Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የ ዲሲ የሰባዊ መብቶች ቢሮ (ኦ ኤች አር) ፕሮግራም ሃላፊ ጋር ይተዋወወቁ

Tuesday, August 16, 2022

የተወደዳችሁ ወላጆች፤ ተማሪዎች፤ መማህራንና ሰራተኞች፡

ህ የነሓሴ ወር አዲስ የትምህርት ዓመት የሚጀመርበት ወር እንደመሆኑ መጠን፤ ራሴን ለማስተዋውቅና ስለ ጥፋተኛነትን የማስወገድ ከተማ-አቀፍ የወጣቶች ፕሮግራም (ዋይ-ቢ-ፒ-ፒ-) እንደገና ለመግለጽ እፈልጋለሁ።  ስሜ አርነስት ሼፓርድ እባላለሁ። በዚህ ጥፋተኛነት    የመከላከል ከተማ-አቀፍ የወጣቶች ፕሮግራም ውስጥም ፕሮግራም ሃላፊ ነኝ ። በዲሲ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ላለፉት አራት ዓመታት ስሰራ ከቆየሁ በኋላ፤ የ ዲሲ የሰባዊ መብቶች ቢሮ (ኦ ኤች አር) ስራ የጀመርኩት ባለፈው ሚያዝያ (April) 2022  ላይ ነበር።  በዚህ ባለፈው ስራዬ፣ በ115 የዲሲ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተፈጸሙ የተባሉ በቆዳ ቀለም ወይም በዘር የተደረጉ አድሎዎችን፤ በጾታ ምክንያት የሚደረጉ ግፎችን እንዲሁም ጥፋተኛነትን የሚመለከቱ በደሎችን እመረምርና አጣራ ነበር። ታይትል 9 በመባል የሚታወቅ ትምህርት ሰልጥኜ የምስክር ወረቀት ያለኝ መርማሪም ነኝ፤ ቀደም ስልም የታይትል 9  ምክትል አስተባባሪ ሆኜ አገልግያለሁ። በዚህም ስራዬ፤ የዘር ልዩነት አድልዎ ተደርጓል፣ ጾታዊ በደል ወይም ማስፈራራት ተፈጽሟል ወይም በዝምድና ላይ የተመሰረት አድሎአዊ ዓመጽ ወይም የማሳደድ ተግባር ተደርጓል ...ወዘተ የሚሉ ክሶች ሲቀርቡ  ዋናው አጣሪ ወይም መርማሪ በመሆን ሰርቻለሁ። በዲሲ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከመስራቴ ቀደም ሲልም ከታይትል 9 ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዋሺንግተን ና በኖርት ካሮላይና ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሰርቻለሁ።

የወጣቶች ጥፋተኞች ማስወገጃ ሪፖርት፤ ከ 2019-2020 የትምህርት ዓመት፤ ምንም እንኳን በአጠቃላይ የአገሪቱ ደረጃ ሲታይ  በዲስትሪክቱ ትምህርት ቤቶች አካባቢ (ከ 19.5 ከመቶ ወደ 12.7 ከመቶ)፣ በኮምፑተር በሚደረግ ውንብድና  ደግሞ (15.7 ከመቶ ወደ 10.6 ከመቶ ) የጥፋተኛነትን  ተግባር  ዝቅ ማለቱ ቢመዘገብም፤ በሚደረጉ ጥሎች ወይም የ እርስ በርስ መደባደብ  (ከነበረው 8.0 ከመቶ ወደ 14.1 ከመቶ) ከፍ በማለታችን፤ ከአገሪቱ ውስጥ ከፍተኞች ከሚባሉት ክፍሎች ውስጥ አንዱ መሆናችንን ያሳያል። ምንም እንኳን በ2017 (8.9 ከመቶ)፤ 2019 (10.5 ከመቶ) ጥፋተኛነትን ጠባይ በአነስተኛ ደረጃ ወደ ላይ ቁጥሩ  ከፍ ቢልም፤ በአጠቃላይ የኮቪድ የወረርሽኝ በሽታ ወቅትን ጨምሮ፤ በትምህርት ቤቶች ያለው የጥፋተኛነት ጠባይ ምንም ሳይቀየር በዛው በነበረበት ቆይቷል ማለት ይቻላል። እነኚህ የተጠቀሱት ቁጥሮች የሚያሳዩት ወይም የሚያስተሳስቡት ነገር ካለ የዚህ የዋይ-ቢ-ፒ-ፒ-( ፕሮግራም ቀጣይነት ምን ያህል አንገብጋቢ መሆኑን ነው።

