Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የ2012 የቋንቋ ተደራሽነት ፕሮግራም ተግባር ላይ መዋል ሪፖርት

Tuesday, February 26, 2013
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ ላልሆኑ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ያደረጉትን መሻሻል እና ክፍተት ይገመግማል

 

ባስቸኳይ የሚሰራጭ: ስኞ, February 26, 2013
ተጠሪ፣ ኢልዮት ኢምስ (OHR) 202.481.3773; [email protected]
 
(ዋሽንግተን፣ ዲ.ሲ.) – የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ (OHR) የቋንቋ ተደራሽነት (LA) ፕሮገራም የ2012 የቋንቋ ተደራሽነት በስራ ላይ መዋሉን በተመለከተ ያደረገውን ግምገማ ዛሬ ይፋ አደረገ። ሪፖርቱ ውስን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች እና ምንም የእንግሊዝኛ ቋንቋ መናገር ችሎታ የሌላቸው (LEP/NEP) ተገልጋዮች የተሟላ አገልግሎት ሰለማግኘት በዲስትሪክቱ የሚገኙ ድርጅቶች በስራ ላይ ያዋሉት እና የቀሩት ክፍተቶች ላይ ያተኩራል። ክህዝብ ጋር ሰፊ ግንኙነት ያላችው 32 ድርጅቶች የተሳታፊነት መታወቂያ የሚሰጠው ሪፖርት የቋንቋ ድንጋጌን ተግባር ላይ ለማዋል በሚያስፈልጉ ሶስት የማሻሻያ ክፍሎች ላይ ያተኩራል፡ (1) (LEP/NEP) ተገልጋዮችን መከታተል፣ (2) ጠቃሚ የሆኑ ሰነዶችን መተርጎም፣ (3) የድርጅቶች ድረ ገጾች ተደራሽነት።
 
“ድርጅቶች ማሻሻል አድርገዋል። ይሁን እንጅ ለውስን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ ላልሆኑ (LEP/NEP) የዲስትሪክቱን መረጃዎች እና እግልግሎቶች ማግኘታቸውን ለማረጋገጥ የበለጠ መሰራት ይኖርበታል” በማለት ሞኒክ ፓላሲዮ፣ የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ (OHR) የሚቆጣጠረው የላንጉዌጅ አክሰስ ፕሮግራም ዲሬክተር ተናገረዋል። ይህ በተግባር ላይ የማዋል ግምገማ የሚያተኩረው የድርጅቶችን ጥንካሬ እና መሻሻል የሚያስፍልጋቸውን ክፍሎች የተሳታፊነት መታወቂያ በመስጥት የቋንቋ ተደራሽነት ፕሮግራም መሻሻል ወይም አለመሻሻልን በትክክል ለመከታተል ያተኩራል።
 
ይህ አዲሱ ዘዴ የቋንቋ ተደራሽነት በ32ቱ ድርጅቶች ተግባር ላይ መዋሉን ለመገምገም የጥራት እና የመጠን መለኪያዎችን ይጠቀማል። ጥናቱ የዲስትሪክቱ ነዋሪዎች፣ ጠበቃዎች እና ኤጀንሲዎች የድርጅቶችን ድክመት በበለጠ ለመገንዘብ እና ለውስን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች እና ምንም የእንግሊዝኛ ቋንቋ መናገር ችሎታ ለሌላቸው (LEP/NEP) ተገልጋዮች በተለያዩ ድርጅቶች የሚሰጡ አግልግሎቶችን ለማሽሻል የጽሁፍ መገምገሚያ ይስጣል። በተጭማሪም ሪፖርቱ በ23 ድርጅቶችየተደረጉ ጥናቶች ውጤቶችን እና በ2012 በሰብዓዊ መብቶች ቢሮ (OHR) የቀረቡ አቤቱታዎችን ቅድመ ክለሳ ያደርጋል።
 
የቋንቋ ተደራሽነት ፕሮግራም የተጀመረው በ2004 የቋንቋ ተደራሽነት ድንጋጌ መሰረት ሲሆን በብዛት የሕዝብ ግንኙነት ያላቸውን የዲስትሪክቱን ተቋሞች የቋንቋ ተደራሽነትን በተግባር ላይ ማዋል ይቆጣጠራል። ድንጋጌው የዲስትሪክቱ ኤጀንሲዎች ለ500 ወይም ከጠቅላላ ተገልጋዮቹ 3% ለሚሆኑት ለውስን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች እና ምንም የእንግሊዝኛ ቋንቋ መናገር ችሎታ ለሌላቸው (LEP/NEP) ተገልጋዮች የማስተርጎም አግልግሎቶች እና ጠቃሚ ሰነዶችን መተርጎም ያስገድዳል። የቋንቋ ተደራሽነት ፕሮግራም ለተቋሞች ስልጠና አና የቴክኖሎጂ እርዳታ በመስጥት የቋንቋ ተደራሽነት ፕሮግራምን በተግባር ላይ እንዲያውሉ ይረዳል።
 
“የቋንቋ ተደራሽነት ፕሮግራም ቡድኖቻችን እና በየድርጅቱ ከሚስሩት የቋንቋ ተደራሽነት አስተባባሪዎች ጋር በመተባበር በሚያደርጉት ያልታከተ ጥረት የማስተርጎም አገልግሎቶች እና የተተረጎሙ ስነዶች ማግኘት አገልግሎቶች እየተሻሻሉ ነው።” የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ (OHR) ዲሬክተር ጉስተቫ ቬላስኩዌዝ ሲሉ ተናግረዋል። “ስራዓት ያለው ለውጥ ብዙውን ጊዜ ቀላል አይደለም፣ ሆኖም ቡድናችን ለውስን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች እና ምንም የእንግሊዝኛ ቋንቋ መናገር ችሎታ ለሌላቸው (LEP/NEP) ነዋሪዎች የበለጠ ህዝባዊ አገልግሎቶች ማግኘት እንዲችሉ እና በመንግስት ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች እንዲጠቀሙ ለመስራት ዘግጁ ነው።
 
የ2012 “የቋንቋ ተደራሽነት በተግባር ላይ መዋል ሪፖርት በድረ ገጽ ohr.dc.gov/languageaccess/2012report ይመልክቱ።
 
ሰለ የቋንቋ ተደራሽነት በተግባር ላይ መዋል ፕሮግራም ተጨማሪ መርጃ በድረ ገጽ ohr.dc.gov/languageaccess ይገኛል።
 
###
 
ስለ የዲ.ሲ ሰብዓዊ መብቶች ቢሮ
የዲ.ሲ ሰብዓዊ መብቶች ቢሮ (OHR) የተመሰረተው በዲ.ሲ. የሚኖሩ ወይም የሚጎበኙ ሰዎች ላይ አድሎን ለማስወገድ፣ የእኩልነት መብት ለመጨመር እና የሰባዓዊ መብትን ለማስከበር ነው። ይህ ቢሮ የፌደራላዊም ሆነ የአካባቢ መንግስት የስው ልጅ መብት ህጎችን፣ የዲ.ሲ ሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌን ጨምሮ፣ ህጋዊ አገልግሎት በመስጠት መብታችን ተገፈፈ የሚሉትን ይረዳል። የዲ.ሲ ሰብዓዊ መብቶች ቢሮ በዳይሬክተሩ በኩል ለሚቀርቡ ጥያቄዎች አድሎአዊ የሆኑ ድርጊቶችን እና ፖሊሲዎችን ለማጋለጥ እና ለመመርመር በማያወላውል መንገድ ያስፈጽማል።