈት ቤት መስማት የተሳናቸው፣ የመስማት ችግር ያለባቸውና ማየት የተሳናቸው ቢሮ (ኤም-ኦ-ዲ-ዲ-ኤች-MODDH) ጋር በመተባበር አያሌ አስፈላጊ ነገሮች ተደራሽነት እንዲኖራቸውና ትምህርታዊ ጥረቶች እንዲደረጉ በመስራት ላይ ይገኛል። በተጨማሪም፤ ይህ ህግ በስራ ከተተረጎመበት ከጥር ወር (October) 2024 ጀምሮ  የዲሲ የሰባዊ መብቶች ቢሮ (OHR) (OHR)፤ ህጉ በስራ መተርጎሙን ለማወቅ ሁለት ጥናቶችን አካሂዷል። በሁለቱም ጥናቶች በዲስትሪክቱ የሚገኝ እያንዳንዱ ሲኒማ ቤት ህጉን በስራ ላይ እንደተረጎመ በማረጋገጣችን ደስታ ይሰማናል። ኦ-ኤች-አር (OHR)፤ ይህንን የሚያካሂደውን ጥናት ወደፊትም የሚቀጥለው ሲሆን፤ እስከአሁን የተደረገው የመጀመርያው ጥናት፤ የመስማት ችግር ያለባቸው የዲሲ ተቀማጮች ምን ያህል ትርጉም ያለው ጥቅም በማግኘት ላይ መሆናቸውንና የህጉን ውጤታማነት ያሳያል።

የዲሲ የሰባዊ መብቶች ቢሮ (OHR) (OHR) በዲስትሪክቱ ውስጥ ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ለማድረግና የማህበረሰቡን ተሳታፊነት ለማጠናከር፤  ያሉትን መሳርያዎችና ማስፈጸሚያዎችን  ለመጠቀም ቃል ይገባል። ወደዚህ አዲስ ወቅት በማናመራበት ግዜ፤ አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣትና ግንኙነትን ለማጠናከር በምናደረገው ጉዞ ከእኛ ጋር አብረውን እንዲሆኑኙ እንጋብዛለን- አሰራራችን- (one trait, one action at a time!

በህብረት

ኤሊዛቤት ፎክስ-ሰለሞን (Elizabeth Fox-Solomon)

ማስታወሻ፡ እዚህ ላይ የግል ማስታወሻ አለኝ፤ የሰፕቴምበር ወር (September) የማህጸን ካንሰር የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር (Gynecologic Cancer Awareness Month) ነው። እንደ አንድ ከዚህ የማህጸን ካንሰር  የዳነ ሰው መጠን፤ ‘ቢሎው ዘ ቤልት” (below-the-belt) ስለሚባሉት የካንሰር በሽታዎች በደንብ እንድታውቁ አበረታታችኋለህ። በአሁኑ ግዜ በተለይም በጥቁር ሴቶች መካከል በዚህ የማህጸን ካንሰር( Uterine cancer) እየጨመረ በመሄድ ላይ ያለው ሴቶች  ቁጥር እያደገ በመምጣትና የሚደርሰው የሞት አደጋም እየጨመረና ከፍተኛውን ደረጃ እየያዘ የመጣው በጥቁር ሴቶች ላይ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል። እውቀት ሃይል ነው፤ የራስዎን ወይም የሚወዱትን ሰው ህይወት ሊያድን ይችላል። ይህን ተጭነው  here. የበለጠ ይወቁ።