Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የሜይ (May) 2024 (Amharic)

Tuesday, May 21, 2024

የተከበራችሁ የዲሲ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶችና ጓዶች የዲሲ የቋንቋ ተደራሽነት ሕግ (DC Language Access Act) 20ኛውን ዓመትና ፍትሃዊ የመኖርያ ቤቶች ተደራሽነት ወርን (Fair Housing Month) በመላው ኤፕሪል (April) ወር ስናከብር የዲሲ ሰብአዊ መብቶች ቢሮ (ኦ-ኤች-አር) ብዙ ስራ የተካሄደባቸው የስፕሪንግ ወር ወራት በመገባደድ ላይ ነበር። ይህ የበዓል አከባበር ስራችንም ወደ ሜይ ወር ተሸጋግሮ የኤስያውያን አሜሪካውያን (Asian American)፣ የሃዋይየ ዜጋዎች (Native Hawaiian)፣ የፓሲፊክ ሃይላንደር (Pacific Islander (AANHPI) ተወላጆች የቅርስ ወራትን በቀጣይ በከፍተኛ ኩራት እናከብራለን። ይህ ዓመታዊ በዓል ስር የሰደደው የተለያዩ ባህሎችና ቋንቋዎች ያላቸውና ከ75 በላይ አገሮችና ደሴቶች የተውጣጡ ግለሰቦችን ከሚያጠቃልለው ከፓሲፊክ ሃይላንደር (Pacific Islander (AANHPI) ማህበረሰብና እምቅ የታሪክ ቅርስ ነው።

ይህ የቅርስ ወር በዓል መከበር የጀመረው በጁን (June)1977 ሲሆን፤ ከኑዮርክ ፍራንክ ሆርቶን (Frank Horton) እና ከካሊፎርንያ ኖርማን ሚኔታ (Norman Mineta) የተባሉ ሁለት የፓርላማ ተወካዮች የሜይ (May)ወር የመጀመርያዎቹ አስር ቀናት የ ኤስያውያን አሜሪካውያን ሳምንት ተብለው እንዲሰየሙና እንዲከበሩ ባደረጉት ያላሰለሰ ጥረትና ትግል አማካይነት ነው። በኦክቶበር(October) ወር 1978 ዓም ፕሬዚደንት ጂሚ ካርተር (President Jimmy Carter) ይህንን በዓል በየዓመቱ እንዲከበር ሲያደርግ ከአስራ ሁለት ዓመታት በኋላ ደግሞ ፕሬዚደንት ጆርጅ ኤች ደብሊው ቡሽ (President George H.W. Bush) ወሩን በሙሉ የሚከበር በዓል እንዲሆን ውሳኔ አስተላለፉ። ወሩ የሜይ(May) ወር እንዲሆን የተወሰነበት ምክንያት ደግሞ ከጃፓን አገር የመጡ የመጀመርያዎቹ ስደተኞች ወደ እዚህ አገር የገቡበት በሜይ(May) ወር 1843 በመሆኑና ትራንስኮንትነንታል ሬልሮድ (Transcontinental Railroad) የተባለው የባቡር ሃዲድ፤ በቻይናውያን ስደተኞች ተሰርቶ በሜይ (May) ወር 1869 ተሰርቶ የተጠናቀቀበትን ጊዜ ለመዘከርለ ታስቦ የተደረገ ነው። ።

ይህንን የኤስያውያን አሜሪካውያን የቅርስ ወር (AANHPI Heritage Month) በዓል በምናከብርበት ወቅት ለአምስት የመብት ታጋዮች እውቅናና ክብር እንሰጣለን:- እነሱም ዩሪ ኮቾቺያማ (Yuri Kochiyama)፣ ላሪ ኢትሊዮንግ (Larry Itliong)፣ ግሬስ ሊ ቦግስ (Grace Lee Boggs)፣ ሆናኒ -ኬ ትራስክ (Haunani-Kay Trask) እና ፓትሲ ሚንክ (Patsy Mink) የተባሉ ሲሆኑ መገለልን በመቃወምና ፍትሃዊነትና እኩልነት እንዲነግስ እጅግ አደገኛና አስፈሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ለረጅም ዓመታት በጽናት የታገሉ ናቸው። እነኚህ የህዝብ መብት እንዲከበር የታገሉ ጀግኖች፤ ከብዙው በጥቂቱ ያስተማሩን ነገሮች ካሉ የመቋቋም አቅማችንን ማጠናከርና በጽናት መታገል ወደ ፍትህና እኩልነት የሚያመሩ ብርሃኖች መሆናቸውን ነው። ስለ እነዚህ ሰዎች የትግል ጉዞና ያደርጉት ትግል በሰኬታማነታቸው ላይ ምን ያህል ዘላቂ አስተዋኦ እንዳደረገ በበለጠ ለማወቅ ከፈለጉ በዜና ማሰራጫዎቻችን የምናስተላልፈውን መረጃ ተከታተሉ።

ከእኛ በፊት የነበሩ ኤስያውያን አሜሪካኖች የከፈሉትን መስዋእትና ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ስናስብ እነሱ ካደረጉት ቁርጠኛነትና ጽናት ትምህርት በመቅሰም ሁሉም ሰው በእኩልናትና በመከባበር የሚኖርባትን ዓለም ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ጽናታችንንና ትግላችንን አጠናክረን እቀንጥል።

በህብረት

ኬነት ሶንደርስ (Kenneth Saunders)