Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የሐምሌ 2022 የዳይሬክተር ማስታወሻ

Tuesday, July 19, 2022

ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች፣ እና ጓደኞች፣

በአዕምሮ ጤና እና ከሱ ጋር የሚኖሩ ማህበረሰቦች ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ግንዛቤን ስናሳድግ፣ በአዕምሮ ጤና እና በአዕምሮ ጤና ህክምና ዙሪያ ያለውን መገለል ለማስወገድ በጋራ መስራት አስፈላጊ ነው። የአዕምሮ ጤና ህመሞች በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በጣም ከተለመዱ የጤና እክሎች ውስጥ ናቸው። በ2020፣ በUS ውስጥ በግምት 52.9 ሚልዮን አዋቂዎች (ወይም ከ5 አዋቂዎች 1) ከአዕምሮ ህመም ጋር ይኖሩ ነበር። እንዲሁም፣ ከ5 ልጆች መካከል 1 አሁን ወይም በህይወታቸው የሆነ ወቅት ላይ አድካሚ የአዕምሮ ህመም ያጋጥማቸዋል። ከልጆች መካከል፣ አቴንሽን ዴፊሲት ሃይፐርአክቲቭ ዲስኦርደር /attention deficit hyperactivity disorder (ADHD)፣ ጭንቀት፣ ድብርት፣ ወይም ሌሎች የባህሪ ችግሮች በጣም የታወቁ ህመሞች ናቸው። በ ኤስ ውስጥ ለአዕምሮ ህመም ልኬትን አስተዋጽዖ የሚያደርግ ምንም አይነት ምክንያት ባይኖርም፣ እንደ አሰቃቂ ተሞክሮ ወይም ስቃይ ያሉ ጎጂ የቀድሞ የህይወት ተሞክሮዎች፣ እየተከናወኑ ያሉ ሌሎች የህክምና ተዛማጅ ተሞክሮዎች፣ ዘረመል፣ የኬሚካል አለመመጣጠን፣ ወይም እጽን ያላግባብ መጠቀም ያሉ በርካታ ነገሮች እንደ ምክንያት ሊያዙ ይችላሉ፣ ነገር ግን በእነዚህ ብቻ አይወሰኑም። የ2020ዎቹ የመጀመሪያ አመታት፣ በተለይም በአለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው ወረርሽኝ፣ በአካባቢያዊ አደጋዎች፣ በማህበራዊ አለመረጋጋት፣ በወታደራዊ ግጭቶች፣ በዋጋ ግሽበት፣ እና በምግብ እጥረት ለአዕምሮ ህመሞች ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳበረከቱ ምንም ጥርጥር የለውም። በእውነቱ፣ የአለም ጤና ድርጅት፣ በማርች 2022፣ የ COVID-19 ወረርሽኝ በአለም አቀፍ ደረጃ በድብርት እና በጭንቀት ላይ 25 ፐርሰንት ጭማሪ እንዲኖር ማድረጉን ዘግቧል።

አሃዛዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በ2022  ከግማሽ በታች የሚሆኑ አሜሪካዊያን አዋቂዎች ህክምና አግኝተዋል። ከአዋቂዎች መካከል፣ ወንዶች (37.4 ፐርሰንት)፤ ሂስፓኒክ ያልሆነ እስያዊ (20.8 ፐርሰንት)፤ ሂስፓኒክ ያልሆነ ጥቁር ወይም አፍሪካዊ አሜሪካዊ (37.1 ፐርሰንት)፤ እና ሂስፓኒክ ወይም የላቲኖ ሰዎች (35.1 ፐርሰንት) ዝቅተኛ የሆነ አመታዊ የህክምና መጠን አላቸው።

ከአዕምሮ ጤና ጋር ምንም አይነት ችግር ቢያጋጥምዎትም እንኳን፣ ብቻዎትን እንዳልሆኑ፣ እና በ ዲሲ የሰብዐዊ መብቶች ህግ እና የአሜሪካ የአካል ጉዳተኞች ህግ ስር ከመድልዎ የተጠበቁ መሆንዎን እንዲያውቁ እንፈልጋለን። በ ዲሲ የሰብዐዊ መብቶች ህግ ስር፣ በስራ፣ በመኖሪያ ቤት፣ በትምህርት ተቋማት፣ በህዝብ መጠለያ፣ እና በመንግስት አገልግሎቶች ውስጥ የአዕምሮ ጤና እክል መድልዎ ጥበቃ አለ። እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው የአካል ጉዳት መድልዎ ከደረሰብዎ፣ ከክፍያ ነጻ እዚህ በOHR ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ። እንዲሁም፣ የአዕምሮ ጤና ችግሮች ሊሆኑ የሚችሉ የዘረመል ስሮች ሊኖራቸው ስለሚችል፣ የዘረመል መረጃ መድልዎ በ ዲሲ የተከለከለ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። በዚህ ወር የዜና መጽሄት ውስጥ የዘረመል መረጃ የተጠበቀውን ባህሪ አጉልተን እያሳየን ያለነው ለዚህ ነው።

