የ OHR (የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ) የሰፕተምበር 2026 ወርሃዊ ዜና መጽሔት- የዳይሬክተር መልዕክት
ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እናወዳጆች፡
የትውልደ አፍሪካውያን ስደተኞች የቅርስ ወርን (አፍሪካን ኢሚግራንት ሄሪቴጅ መንዝ) እና የስፓኒሽ ቅርስና ወርን (ሂስፓኒክ ሄሪቴጅ መንዝ) የምናከብርባት ሰፕተምበር የመገናኛ፣ የባህል እና የማህበረሰብ አንድነት ወር ናት። በዲሲ የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ (ዲሲ ኦፊስ ኦፍ ሂዩማን ራይትስ) ያለን ተልዕኮ ቀላል፣ ነገር ግን ኃያል ነው፦ በዋሽንግተን ዲሲ አድልዎና መድልዎን ማስወገድ፣ እኩል ዕድልን ማስፋፋት እንዲሁም የሰብዓዊ መብቶችን መጠበቅ ነው።ይህ ተልዕኮ አድልዎ በሚከሰትበት ጊዜ ምላሽ ከመስጠት በላይ የሆነ ስራ ይፈልጋል። ይህም ማለት ሰዎች መብቶቻቸውን እና ጥበቃዎቻቸውንእንዲገነዘቡ መርዳት፣ እንዲሁም ነዋሪዎችን ባሉበት ቦታ ለማግኘት የሚያስችሉ ግንኙነቶችን መፍጠር ማለት ነው። በዚህ ወር ይህ ተግባር በትምህርት ቤቶች፣ በማህበረሰብ ዝግጅቶች፣ በጤና አውደ-ርዕዮች እና በመላው ዲስትሪክቱ መገኘትን ያካተተ ነው።
ተማሪዎች እና አስተማሪዎች አዲሱን የትምህርት ዘመን ሲጀምሩ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና አካታች የመማሪያ አካባቢዎች መፍጠር የዚህ ጽኑ አቋም አስፈላጊ አካል ሆኖ ይቀጥላል። በወጣቶች ጉልበተኝነት መከላከል ፕሮግራማችን (YBPP) በኩል፣ ለትምህርት ቤቶች፣ ወጣቶችን ለሚያገለግሉ ድርጅቶች፣ ለወላጆችና እና ለወጣቶች ጉልበተኝነትንለመለየት፣ ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ መሣሪያዎችን እናቀርባለን።በድረ-ገጻችን ላይ ከሚገኙት የግንዛቤ ማስጨበጫ ቁሳቁሶች በተጨማሪ፣ ክህሎተ ብዙ የሆኑ የወጣቶች ሰብዓዊ መብቶች አምባሳደሮቻችንበማህበራዊ ሚዲያ ጉልበተኝነትንለመጋፈጥና ለመከላከል የሚረዱ ሦስት ምክረ ሃሳቦችን አካፍለዋል። እንዲሁም በላቲኔ የአካል ጉዳተኞች ኮንፈረንስ (ላቲነ ኮንፈረንስ ኦን ዲስኤቢሊትዪስ) ላይ የተሳተፍን ሲሆን፣ መረጃው ለሁሉም ተሳታፊዎች ተደራሽ መሆኑን ለማረጋገጥ ከትርጉም አገልግሎት ጋር በስፓኒሽ ቋንቋ የወጣቶች ጉልበተኝነትንመከላከል ሥልጠና አቅርበናል።
ሰዎችን ባሉበት ቦታ ለማግኘት ያለን ቁርጠኝነት ከመማሪያ ክፍልውጪ ድረስ የሚዘልቅ ነው። በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ፣ በላቲኖ ጉዳዮች ቢሮ፣ በካሪቢያን ማህበረሰብ ጉዳዮች ቢሮ እና በእስያ እና የፓሲፊክ ደሴቶች ጉዳዮች ቢሮ ካሉ አጋሮቻችን ጋር በመሆን በዲሲ ሱፒርየር ፍርድቤት 2ኛው ዓመታዊ የጤና እና ደህንነት አውደ-ርዕይ፣ በተከራዮች ተሟጋች ቢሮ በተዘጋጀው የ2026 የተከራዮች ጉባዔ፣ በቪዳ (VIDA) የአረጋውያን ማዕከላት የጤና አውደ-ርዕይ እና በዲሲ ዩኒቲ የእግር ኳስ ዋንጫ (ዲሲ ዩኒቲ ሶከር ካፕ) ላይ ከነዋሪዎች ጋር ተገናኝተናል።እነዚህ አጋጣሚዎች ስለ ሰብዓዊና የዜጎች መብቶች ጥበቃ መረጃ እንድናጋራ ብቻ ሳይሆን እንድናዳምጥ፣ግንኙነቶችን እንድንገነባ እና የምናገለግላቸውን ማህበረሰቦች ፍላጎት በተሻለ ሁኔታ እንድንረዳ ያስችሉናል።
