Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

መስከረም 2023 (Amharic)

Thursday, September 21, 2023

ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እና ጓደኞች፣

መስከረም የዓመቱ አስደሳች ጊዜ ነው። የወደፊት መሪዎቻችን እና ለውጥ ፈጣሪዎች የሚሆኑ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት የሚመለሱበት ነው። አየሩ ትንሽ ቀዝቀዝ የሚልበት፣ የዱባ ቅመም ላቴ የሚመለስበት እና የፎል (መኸር) ስፖርት የሚጀመርበት ወቅት ነው። ነገር ግን በዚህ ወር የዲስትሪክታችን የብዝሃነታችን አከባበር መገለጫ የሆኑትን፣ የአፍሪካ ቅርስ ወር እና ብሄራዊ የሂስፓኒክ ቅርስ ወር (ከሴፕቴምበር 15 እስከ ኦክቶበር 15) ነው።

ከ 2010 ጀምሮ ዲስትሪክታችን የአፍሪካን ተፅእኖ፣ የዲያስፖራ ትሩፋት፣ እና የአፍሪካ ማህበረሰባችን የእለት ተእለት ህይወታችንን ቅርፅ በመቅረጽ የተጫወተውን ጥልቅ ፋይዳ ለማክበር የአፍሪካ ቅርስ ወር በይፋ እውቅና ሰጥቷል። እውቅና ካገኘበት ጀምሮ፣ የበለጠ ተወዳጅ እየሆነ መጥቷል፤ እና በ 2022 ጎረቤታችን፣ የቨርጂኒያ ግዛት እውቅና ሰጥቶታል። የከንቲባው የአፍሪካ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት (The Mayor’s Office of African Affairs)፣ የዲስትሪክታችንን የአፍሪካ ማህበረሰብ ጥበብ፣ ባህል፣ ምግብ፣ ታሪክ እና ሙዚቃ በሚያሳዩ ዝግጅቶች ይህን ወር ለማክበር በበላይነት ይመራዋል።

ከዚህ ጎን ለጎን፣ ለሂስፓኒክ እና ላቲኖ ቅርስ ክብር እና ለሀገራዊ የሂስፓኒክ ቅርስ ወር ያለው ክብር መነሻው በ 1960ዎቹ ሲሆን ይህም በሲቪል መብቶች ንቅናቄ እና በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ላሉ የተለያዩ ባህሎች ግንዛቤ እያደገ መሆኑን በማሳየት የሚገለጽ ዘመን ነው። ፕሬዝደንት ሮናልድ ሴፕቴምበር 15 የብሄራዊ የሂስፓኒክ ቅርስ ወር መጀመሪያ አድርገው በ 1988 የከበሩበት ምክንያት እንደ ኮስታሪካ፣ ኤልሳልቫዶር፣ ጓቲማላ፣ ሆንዱራስ እና ኒካራጓ ያሉ አንዳንድ የላቲን አሜሪካ ሀገራት የነጻነት መታሰቢያ አመታዊ በዓል በመሆን ስለሚታወቅ ነው ። ከዲስትሪክታችን ላቲኖ/ማህበረሰብ ጋር እንዴት እንደሚገናኙ ለማወቅ በላቲኖ ጉዳዮች የከንቲባ ጽ/ቤትን (the Mayor’s Office on Latino Affairs )ያግኙ እና በመላው ዲሲ በዓላትን (festivities) ለማክበር እና ለመደሰት እርግጠኛ ይሁኑ።

እዚህ በ OHR፣ የዲስትሪክታችንን ብዝሃነት ስናከብር፣ ነዋሪዎች እና ጎብኝዎች መካተት እና መከባበር እንዲሰማቸው ለማድረግ ቋንቋን ያካተተ ሁኔታ በማነጽ ላይ እናተኩራለን። በሚቀጥሉት አራት ሳምንታት ውስጥ ስለዚህ ጉዳይ በማህበራዊ ሚዲያችን ላይ ተጨማሪ መረጃ እናካፍላለን። አሁንም፣ ጉጉታቸው ገደብ ለሌለው፣ “የቃላት ጉዳይ፡ በዘር እና በጎሳ ማንነት ዙሪያ አካታች ቋንቋ መመሪያ” የሚል ርዕስ ያለው ሁሉን አቀፍ የመረጃ ምንጭ የእርስዎን ንባብ/ጥናት ይጠበባቃል፡ ይኽም ለማስተማር፣ መሰናክሎችን ለማፍረስ እና እኩል እድሎችን ማስተዋወቅ፣ ከዘር እኩልነት ቢሮ (the Office of Racial Equity )ጋር የሚደረግ የትብብር ጥረት ነው።

 

አገልጋይዎ፣

HNK