ምንም እንኳን ከዚህ በላይ የአዕምሮ ጤና እና የአደንዛዥ እጽ መርጃዎችን በ ዲሲ በባህሪ ጤና መምሪያ እና በናሽናል ካፒታል ኤሪያ ዩናይትድ ዌይ በኩል ብንሰጥም፣ በእርስዎ ማህበረሰቦች ውስጥ የሚገኙትን ሌሎች የመርጃ አይነቶችንም አጉልተን ማሳየት እንፈልጋለን።

ከቤት ውጪ ስለመሆን፣ ስለ ፓርኮች፣ እና በእነዚያ ቦታዎች ስለሚደረጉ የመዝናኛ እንቅስቃሴዎች ስናስብ፣ አዕምሯዊ እና አካላዊ ጤንነታችንን ለማሻሻል ያላቸውን ችሎታ በብዛት አናስብም። በ Frontiers in Psychology ውስጥ የተደረገ የ2019 ጥናት ከ20-30 ደቂቃዎች ውጪ ማሳለፍ የጭንቀት እና የኮርቲሶል መጠንን መቀነሱን እንደተረጋገጠ አመልክቷል። ቀጥተኛ የጸሃይ ብርሃን እና ንጹህ አየር ሴሮቶኒንን ይጨምራል፣ ኢንዶርፊንን ያስወጣል፣ ቫይታሚን ዲ ይጨምራል፣ እና በአንዳንድ ጥናቶች የካርዲዮቫስኩላር በሽታዎችን፣ እብጠትን፣ እና የስኳር በሽታን የመከላከል አቅምን ይሰጣል። ከቤት ውጪ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ድብርት እና ጭንቀትን በመዋጋት ውጤታማ መሆኑ ተረጋግጧል።

ከ1985 ጀምሮ፣ ብሄራዊ የመዝናኛ እና ፓርክ ማህበር (NRPA) በፓርኮች እና በመዝናኛዎች ጠንካራ፣ ጤናማ፣ እና በሽታን የሚቋቋሙ ማህበረሰቦችን መገንባትን ለማበረታታት የፓርክ እና የመዝናኛ ወርን በጁላይ ወር አክብሯል። የዚህ አመት መልዕክት ለፓርኮች እና ለመዝናኛ ቦታዎች ተነስተናል" የሚል ነው። እንዲሁም መልዕክቱ ማህበረሰባቸውን በፍትሃዊነት፣ በአየር ንብረት-ዝግጁነት፣ እና በአጠቃላይ ጤና እና ደህንነት አገልግሎትን ለሚደግፉ ፓርኮች እና የመዝናኛ ባለሙያዎች እውቅና ይሰጣል። በ ዲሲ ውስጥ፣ የፓርኮቻችን እና የመዝናኛዎቻችን መምሪያ ለእርስዎ ደስታ የጁላይ 12 “በፓርኩ ውስጥ ይጫወቱ”ን፣ የጁላይ 13 የቤተሰብ መዝናኛ ምሽትን፣ የጁላይ 20 የአረጋውያን የቀለም ዝግጅት እና ሌሎችንም ጨምሮ በርካታ የቤት ውጪ እንቅስቃሴዎች አሉት። ስለ ዝግጅቶቹ እዚህ የበለጠ ማወቅ ይችላሉ።

ሚስተር ሮጀርስ/Mr. Rogers አባባል፣ ይህን እናስታውስ፣ “ሁላችንም፣ በአንድ ወቅት ወይም በሌላ፣ እርዳታ እንፈልጋለን። እርዳታ እየሰጠን ወይም እየተቀበልን ብንሆንም፣ እያንዳንዳችን ወደዚህ አለም ይዘንው የምንመጣው ጠቃሚ ነገር አለን። እንደ ጎረቤታሞች ከሚያገናኙን ነገሮች አንዱ ይህ ነው--በራሳችን መንገድ፣ እያንዳንዳችን ሰጪ እና ተቀባይ ነን።

 

 

ከአክብሮት ጋር