በዚህ ወር የዩናይትድ ስቴትስ የእኩል የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን (ዩኤስ ኢኳል ኢምፕሎይመንት አፖርቹኒቲ ኮሚሽን) ያቀረበውን የሰው ኃይል ሥነ-ሕዝብ (ዴሞግራፊክ) ሪፖርት አቀራረብ መዋቅሩን እንዲይዝ እና እንዲያዘምነውለማሳሰብ፣ የመሰረዝ ሀሳቡን ውድቅ በማድረግ ማለት ነው፣ በመላ አገሪቱ ከሚገኙ ሰባት የሰብዓዊ እና የሲቪል መብቶች ኤጀንሲዎች ጋር ተባብረናል። ይህ መረጃ ከ1966 ጀምሮ የእኩል የሥራ ዕድልን ለማስፋፋት እና በሥራ ቦታ ላይ አድልዎን ለመከላከል ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። የእኛ ተሳትፎ OHR የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃዎች ትርጉም ባለው መንገድ እንዲተገበሩ አስፈላጊ በሆኑ መረጃዎች እና መሣሪያዎች እንዲደገፉ ለማድረግ ያለውን ቀጣይ ቁርጠኝነት ያንጸባርቃል።የጋራ መግለጫችንን እዚህ ማንበብ ይችላሉ።
እዚህ በዲስትሪክቱ ውስጥ በአገሪቱ ውስጥ ካሉ እጅግ በጣም ጠንካራ እና ሁሉን አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሕጎች መካከል የተወሰኑትን በማስከበራችንኩራት ይሰማናል። በአገር አቀፍ ደረጃ የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ እየተለዋወጠ ሲሄድ OHR በዲስትሪክቱ ውስጥ የሚኖሩ፣ የሚሰሩ እና ዲስትሪክቱን የሚጎበኙ ሰዎች በዲስትሪክቱ ሕጎች ሥር የሚያገኟቸውንጥበቃዎች እንዲገነዘቡ በማድረግ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ይቀጥላል። እኛ ከማህበረሰባችን ጎን ቆመን ነዋሪዎችንና ጎብኚዎችን እያስተማርን፣ሠራተኞችንና አሰሪዎችን እየደገፍን፣ እንዲሁም አካታችነትን እና እኩል ዕድልን ለማስፋፋት የድርሻችንን እየተወጣን እንገኛለን።
መልዕክቴን ከማጠናቀቄ በፊት ሰፕተምበር የማህፀን ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር (ጋይኖኮሎጂካል ካንሰር አዌርነስ መንዝ) መሆኑን መግለጽ እፈልጋለሁ። ከኢንዶሜትሪየምእና የማህፀን ካንሰር የዳንኩኝ ሴት እንደመሆኔ ይህ ጉዳይ ለእኔ ጥልቅ ትርጉም አለው። ተሞክሮዬን ማካፈሌ ሌሎች ሰዎች ስለእነዚህ ብዙ ጊዜ ችላ ስለሚባሉ የካንሰር ዓይነቶችን የበለጠ እንዲያውቁ እና ስለ ጤናቸው ውይይት እንዲያደርጉ ለማበረታታት አንዱ መንገድ ነው። ስለ ማህፀን ካንሰር ምልክቶች ግንዛቤ ለማግኘት ጥቂት ጊዜ እንዲወስዱ አበረታታዎታለሁ። የማንን ሕይወት ሊታደጉ እንደሚችሉ ማን ያውቃል።
ወደ ፎል ወቅት ስንሸጋገር እርስ በርሳችን መጠያየቃችንንእና ከተማችንን ይበልጥ ጠንካራ የሚያደርጉትንግንኙነቶች ማጠናከራችንን እንቀጥል። ማንም ሰው ከአድልዎ ነፃ ሆኖ የሚኖርባት፣ የሚሰራበት፣ የሚማርባት እና የሚያድግባትንዋሽንግተን ዲሲን በጋራ መገንባታችንን እንቀጥላላለን ።
