Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

ሜይ (May) 2022 የዲሬክተር ማስታወሻ

የኦ-ኤች-አር (OHR) ወርሃዊ ጋዜጣ

   ሜይ (May) 2022  የዲሬክተር ማስታወሻ

የተከበራችሁ የዲሲ ነዋሪዎች ፣ ጎረቤቶችና ጓደኞች፡

ሁላችንም እንደምናውቀው፤ ቋንቋ፤ በአካባቢያችን ያለውን ሁሉ ለመረዳትና እርስ በርስ ለመግባባት የሚረዳን ጠንካራ መሳርያ ነው።. የምንጠቀምባቸውን ቃላት በደንብ መምረጥ እጅግ አስፈለጊ ነው ምክንያቱም የምንጠቀምበት ቋንቋ በአስተሳሰባችን፣ በአመለካከታችን እንዲሁም በአኗኗራችንና ከሌሎች ጋር ባለን መግባባት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አለውና። ሁሉንም የሚያካትት ቋንቋ ስርአት በዲስትሪክታችን እንዲጎለብት የምንፈልገውን አንድነት፣ ሁሉን -አቀፍ  ኢኩቲና እኩልነት፣ እኒሁም ኦ ኤች አር (OHR)አድሎአዊነት ከዲስትሪክታችን ውስጥ እንዲወገድ የሚደረገውን ጥረት ያበረታታ።እንደ ዲስትሪክታች  ማህበረሰባችን፤ ትምህርት ቤቶቻችን፤ ስራ ቦታዎቻችን   እኒዲሁም ማናቸውም ህዝባዊ አገልግሎቶች ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ያማከለ አገልግሎት መስጠታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። በመሆኑም ህበረብሄራዊ አንድነታችንን የሚያጎለብት ትክክለኛ የቋንቋ አጠቃቀም ሊኖረን የግድ ይላል።።

ኦ-ኤች-አር (OHR) የመጀመርያውየሆነውን “ ሁሉንም የሚያካትት የቋንቋ መመርያዎች” ለማውጣት በመብቃቱ ኩራት ይሰማዋል። እነኚህ መመርያዎች ” 8 ዋና” (big 8) ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ሲሆን እነሱም ዘር፣ብሔር፣ አካል ጉዳተኝነት፣ ዕድሜ፣ የኤኮኖሚያዊ ሁኔታ፣ ጾታ፤ ጾታዊ ይዘት (sexual orientation)ና ሃይማኖት ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ የመጀመርያው የቋንቋ መመርያ በዘርና በብሔር ላይ የተመረኮዘ ሆኖ በኦ-ኤች-አር (OHR)እና በከንቲባው የዘር/ በብሔር እኩልነት ጽህፈት ቤት (Mayor's Office of Racial Equity (ORE) የተባበረ ጥረት ነው። መመርያው፤ በግልና በስራ ሕይወታችን ውስጥ የሚያስፈልጉንን ጠቃሚ የቋንቋ መግለጫዎች፣ ሰንጠረዦችንና ምንጮችን የሚያካትት ሲሆ እነኚህም በሰዎች የግልና የሙያ ዘርፍ መካከል ውጤታማ ግንኙነት እንዲኖር ይረዳል። ሁሉን አካታች የቋንቋ ስርአት ሰዎች ምንም ዓይነት አላስፈላጊ ለውጦችን በራስ ላይ ለማምጠት ሳይሞክሩ ትክክለኛ ማንነታቸውን የሚገልጹበትና እርስበርስ የሚግባቡበትን መንገድ በመሻት የቅርብ ግንኙነትና እኩልነት እንዲሰፍን ለማድረግ ይረዳል።

 

የእነኚህ መመርያዎች መውጣት ልክ የኤስያዊ ፓሲፊክ ወር (Asian Pacific Heritage Month) ና የአይሁድ አሜሪካውያን ወር (Jewish American Heritage Month) በምናከብርበት ግዜ መሆኑም በጣም ጥሩ ግዜ ነው። እነዚህ ሁለት ማህበረሰቦች፤ ከሌሎች ማህበረሰቦች ጋር፤ ለብዙ መቶ ዓመታት አላስፈላጊ ያልሆነና እጅፍ አሰጸያፊ የሆነ አድልዎ ሰለባ ሁነው የቆዩ ህዝቦች ናቸው። በዚህ መመርያችን እንደምትገነዘቡት፤ አንዳንዶቹ ገለጻዎቻችንና የምንጠቀምባቸው ቃላት፤ በዘር አድልዎ፤ በጸረ አይሁድ፣ በጎሳና ብሄር እንዲሁም የውጭ አገር ሰዎችን በመጥላት ስሜት ላይ የተመረኮዙ ናቸው። እነኝህም “ማየት የለም/ማድረግ የለም” (no can see/no can do) ወይም “ብዙ ግዜ ብዙ አለማየት” (long time no see) እንደሚሉት ዓይነቶች አነጋገሮች ናቸው። እነኚህ ጸረ-ኤስያውያን አነጋገሮች  በ19ኛው ክፍለዘመን በተለይ በጃፓናውያንና ቻይናዎች፣ እንግሊዘኛ ካለማወቅ የመነጩ አጫጭር አነገገሮች ለመቀለድ ወይም ለማፌዝ የተጀመሩ የዘር አድሎዎች ናቸው። ይህ አጫጭር የእንግሊዘኛ ቃላት መጠቀም (ፒጂን እንግሊዘኛ Pidgin English) በብዙ የዓለም ክልል የሚዘወተር ቀላል የእንግሊዘኛ አነጋገር ነው። “ሂፕ፣ሂፕ፣ ሁሬ”( Hip hip hooray) የሚባል አነጋገርም እንዲሁ በዘር አድልዎ ላይ የተመረኮዘ አነጋገር ነው። እነኚህ ቃላት ከጀርመን ቋንቋ “ሄፕ ሄፕ” (hep hep) ከሚለው የመነጩ ሲሆኑ ጸረ-አይሁድ የሆኑ ሰዎች በ1819  የሄፕ ሄፕ አድማዎች የተደረገበትን ወቅት ሲያመለክቱ ከዛ በኋላ ጀርመን ናዚዎች አይሁዳውያንን በብዛት አስረው በገለደሉበት በ ሆሎኮስት (Holocaust)ወቅት ለአይሁድ የሰጡት ስም ሆነ።

 

በመሆኑም እነኚህን መመርያዎች በምንጠቀምባቸው ቃላትና በምናዝወትረው አነጋገርም፤ ሳናስበው ወይም ሳናውቀው በዘልማድ ስንጠቀምባቸው የቆየነው የአድልዎ ቃላትን ከመጠቀም  እንድንቆጠብ በማገዝ ይረዱናል የሚል ተስፋ እናደርጋለን።

 

 

 

ሁሉን አካታች (Inclusively)