ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች፣ እና ወዳጆች ፦
በአፕሪል 21፣ 2004፣ ከንቲባ አንቶኒ ዊሊያምስ ለዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ዋነኛ የህግ አካል የሆነውን፣ የቋንቋ ተደራሽነት ህግን ፈርመዋል፣ እንዲሁም በሃገሪቱ ውስጥ አስፈላጊ የሆነ የሲቪል መብት መስፈርት አውጥተዋል። የዲስትሪክቱ ነዋሪዎች የሚናገሩት ቋንቋ ወይም የእንግሊዝኛ ቋንቋን የመናገር ብቃት ደረጃቸው ምንም ይሁን ምን ህጉ ለመንግስት አገልግሎቶች፣ ሰነዶች፣ እና ፕሮግራሞች እኩል ተደራሽነትን ያቀርባል። ህጉ በትጋት የሚሰሩ፣ የእለት ተዕለት ነዋሪዎች አስፈላጊ የመንግስት አገልግሎቶችን እና/ወይም ፕሮግራሞችን እንዳያገኙ የሚከለክሉትን የቋንቋ እንቅፋቶችን መፍትሄ በመስጠት የተገደበ የእንግሊዝኛ ብቃት (LEP) እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቃት የሌላቸው (NEP) ማህበረሰቦች ሚዛናዊ የሆነ የመልካም አጋጣሚዎች እና የአገልግሎት አቅርቦት እንዲኖር ያበረታታል፣ ህጉ በስራ ላይ ከዋለ ከተላለፈ በዚህ ወር አስራ ዘጠኝ አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፣ የዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ነዋሪችን እና ጎብኝዎችን ዲሲ አካታች ከተማ መሆኗን እንዲሁም በዲሲ የሚኖሩ፣ የሚሰሩ እና የሚጎበኙ ገምቢ አስተዋጾ ሊያበረክቱ የሚችሉ የስደተኛ ማህበረሰብ ለመገንባት እና ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ማረጋገጡን ቀጥሏል።
የዲሲ ሰባዊ መብቶች ቢሮ የቋንቋ ተደራሽነት ፕሮግራምን (ፕሮግራሙን) በማዘጋጀቱ እና የ ዲሲ ቋንቋ ተደራሽነት ህግን የማስፈጸም እና የመተግበር ስራን የሚሰራ አካል በመሆኑ ኩራት ይሰማዋል። ፕሮግራሙ ለ63 የመንግስት ድርጅቶች እንዲሁም በገንዘብ ለሚደገፉ አካላት የቴክኒክ ድጋፍ እና የቋንቋ መርጃዎችን አቅርቧል።
እንደ አስፈጻሚ ተቋም እና ፕሮግራም ባለው ሚና፣ ፕሮግራሙ ለሁሉም የቋንቋ ተደራሽነት ባለ ድርሻ አካላት፣ በቋንቋ ተደራሽነት ስልጠናዎች አማካኝነት፣ በቋንቋ ተደራሽነት የተሻሉ ተሞክሮዎች ቴክኒካዊ ድጋፍ በማቅረብ ግንባር ቀደም ሆኖ ቆይቷል።
እንደ ሰባዊ መብቶች ቢሮ ተልዕኮ አካል፣ የድምጽ አልባውን ማህበረሰብ መተማመን የሚጨምር እና የከተማችንን የተነቃቃ መንፈስ የሚጠብቅ የሲቪል መብት አስፈላጊነትን ለማሻሻል እና ግንዛቤን ለማስጨበጥ ቃል እንገባለን። ለዚህ ነው — የLAA ህግ አውጪ 19ኛው በአል አከባበር ላይ — የ ሰባዊ መብቶች ቢሮ የቋንቋ ተደራሽነት ፕሮግራም ከተማ አቀፍ የቋንቋ ተደራሽነትን ፕሮግራሙን በህዝብ ትራንፖርት ተቋማት በኩል በማስተዋወቅ ለይ ይገኛል።
ለስደተኞች ተስማሚ የሆነ አካባቢን መገንባት እና እያደገ የመጣውን የከተማዋን ብልጽግና ተደራሽነት የሚያረጋግጡ መልካም አጋጣሚዎችን ለማስፋፋት ልምዶቻችንን እና መመሪያዎቻችንን ለማጠናከር ያለንን ቁርጠኝነት የምንቀጥል ይሆናል።
በሰብዐዊ መብቶች ቢሮ የቋንቋ ተደራሽነት ፕሮግራም ዳይሬክተር እንደመሆኔ እና ቡድኑን በመወከል፣ መላው ነዋሪዎች ነዋሪዎች እና የማህበረሰብ አባላት በሙሉ ንቂ ተሳትፎ እንዲኖራቸው የሚያስፈልጋቸውን አገልግሎቶች እንዲያገኙ የሚያግዙ አጠቃላይ የቋንቋ ተደራሽነት ፖሊሲዎችን ያስፋፋ፣ ያቀፈ፣ እና ተግባራዊነት እየተጋች ያለች የዲሲ አገር አቅፍ መሪ ከተማ ነዋሪ ተብዬ በመጠራቴ ኩራት ይሰማኛል።
ሮዛ ካሪሎ
የቋንቋ ተደራሽነት ፕሮግራም ዳይሬክተር
ፕሪሲላ መንዳዛባል
የቋንቋ ተደራሽነት ፕሮግራም አናሊስት
አልኪንዲ ካዲር
የቋንቋ ተደራሽነት የፕሮግራም ድጋፍ ልዩ ባለሙያ