Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

ፌብሩዋሪ 2024፣የዳይሬክተሯ ማስታወሻ (Amharic)

Tuesday, February 27, 2024

ውድ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እና ጓዶች፦ በ1920ዎቹ የሃርለም ህዳሴ ከመጀመሩ በፊት፣ ዩ ስትሪት መተላለፊ ያኮሪዶር በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን ትልቁን የአፍሪካ አሜሪካውያን በከተሞች የሚኖሩ ህዝቦችን ነበር። በመሰረቱ የሚሰራው አፍሪካዊ አሜሪካውያን ከጂም ክራውን እስራት ነጻ የወጡበት እና በጥቁር ባለቤትነት ስር ባሉ ወይም ለጥቁር ተስማሚ በሆኑ የንግድ ስራዎች፣ አብያተክርስቲያናት፣ ቲያትር ቤቶች፣ ስፖርት መስሪያ ቤቶች ወይም ሌሎች የማህበረሰብ ቦታዎች በነጻ የሚዝናኑበት በከተማ ውስጥ እንዳለ ከተማ ነበር።

ለ20ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ አጋማሽ፣ በተዋናይት፣ ደራሲ እና ዘፋኝ ፒርል ቤይሊ የወጣው “ብላክ ብሮድዌይ” ተብሎ የሚጠራ የፈጠራ፣ የተሳትፎ እና የማህበረሰብ ማዕከል ነበር - የጥቁር ድምጾች አለማችንን የመቅረጽ አስደናቂ ሃይል እንዳላቸው የሚያሳይ ማስረጃ ነው። እንደ ሉዊስ አርምስትሮንግ፣ ማዳሜ ሊሊያን ኢቫንቲ፣ ቢሌይ ሆሊዴይ፣ ማይልስ ዴቪስ እና ጄሊ ሮል ሞርቶን የመሳሰሉ ልዩ ታዋቂ ሰዎች በአገር ውስጥ ክለቦች ውስጥ የተጫወቱ ሲሆን እንደ ዞራ ኒሌ ሀርቶን እና ሜሪ ማክሊኦድ ቤቱኔ ያሉ ታዋቂ ሰዎች ጥገኝነት አግኝተው ነበር።

እንዲሁም አካባቢው በ1853 የተከፈተው እና በከፊል ለሲቪል መብት ተሟጋቾች እንደ ስብሰባ ቦታ ሆኖ የሰራው የሃገሪቱ የመጀመሪያው አፍሪካዊ አሜሪካዊ YMCA መኖሪያ ነበር። በታገደበት ጊዜ፣ ብዙ የዲስትሪክቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ህገወጥ ቡና ቤቶች በመተላለፊያ መንገዱ ላይ ይገኙ ነበር፣ ይህም የታሪክ ጸሃፊው ጋሬት ፔክ በጥልቅ መገለል ላይ የነበረችውን ከተማ ለማዋሃድ ስላገዙ እውቅና ይሰጣቸዋል። ዩ ስትሪት (U Street) እና ሌሎች ታዋቂ የዲሲ ሰፈሮችን በሚመለከት በዲሲ የቅርስ ማስረጃ ላይ የበለጠ ማወቅ ይችላሉ።

የጥቁር ብሮድዌይ ታሪክ በአንዳንዶች ለረጅም ጊዜ የተረሳ ቢሆንም፣ የዲስትሪክቱን ብቻ ሳይሆን የሃገሪቱን የባህል እና የፖለቲካ ምህዳር በመቅረጽ ረገድ ጥቁር አርቲስቶች ወሳኝ ሚና መጫወታቸውን አስታዋሽ ነው። ለዘመናት የሚታዩትም ሆኑ የሚሰሩ የቲያትር ጥበባት፣ ስነ ጽሁፍ፣ ሙዚቃ፣ የምግብ አሰራር እና የመሳሰሉት ለታሪክ፣ ለፖለቲካ ተሳትፎ እና ለማህበራዊ ለውጥ ጠንካራ ማስተላለፊያ ሆነው ቆይተዋል።

የጥቁር ታሪክ ወርን ስናከብር፣ ጥቁር የኪነጥበብ ሰዎችን ቅርስ ለማክበር እና የጥቁር ድምጾችን ለማጉላት እና አዳዲስ ተሰጦዎችን ለመደገፍ ያለንን ቁርጠኝነት እንደገና ለማረጋገጥ አጭር ጊዜ መውሰድ አለብን። እንደዚህ በማድረግ፣ የዘር ፍትሃዊነትን ለማሻሻል እና ጥበባት የጋራ ሰብዐዊነታችን የሚያስተጋባ ነጸብራቅ ሆኖ መቀጠሉን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆናችንን በድጋሚ እናገራለን።

በጋራ፣ የጥቁር ማህበረሰብን ጽናት፣ ፈጠራ እና ዘላቂ መንፈስ በፌብሩዋሪ ብቻ ሳይሆን አመቱን ሙሉ ማክበራችንን እንቀጥል።

በአንድነት፣