ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እና ጓደኞች
እንኳን ለወርሃ ኦክቶበር አደረሰዎ! አንደኛውን የበጀት አመት አጠናቀን አዲሱን የምንጀምር ከመሆኑ አንጻር ይህ ለኦኤችአይ አስደሳች እና የስራ ውጥረት የበዛበት የአመቱ ወቅት ነው፡፡ ኦኤችአር የ2024ን የበጀት አመት አዲስ በተደነገገው የቤት ሠራተኞች የስራ ቅጥር መብቶች ማሻሻያ አዋጅ መሰረት ለዲስትሪክቱ የቤት ሠራተኞች አዲስ ጥበቃዎችን ተግባራዊ በማድረግ በጥንካሬ ይጀምራል፡፡ ከቀን ኦክቶበር 1/2023 ጀምሮ የሚጸናው ይህ አዲስ ህግ የቤት ሠራተኞች ዘርን፣ የትውልድ ሀገርን ወይም ጾታዊ ዝንባሌን በመሳሰሉ ጥበቃ የሚደረግላቸው 18 ጉዳዮች ላይ በመመስረት መድልዎ ተደርጎብናል ብለው በሚያምኑበት ጊዜ እንደ ማንኛውም ሌሎች ሠራተኞች በዲሲ የሰብአዊ መብቶች ጽ/ቤት (ኦኤችአር) ዘንድ ህጋዊ ክስ ለመመስረት ያስችላቸዋል፡፡
እንደ ማህበረሰብ አጋርነቱ ኦኤችአር ከቤት ሠራተኞች ማህበረሰብ ጋር ሲሰራ የቆየ ሲሆን፤ ሠራተኞቻችን እና ነዋሪዎቻችን አዲሱን የህግ ጥበቃ እና ኃላፊነቶች እንደሚገነዘቡና እንደሚረዱ ለማረጋገጥ ዓላማ ይህንን ግንኙነታችንን ከቤት ሠራተኞች እና ከዲስትሪክቱ ቤተሰቦች/ነዋሪዎች ጋር ለማስቀጠል እንፈልጋለን፡፡ በተለያዩ ቋንቋዎች አዲስ ከታተመው መመሪያችን ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ይችላሉ፡፡
ኦክቶበር የኤልጂቢቲኪው+ የታሪክ ወር እንደመሆኑ፤ የኤልጂቢቲኪው+ ጉዳዮች እና ወርድስ ማተር፡- ኤ ጋይድ ቱ ኢንክሉሲቭ ላንጉጅ አራውንድ ሴክሹዋል ኦሪየንቴሽን እና ወርድስ ማተር፡- ኤ ጋይድ ቱ ኢንክሉሲቭ ላንጉጅ አራውንድ ጄንደር አይደንቲቲ ኤንድ ኤክስፕሬሽን የሚሉ ሁለት አዲስ የአካቶ ቋንቋ መመሪያዎች ዝግጅትን በተመለከተ ከከንቲባው ቢሮ ጋር በመተባበር ያገኘናቸውን ስኬቶች እና ለዲስትሪክቱ የኤልጂቢቲኪው ማህበረሰብ ያደረግናቸውን አስተዋጽኦዎች የምናከብርበት ወር ነው፡፡ ሁለቱ መመሪያዎች ለሠራተኞች፣ ነዋሪዎች እና ጎብኚዎች ጠቃሚ መረጃዎችን የሚሰጡ ሲሆን፤ ጾታዊ ዝንባሌን እና የጾታ ማንነትን በተመለከተ የሚደረጉ ውይይቶች ላይ የበለጠ በማስተዋል ተሳትፎ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል፡፡ እነዚህ መመሪያዎች በሚታተሙበት ጊዜ inclusion and Equity Resources በሚል ርዕስ ስር ከድረገጾቻችን ሊያገኟቸው ይችላሉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ኦክቶበር የብሔራዊ የአካል ጉዳተኞች የስራ ቅጥር ግንዛቤ ወር (ኤንዲኢኤኤም) እና የቤት ውስጥ ጥቃት ግንዛቤ ወር ነው፡፡ የዚህ አመት የኤንዲኢኤኤም ጭብጥ “ተደራሽነትንና እኩልነትን ማራመድ” የሚል ሲሆን፤ የ1973ቱን የመልሶ ማቋቋም