Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

ጃንዋሪ 2024 (Amharic)

Thursday, January 18, 2024

ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እና ጓደኞች፦

 ሰብዐዊ መብቶች በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከበሩበትን እና ጥበቃ የሚያገኙበትን የአለም ስራችን አዳዲስ እና ያለማቋረጥ የሚቀጥሉ ተግዳሮቶችን በመጋፈጥ፣ እንዲያነሳሳዎት የያኔው ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየርን ዘላቂ ጽናትና ሌጋሲ እንዲያስቡ አበረታታዎታለሁ።

ከሃምሳ ስድስት አመታት በፊት፣ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ የዘር እና ኢኮኖሚያዊ ፍትህ እንዲሰፍን ለማድረግ ያደረገው ፍለጋ ያለጊዜው በመሞቱ ተቋርጦ ነበር። ሆኖም ግን ህልሙ በተወሰነ ጊዜ እና ቦታ አልተወሰነም። የለውጥ እና የፍትህ አነሳሽ እንድንሆን የእኛን የጋራ ጥረቶች የሚጠይቅ ቀጣይነት ያለው የለውጥ ጉዞ ነው።

በዚህ የጃንዋሪ ወር፣ / ማርቲን ሉተር ኪንግ  ህልም እና ከልባቸው ለፍትህ እና ፍትሃዊ ማህበረሰብ ደከመኝ ሳይሉ የታገሉ የሌሎች የብዙዎችን ህልም ለማሳካትለ እራሳችንን እንደገና ለማዘጋጀት ሌላ እድል አለን። ስራው ተስፋ አስቆራጭ ሊመስል ይችላል ይሁን እንጂ ዶ/ር ኪንግ እንደተናገሩት “አንድ ሰው አስተማማኝ ያልሆነ ወይም ፖለቲከኛ ወይም ታዋቂ የማይሆንበት ስራ ላይ ለመሆን የሚገደድበት ጊዜ ይመጣል፣ ነገር ግን [የግለሰቡ] ህሊና ትክክል እንደሆኑ [ለእነሱ] ስለሚነግራቸው [መያዝ አለባቸው]።” ይህንን ወር ምን ያህል ርቀን እንደመጣን ለማሳየት ብቻ ሳይሆን የሰብዐዊ መብቶችን ተጋድሎ ለማሳደግ ያለንን የግል ሚና በድጋሚ ለመፈተሽ ይህንን ወር እንደ ተጨማሪ እድል ይጠቀሙበት።

በማህበረሰብዎ ውስጥ እንዲሁም ትርጉም ባላቸው ውይይቶች ላይ እንዲሳተፉ አበረታታዎታለሁ።  የዲሲ ሰብ አዊ መብቶች ቢሮ/ኦኤች አርከሌሎች ጋር በሚገናኙነት ጊዜ አካታች ቋንቋ እንዲጠቀሙ የሚያግዝዎትን መሳሪያ አዘጋጅቷል። በተጨማሪ ስልጠናዎችን እንዲሁም “የመስሚያ ቤተሙከራዎችን” የምናዘጋጅ ሲሆን የሰብዐዊ መብቶች ቢሮ ከማህበረሰባችን ጋር ለጋራ ጥቅም መቆሙን እና በፍትህ እጦት ለተጎዱ ሰዎች ውጤታማ መፍትሄዎችን ማቅረቡን ለማረጋገጥ ከማህበረሰብ መሪዎች ጋር በየሶስት ወሩ ስብሰባዎችን አደርጋለሁ። እነዚህን ስልጠናዎች እና ዝግጅቶች በሚመለከት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ የእኛን ድረገጽ፣ ማህበራዊ ሚዲያ ((ፌስቡክ ፣ ኢንስታግራም (@dchumanrights)፣ እና ሊንክዲን ) በ[email protected] ይመልከቱ። በጋራ፣ የተለያዩ አመለካከቶች የሚስተናገዱበት ብቻ ሳይሆን የሚከበርበትን አካባቢ ማስፋፋት እንችላለን። ትርጉም ባላቸው ውይይቶች እና የጋራ እርምጃ፣ በዲስትሪክቱ ውስጥ እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ላሉ የሰብዐዊ እና የሲቪል መብቶች ውስብስብ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ያለንን አቅም ማጠናከር እንችላለን።

ኦኤች አር//OHR ስራ ስለደገፉ እንዲሁም ለፍትህ እና ለእኩልነት ስላለዎት ቁርጠኝነት እናመሰግናለን። የ/ ማርቲን ሉተር ኪንግ  መንፈስ ከፊታችን ባለው አመት እኛን በማነቃቃት እና በመምራት እንዲያገለግለን እንመኛለን።  እንዲሁም “ሰዎች ትክክለኛ በሆነ ነገር ላይ ሲሳተፉ እና ለዚያ ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኞች በሚሆኑበት ጊዜ ከስኬት ወደሗል የሚያደርግ ምንም አይነት ምክንያት እንደሌለ” ያስታውሱ።

ከሰላምታ ጋር

ኤች ኤን