Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የዲሲ ሰብአዊ መብቶች ቢሮ/OHR/ የፌብሩዋሪ ወርሃዊ ጋዜጣ - የዳይሬክተሩ መልዕክት

Thursday, February 27, 2025

የዲሲ ሰብአዊ መብቶች ቢሮ/OHR/ የፌብሩዋሪ ወርሃዊ ጋዜጣ - የዳይሬክተሩ መልዕክት

 

ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እና ወዳጆች


ለጥቁር ታሪክ ወር እውቅና ስንሰጥ ህዝባችን ላይ ተጽዕኖ ያሳደሩ ብቻ ሳይሆን የዋሽንግተን ዲሲ መሰረት የሆኑ የጥቁር መሪዎች፣ ንቁ የፖለቲካ ተሳታፊዎች እና ዘወትር አዳዲስ ነገሮችን ለሚያከናውኑ እና ጉልህ ተጽእኖ ተጽዕኖ ለሚያመጡ ሰዎች  ክብር እንሰጣለን። በአናኮስቲያ ውስጥ መኖሪያ ቤቱ የመታሰቢያ ቅርስ ምልክት ሆኖ ከቀረው ፍሬደሪክ ዳግላስ/Frederick Douglass/ ማግለልን ለማስወገድ መሰረት እስከጣሉት የሃዋርድ ዩንቨርሲቲ ፕሮፌሰር ቻርለስ ሃሚልቶን/Charles Hamilton/ ድረስ ዲሲ የሲቪል መብቶች ተሟጋችነት እና የእድገት ማዕከል ሆኖ ቆይቷል።


ከተማችን ዋሽንግተን ዲሲ ከማርች 1963 ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር/Martin Luther King Jr./ “ህልም አለኝ” የሚለውን ንግግሩን ካቀረበበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ለፍትህ ለሚደረገው ቀጣይ ጥረት የታሪካዊ እንቅስቃሴ መድረክ ሆና ቆይታለች። በዲሲ የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ (OHR) የሲቪል መብቶች ጥበቃዎችን ለማስከበር እና በከተማችን ውስጥ ያሉ ሁሉም ነዋሪዎች እና ሰራተኞች በፍትሃዊነት እና በአክብሮት እንዲስተናገዱ ለማድረግ በየቀኑ በመስራት ይህንን ቅርስ እናከብራለን። በቅርብ ጊዜ በእኛ የአፈጻጸም ቁጥጥር የችሎት ሂደት ባለፈው አመት የኤጀንሲያችንን የስራ ክንውኖች ለማጉላት እና አፈጻጸምን ለማጠናከር እንዲሁም ለማህበረሰችን ተደራሽነትን ለማስፋት እና  እቅዶቻችንን ለመዘርዘር እድል አግኝቻለሁ። ትርጉም ያለው እድገት እያመዘገብን ቢሆንም ገና ብዙ መስራት ይጠበቅብናል። በዲስትሪክቱ ውስጥ የሰብዓዊ መብቶችን የማሻሻል ታሪካዊ ስራን ለማስቀጠል እና እያንዳንዱ ሰው የሚገባውን ጥበቃዎች ያገኝ ዘንድ ለመርዳት ቁርጠኛ ነን።

በዚህ ወር የዲሲን የጥቁ
ሮች ታሪክ በተለያየዩ ዝግጅቶች፣ ሙዚየም ኤግዚቢሽኖች እና ማህበረሰብ ውይይቶች ላይ በመሳተፍ እንዲያስሱ እናበረታታዎታለን። የአፍሪካውያን አሜሪካውያን ታሪክ እና ባህል ብሄራዊ ሙዚየም በመጎብኘት፣ በጥቁር ባለቤትነት በሚተዳደር አነስተኛ የንግድ ስራዎች ጋር አብሮ በመስራት ወይም ለጎረቤቶችዎ በመቆምና በመሟገት እያንዳንዳችን ቀደም ሲል ከእኛ በፊት የነበሩትን ሰዎች ስራ በማስቀጠል የበኩላችንን  እንጫወታለን።

ለተደራሽነት እና ማህበረሰብን ለማጎልበት  
ቁርጠኛ እንዳመሆናችን OHR ከመራጮች ጋር ለመገናኘት፣ ስለ ሲቪል መብቶች ጥበቃዎች ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እና ቅሬታን በተመለከተ ሂደታችን ላይ ግለሰቦችን ለማስተናገድ  በቂ የስራ ሰዓት ክፍለ ጊዜ አዘጋጅቷል። በሚቀጥለው ፕሮግራማችን ላይ እንዲገኙ እንጋብዝዎታለን -ስጋት ካለዎት፣ እርዳታ ከፈለጉ ወይም ስለመብቶችዎ የበለጠ ማወቅ ከፈለጉ፣ ልንረዳዎት ዝግጁ ነን

በመሆን የጥቁሮች ታሪክን በየቀኑ በፌብሯሪ ወር ብቻ  ልክ እንዳለፈው ፣ የአሁኑ እና የወደፊቱ ወሳኝ አካል አድርጎ በማየትና ከግምት ውስጥ በማስገባት እናክብር! 

 

በአንድነት፣

ኬነዝ ሳውንደርስ