ህግ 50ኛ አመት እና በፌዴራል መስሪያ ቤቶች፣ የፌዴራል ስራ ተቋራጮች እና በፌዴራል የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸው አካላት ዘንድ በአካል ጉዳት ሁኔታ ላይ የተመሰረቱ ቅጥሮችን በሚመለከት የሚደረጉ መድልዎዎችን በመከላከል ረገድ ያለውን አስፈላጊነት ያከብራል፡፡ ምንም እንኳን ኦኤችአር በፌዴራል መንግስት ላይ ስልጣን ባይኖረውም፤ በዲሲ ሰብዓዊ መብቶች ህግ መሰረት የሚቀርቡ የአካል ጉዳተኝነትን የሚመለከቱ ቅሬታዎችን በተመለከተ የግል ድርጅቶችን እና የዲሲ መንግስትን የመመርመር፣ የመበየን እና የመክሰስ ስልጣን አለን፡፡ በዲሲ ስራ ቦታዎች አካቶ እና ተደራሽነት ምን እንደሚመስሉ ከዚህ ላይ የበለጠ ለማወቅ ይችላሉ፡፡
የቤት ውስጥ ጥቃት፣ ጾታዊ ጥቃት እና ስቶኪንግ (ያለ ፈቃድ የሚደረግ ክትትል) ሰለባዎች/ዲቪኦኤስ/ የስራ ቅጥር ጥበቃ የማሻሻያ ህግ መሰረት ዲስትሪክቱ በቤት ውስጥ ጥቃት ሰለባዎች ላይ የሚደረግ መድልዎን ለማስወገድ ቁልፍ ተዋናይ ሆኖ ይቀጥላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የዲሲ ምክር ቤት ጉዳዩ ለዲስትሪክቱ ከመሰጠቱ በፊት የነበረውን የ6 ወር እስከ 1 አመት አስገዳጅ
የፍቺ መጠበቂያ ጊዜን የሚያስወግዱትን የመጀመሪያዎቹን ሁለቱን የህግ ድምጾች ሙሉ በሙሉ አጽድቋል፡፡ ይህ ሰዎች በጥቃት የተሞላውን ግንኙነት አስቀድመው ለመተው/ለማቋረጥ እንዲችሉ ያደርጋቸዋል፡፡ እርስዎ ወይም እርስዎ የሚያውቁት ሌላ ሰው በኦኤችአር አማካኝነት ስላሉት የስራ ቅጥር ጥበቃዎች ተጨማሪ መረጃ ቢፈልጉ እባክዎን እዚህ ላይ የእኛን መመሪያዎች ይመልከቱ፡፡
በመጨረሻም፤ ኦክቶበር በቀልድ ላይ የተመሰረቱ ድርጊቶች (ትሪክስ ኤንድ ትሪትስ) የተሞላውን በበዓልነት ያልተመዘገበውን በዓል ሀሎዊንን ይዞ ይመጣል፡፡ ብዙ ሰዎች ሀሎዊንን በስህተት ከዲያ ዴ ሎስ ሙዌርቶስ ጋር ያያይዙታል፤ ነገር ግን ሁለቱ ተመሳሳይነት የላቸውም፡፡ ከዲያ ዴ ሎስ ሙዌርቶስ ወይም የሙታን ቀን የሚባለው የላቲን በዓል የሚከበረው ከኖቬምበር 1 አስከ ኞቬምበር 2 ሲሆን በዓሉ ህይወትን ማክበር የሚመለከት ሲሆን መሰዊያዎችን በማዘጋጀት እና ወደ ምድር የሚመልሰውን የቤተሰቡን አባል መንፈስ ለማስደሰት ምግቦችን እና ስጦታዎችን በማቅረብ የሞቱባቸውን የሚወዷቸውን የቤተሰብ አባላት የቤተሰብ አባላት የሚያከብሩበት በዓል ነው፡፡ በነዚህ ሁለት በዓላት መካከል ያሉትን ልዩነቶች ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም የተለዩ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለይቶ ማወቁ የህብረት ስሜት በመፍጠር እያንዳንዱ ክብረ በዓል ላይ ግንዛቤ እንደተወሰደ እና በልዩነቱ ተቀባይነት እንደሚሰጠው ለማረጋገጥ ያስችላል፡፡