ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች፣እንዲሁም ወዳጆች
የበጋውን ወር እየገፋንና አዲሱ የትምህርት አመት እየመጣ ባለበት ውቅት የ ኦ ኤች አር የወጣቶች ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እንዲሁም ጏዶች ጉልበትኝነትን መከላከል ፕሮግራም ስልጠናና ፕሮግራሞች ቡድን መሪ የሆኑትን ኤርነስት ሸፐርድ የስራ እንቅስቃሴ ላይ ትኩረት መስጠት እፈልጋለሁ፣ ባሁኑ ሰአት የስልጠናና የማህበረሰብ ተደራሽነት ፕሮግራሞችን ማሻሻል ላይ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ ይገኛል። ይህ ፕሮግራም ‘የተማሪዎች ተከታታይ የውይይት ሂደት’ እስቸው ከሚመሩት መከከል አንዱ ሲሆን፣ አነስተኛ የውይይት ቡድኖች በተለይም ተማሪዎች በድፍረት ስለራሳቸው መናገር የሚለማመዱብት መድረክ ነው::
OHR በዲስትሪክቱ ውስጥ ካሉ ትምህርት ቤቶች ጋር በመተባበር ከነዚህ ውይይቶች ውስጥ አጠቃላይ ጭብጦችን እና ግኝቶችን ከት/ቤት አስተዳዳሪዎች ጋር ያካፍላል። እነዚህ ውይይቶች አወንታዊ የት/ቤት የአየር ሁኔታን ለመፍጠር ይረዳሉ ብለን እናምናለን፣ እና የተማሪ ውይይት በት/ቤትዎ ማካሄድ ከፈለጉ፣ እባክዎን በኢሜል [email protected] ላይ ያነጋግሩን። ስለ ጉልበተኝነት እና ወላጆች ልጃቸው ጉልበተኝነት ውስጥ ስለመካተት ያላቸውን ጥርጣሬ እንዴት መፍታት እንደሚችሉ የበለጠ መረጃ ለማግኘት፡ በዲስትሪክቱ ውስጥ ጉልበተኝነት፡ ጠቃሚ ምክሮች ለወላጆች የሚለውን ይጎብኙ። በተጨማሪም፣ ኧርነስት የወጣቶቻችንን ሰብአዊ መብቶች የሚያስተምር፣ የሚያበረታታ እና የሚያሳትፍ የመጀመሪያውን የOHR የወጣቶች የሰብአዊ መብት አምባሳደር ፕሮግራም ለማዘጋጀት እየሰራ ነው። አምባሳደር የመሆን ፍላጎት ያለው ወጣት ካወቁ፣ በ [email protected] ድረገጽ ሊያገኙን ይችላሉ።
ኦገስት ብሄራዊ የጥቁር ንግድ ወር መሆኑንም ይህን ጊዜ ወስጄ እውቅና መስጠት እፈልጋለሁ። ዲሲ የበርካታ ታሪካዊ በጥቁር-ባለቤትነት የተያዙ ንግዶች መኖሪያ በመሆኑ ኩራት ይሰማዋል እና የራሳቸውን ንግድ ለመጀመር ለሚፈልጉ ጠንካራ ፕሮግራሞችን ያቀርባል። በ2201 Channing St NE ላይ የሚገኘው የመጀመሪያው በጥቁር-ባለቤትነት የተያዘ ስትሪፕ ሞል የሆነው አዲስ የተቋቋመው ብላክ ኤንድ ፎርዝ የዲስትሪክቱ መንግስት በማህበረሰባችን ውስጥ ኢንቨስት የሚያደርጉ በጥቁር ባለቤትነት የተያዙ ንግዶችን እንዴት እንደሚደግፍ የሚያሳይ ፍጹም ምሳሌ ነው። የእሱ መስራች ኤንጅል ግሪጎሪዮ የዲሲ ተወላጅ እና የሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ሲሆን ስፓይስ ስዊትን ያቋቋመ እና የጥቁር ሴት የሆኑ አነስተኛ ንግዶችን የሚደግፍ ነው። የእርሷ ማህበረሰቡን ያማከለ የንግድ ሞዴል ቦታን የማጋራት እና ስራ ፈጣሪዎችን በዲሲ ውስጥ እውቅናቸውን እንዲገነቡ መደገፍ የዲሲ እሴቶቻችንን ያሳያል። በዚህ ወር ድጋፍዎን ያሳዩ እና በአካባቢው በጥቁር ከተያዙ የንግድ ተቋማት ይግዙ።
በመጨረሻም፣ OHR እያደገ እና እየሰፋ ሲሄድ፣ አዲስ ከፍታ ላይ ለመድረስ በምናደርገው ጥረት ጀምስ ዩ (እሱ/የሱ/የሷ) የኤጀንሲው የመጀመሪያ የኮሙዩኒኬሽን እና ፍትሃዊነት ፕሮግራሞች ተባባሪ ዳይሬክተር በመሆን OHR መቀላቀላቸውን በደስታ እገልጻለሁ። ተባባሪ ዳይሬክተር ዩ ቀደም ሲል በከንቲባው የማህበረሰብ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት (MOCA) የሰራተኞች ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆኖ ሰርቷል፤ ከውጪ እና ከውስጥ አጋሮች ጋር ያተኮረ ሽርክና በመመሥረት እና አካታች እና ፍትሃዊ የመልእክት ልውውጥን መርቷል። የወጣቶች ጉልበተኝነትን የመከላከል ፕሮግራምን፣ የቋንቋ ተደራሽነት ፕሮግራምን፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታዎችን መፍጠር እና የግንኙነት እና የማህበረሰብ ተሳትፎ ቡድንን ይቆጣጠራል። ጄምስ OHRን በመቀላቀሉ በጣም ደስ ብሎናል እና ለእሱ ሞቅ ያለ አቀባበል ለማድረግ አብረውን እንደሚሆኑ ተስፋ እናደርጋለን!
OHR will also be recruiting for an Associate Director for OHR ለግዳጅ ማስፈጸሚያ ተባባሪ ዳይሬክተር ይቀጥራል፤ እሱም ምርመራውን እና የ ADR ቡድኖችን የሚቆጣጠረው፡፡ ብቁ የሆነን ሰው የሚያውቁ ከሆነ በድረ-ገፃችን እና በ careers.dc.gov ላይ ለአዳዲስ መረጃዎች ትኩረት ሰጥተው ይታታተሉ ።
ኤች ኤን ኬ