Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

ኦ ኤች አር በዓል ዜና- ህዳር/ታህሳስ 2023

Tuesday, December 12, 2023

ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች፣ እንዲሁም ወዳጆች

ዲሲ የሰባዊ መብቶች ቢሮ/OHR /የመልካም በአል መልክት እና የሞቀ አቀባበል! ባለፈው ወር ብሄራዊ ሀገር በቀል ቅርስ ወርን እና ብሄራዊ የተንከባካቢዎች ወርን በማክበር የሁለት ዋና እንዲሁም ብዙ ጊዜ በበቂ ሁኔታ አድናቆት ያልተሰጣቸው ቡድኖች ላበረከቷቸው ወሳኝ አስተዋዕጾዎች እውቅና ሰጥተናል።

ለወራት በሚቆየው ክብረ በአል ለሃገሩ ተወላጅ ሰዎች መደበኛ እውቅና መስጠት ስለ ልዩ ልዩ ቅርሶቻቸው፣ ባህላቸው እና ትግሎቻቸው (ታሪካዊ እና ዘመናዊ) ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ አዲስ እድል ሰጥቷቸዋል። የሃገሩን ተወላጅ ሰዎች በሚመለከት ያሉት አብዛኞቹ ያልተቀየሩ ሃሳቦች እና የተሳሳቱ አመለካከቶች ቢኖሩም፣ ወደ 4 ሚሊዮን ያህል ሰዎች አሜሪካዊ ህንዳዊ ወይም የአላስካ ተወላጅ እንደሆኑ ይታወቃል (የእኛን Words Matter ይመልከቱ፦ ስለነዚህ የተለያዩ ቃላት ለማወቅ በዘር እና በጎሳ ማንነት ዙሪያ ቋንቋን የሚያካትት መመሪያ)። በዲስትሪክቱ ውስጥ እና ዙሪያ ስላለው የሃገሩ ተወላጅ ማህበረሰብ የበለጠ ለማወቅ “የጎሳ ሉዐላዊነትን እና ማንነት ማክበር” የሚለውን የዚህን አመት ርዕስና መልዕክት እንደ መመሪያ ይጠቀሙ።

አንዳንድ እስታትስቲካዊ መረጃዎች በመላው ሃገር ለአረጋውያን፣ ለታመሙ ወይም ለአካል ጉዳተኞች እንክብካቤ እና ድጋፍ የሚሰጡ ከ53 ሚሊዮን በላይ ተንከባካቢዎች እንዳሉ ያመለክታሉ። ምንም እንኳን ከእነዚህ ተንከባካቢዎች መካከል አንዳንዶቹ የሚከፈላቸው ቢሆንም፣ አብዛኞቹ የማይከፈልበት እንክብካቤ ይሰጣሉ - በጠቅላላው ከ$470 ቢሊዮን በላይ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ይሰጣሉ። እነዚህ ተንከባካቢዎች፣ የቤተሰብ አባላት፣ የሚወዷቸው ሰዎችም ሆኑ የቤት ሰራተኞች የማህበረሰባችን ወሳኝ አባላት ሲሆኑ እነርሱ ላ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ጉዳዮች እራሳችንን ማስተማር በጣም አስፈላጊ ነው። ተንከባካቢዎች በ1997 የዲሲ። ሰብዐዊ መብቶች ህግ መሰረት እንደ ቤት ሰራተኞች እና ጥበቃ/ ከለላ በተደረገላቸው የቤተሰብ ሃላፊነቶች ባህሪያት (በአራቱም ተፈጻሚ ዘርፎች) ጥበቃ ይደረግላቸዋል

 

ወደ ዲሴምበር ወር ስንገባ፣ የበአል ወቅትን ብቻ እየተቀበልን አይደለም፤ በሰብዐዊ እና በሲቪል መብቶች ጥበቃ ውስጥ ጉልህ የሆኑ ወሳኝ ጊዜያትን እያስታወስን ነው። ዲሴምበር አለም አቀፍ የሰብዐዊ መብቶች ወር የሚከበርበት ሲሆን በዚህ አመት የአለም አቀፍ የሰብዐዊ መብቶች አዋጅ - ወደ ነጻነት እና እኩልነት የሚመራን መብራት 75ኛ አመት ክብረ በአልን ያከብራል። ምንም እንኳን እድገት ቢመዘገብም፣ ፍትህ እና መከባበር ሃሳቦች ብቻ ሳይሆኑ የሚኖሩ እውነታዎች ለሚሆኑበት አለም ያለንን ቁርጠኝነት ላስቀጠሉ እና ላደሱ መሰናክሎች እውቅና እንሰጣለን።

በተመሳሳይ፣ የአካል ጉዳተኞች መብት አዋጅ 48ኛ አመት ክብረ በአል ስናከብር ዲሴምበር 20 በልባችን ልዩ ቦታ አለው። ይህ አዋጅ አካታች አካባቢዎች ለመገንባት፣ መሰናክሎችን ማስወገድ እና ለአካል ጉዳተኛ ግለሰቦች መብቶችን ለመታገል የጋራ ሃላፊነታችንን ያጎላል። የአካል ጉዳት መገለልን በመዋጋት እና ተደራሽነትን በማረጋገጥ፣ ለሁሉም ሰው አካታችነትን እና ፍትሃዊነትን የሚያከብር ማህበረሰብ እንፈጥራለን።

የበአሉን ወቅት ስናከብር፣ ፍትህ፣ ነጻነት እና መከባበር ምኞቶች ሳይሆኑ ለሁሉም ሰው የተኖሩ እውነታዎች የሚሆኑበትን አለም ለመገንባት በጋራ ቁርጠኝነት አለም አቀፍ የሰብዐዊ መብቶች ወርን እናክብር።

በፍቅር፣ በደስታ እና በጥልቅ የማህበረሰብ ስሜት የተሞላ መልካም በዓላትን እንዲሆንላችሁ ለሁላችሁም እንመኛለን።