ይህ የከተማ-አቀፍ ጥፋተኛነት ማስወገጃ ፕሮግራም የተጀመረው በጁን ወር 2013  ሲሆን፤ ዋናው ዓላማው በዲስትሪክቱ ውስጥ ጥፋተኛነትን ባህርያት ለመቀነስና ችግሮች ሲያጋጥሙ ተገቢ መቋቋምያ ዘዴዎችን ለመውሰድ ነው። ይህ ዋይ-ቢ-ፒ-ፒ (YBPP) የሚወስደው የጥፋተኛነትን መፍትሄ ከተማ-አቀፍ ነው፤ ከትምህርት ቤቶች ክልል በመውጣትና በዛ ብቻ ሳይወሰን፤ መላውን ማህበረሰብ በማካተት መፍትሄ የሚያስገኝ በመሆኑ በመላው አገሪቱ ካሉት የመንግስት የጥፋተኛነት ማስወገጃ ፕሮግራሞች ውስጥ ልዩና ጥፋተኛነት ችግርን በመፍታት በኩል ከሚታገሉት ውስጥ በቀዳሚነት ከተቀመጡት ውስጥ አንዱ ለመሆ በቅቷል።

ዋይ-ቢ-ፒ-ፒ ሶስት ነገሮችን ያጠቃልላል- መቀበል፤ ስልጠናና ሁሉንም መድረስ ( outreach)። የፕሮግራሙ አስተዳዳሪ እንደመሆኔ መጠን፤  ትምህርት ቤቶች፣ ተቋሞች፣ እና ገንዘብ ሰጪዎች፤ የጥፋተኛነት ማስወገጅያ መመርያዎች እንዲኖሯዋቸውና የጥፋተኛነት ሁኔታ ስያጋጥም ሁሉም አንድ ዓይነት መመርያዎችን እየተጠቀሙ እንዲፈቱ ማረጋገጥ ሃላፊነቴ ነው። ይህ ዋይ-ቢ-ፒ-ፒ (YBPP) ፕሮግራም፤ አስፈላጊ የሆኑ ስልጠናዎችን ለሚመለከታቸው የት/ቤቶች አባላት፣ ለተቋሞችና ለእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ይሰጣል። ይህ ስልጠናም ሰራተኞች ጥፋተኛነትን ለመቋቋም መደረግ ስለሚገባቸው መፍትሄዎች እንዲረዱ ያደርጋል። ሁሉም ሰው በዚህ ፕሮግራም እንዲሳተፍና ፕሮግራሙ ወደፊት እንዲጓዝ በማድረግ በኩል እንዲተባበር፤ በመጨረሻም ፕሮግራሙ ሌሎችን የማህበረሰቡን አባላትንም እንዲያቅፍ በማድረግ በኩልም ይሰራል። ይህ ያለን ሁሉን የመድረስ ፕሮግራምም፤ ወላጆች፣ የልጆች አሳዳጊዎች፤ ወጣቱ ክፍል፤ ሰራተኞች እና ሌሎችም በአካባቢው የሚገኙ ሁሉ ስለዚሁ ዋይ-ቢ-ፒ-ፒ(ፕሮግራም መኖር፤ ዓላማው ምን እንደሆነና  ከእርሱ ጋር የሚሄዱ ምንጮች ምን እንደሆኑ ማስተዋወቅ  ዋናው ሃላፊነቴ ነው።

ጥፋተኛነትን  በተመለከተ (በዚህ)ገብተው የበለጠ መማር ይችላሉ። ወላጆችም ልጃቸው የጉልበተኛነት ጠባይ ያሳያል የሚል ጥርጣሬ ካላቸው እዚሁ ገብተው በበለጠ መረዳት ይችላሉ። ፕሮግራሙን በተመለከተ ጥያቄ ካሎት ወደ [email protected] በመግባት ወይም በስልክ ቁጥር  (202) 519-3333 በመደወል መልስ ማግኘት ይችላሉ።

ከሰላምታ ጋር

አርነስት ሼፓርድ

ከተማ-አቀፍ የወጣቶች ጥፋተኛነትመከላከል ፕሮግራም የፕሮግራም ሃላፊ

(Citywide Youth Bullying Prevention Program Manager)