Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

ሐምሌ 2023 (Amharic)

Monday, July 24, 2023

በ2020 ኔትፍሊክስ (Netflix) በኒኮል ኔውንሀም (Nicole Newnham) እና ጄምስ ለብረችት (James LeBrecht) የተመራ (ዳይሬክት የተደረገ) የተጻፈ እና በጋራ-የተዘጋጀ (ኮ-ፕሮዱስድ) አካል ጉዳተኛ ስለ ሆኑ ሰዎች በኒው ዮርክ ካትስኪልስ ያደረጉት የሳመር (በጋ) ካምፕ የተመለከተ ዘጋቢ ፊልም (ዶኩመንታሪ) አወጣ በካምፑ የተሳተፉ ሰዎች የአካል ጉዳተኛ እንቅስቃሴ በመምራት ረገድ እና በመጨረሻም የ1990ው አካል ጉዳተኛ የሆኑ አመሪካውያን ህግ (አመሪካንስ ዊዝ ዲስኤቢሊቲስ አክት ኦፍ 1990) እንዲወጣ በማድረግ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል። ተሸላሚው ዘጋቢ ፊልም (ዶኩመንታሪ) ሁለንተናዊ መልእክት ያስተላልፋልተነሳሽነት ያላቸው ወጣቶች አለምን የሚቀይር ውጤቶች የሚያመጡ ሥር ነቀል እንቅስቃሴዎችን ሊመሩ ይችላሉ

ካምፕ ጀነድ (Camp Jened) አካል ጉዳተኛ ለሆኑ ልጆች፣ ጎረምሶች (ቲንስ) እና አዋቂዎች የተለያዩ አይነት አካል ጉዳት ላላቸው ተንከባካቢ ማህበረሰብ ለማቅረብ  በ1951  የተመሰረተው ነው። በ1960ዎቹ እና በ1970ዎቹ ካምፑ በ60ዎቹ ጸረ-ባህል (ካውንተር ካልቸር) እና የሂፒ እሴቶች ከፍተኛ ተጽእኖ የነበረው ነው። ካምፑ በካምፑ የሚሳተፉትን እና አማካሪዎቹን (ካውንስለርስ) የአካል ጉዳተኞች የማይገለሉበት ዓለም ስለሚመጣበት ሁኔታ እንዲያስቡ ፈቀደ። አካል ጉዳተኛ ያልሆኑ ሰራተኞች አካል ጉዳተኛ የሆኑ የሚያሳልፏቸውን ትግሎች እንዲረዱም አገዘ፣ ይህም “ጀነድያንስ” በፖለቲካ ንቁ እንዲሆኑ አደረገ። ለምሳሌ፣ አንዳንድ በካምፑ የተሳተፉ ሰዎች በበርክሊ፣ ካሊፎርንያ የሚገኘውን የገለልተኛ ኑሮ ማእከልን (ሰንተር ፎር ኢንዲፐንደንት ሊቪንግ) ተቀላቅለዋል። ማእከሉ አካል ጉዳተኛ የሆኑትን ሰዎች ራስን-መቻል፤ ክብር፤ እና ራስን-በራስ የመወሰን ደገፈ፣ የዚህ ውጤትም ራስን ችሎ መኖር (ኢንዲፐንደንት ሊቪንግ) የሚለው ጽንሰ-ሀሳብ የአካል ጉዳተኛ መብቶች እንቅስቃሴዎች የመአዝን ድንጋይ እንዲሆን አደረገ። ካምፑ ስኬታማ የነበረ ቢሆንም በፋይናንስ ችግሮች 1977 ተዘጋ። በ2009 ከነጭራሹ ከመዘጋቱ በፊት በ1980 በራክ ሂል፤ ኒው ዮርክ ተከፍቶ ነበር።

የኤ.ዲ.ኤ. 33ኛውን የምስረታ በአል ስናከብር ወጣት መር የሆኑ እንቅስቃሴዎችን ኃይል መገንዘ አስፈላጊ ነው። የወጣት እንቅስቃሴዎች የዘመናዊው ህብረተሰብ ዋና ገፅታ ሆነዋል፣ እና ቴክኖሎጂውም፣ በተለይ በዲጂታል ቦታዎች (ስፔስስ) ላይ ድምፃቸውን ከፍ ባለ ድምፅ እንዲያሰሙ እድል ሰጥቷቸዋልበዲጂታል ስፔስ ላይ በአካል ጉዳት፣ በችሎታ (አብለይዝም) እና በተደራሽነት ዙሪያ ውይይቶችን ማቀጣጠል ቻሉ በርካታ የአካል ጉዳተኞች አክቲቪስቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፡ ኒኮል ፓሪሽ (@SoundOfTheForest) በኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር እንደ ትልቅ ሰው ያጋጠማትን ልምድ የምታካፍል እጅግ በጣም የሳንካ አድናቂ፣ ኢማኒ ባርባሪን (@Crutches_And_Spice) በዲጂታል ስፔስስ (ቦታዎች) ውስጥ ስለ ዘረኝነት እና ስለ ችሎታ (አብለይዝም) ምትናገር አክቲቪስት እና የግንኙነት ባለሙያ፣ እና ሐበን ግርማ (@HabenGirma)መስማትና ማየት የተሳናት፣ ለመካተት እና ተደራሽነት ያደረገቻቸው የትግል ተሞክሮዎችዋን የምታጋራ የሰብአዊ መብት ጠበቃ

ለአካል ጉዳተኝነት መብቶች የሚደረገውን ትግል አሁን መቀላቀል አስፈላጊ ነው ምክንያቱም በአንድ ወቅት በአንድ ሰው ህይወት ውስጥ ጊዜያዊ ወይም ቋሚ የአካል ጉዳት ያጋጥማልና ነው። አሁን ያሉበት የአካል ጉዳተኝነት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን ሁሉም ሰው የሚጠቅም ስለ ሆነ፣ ከአካላዊ መስተንግዶ ባሻገር ተደራሽነትን ማረጋገጥ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆን አለበት። በተጨማሪም፤ በዲስትሪክቱ የሚኖሩ፤ የሚሰሩ ወይም የሚጎበኙ ከሆነ በሁሉም በአራቱም የማስፈጸሚያ ቦታዎች አካል ጉዳተኝነት የህግ ከለላ የሚገኝበት ባህሪ (ፕሮቴክትድ ትረይት) ነው፡ በትምህርት ተቋማት፣ ስራ ቦታ፣ መኖሪያ ቤት፣ እና የህዝብ ማረፊያዎች እና የመንግስት አገልግሎቶች እርስዎ ወይም ሌላ እርስዎ የሚያውቁት ሰው መድልዎ ተፈጽሞብኛል የሚል ስሜት ያለ፣ ከሆነ ቅሬታን እንዴት ፋይል ማድረግ እንደሚችሉ በተመለከተ በይበልጥ ለመማር ድረገጻችንን ohr.dc.gov መጎብኘት ይችላሉ።