Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የካቲት 2023 (Amharic)

Monday, February 13, 2023

ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች፣ እና ጓደኞች፦

መልካም የጥቁር ታሪክ ወር! በዚህ ወር ጥቁር አሜሪካውያን ጭቆናን ለመቃወም፣ በሁሉም መልኩ፣ እና ለፍትሃዊነት፣ ለፍትህ፣ እና ለሰላም ለመታገል ላደረጉት ታሪካዊ እና በመካሄድ ላይ ያሉ ትግሎች እውቅና እንሰጣለን። በባርነት የተገዙ ሰዎች ተግባራዊ ካደረጉት የትጥቅ እና የሃሳብ ተቃውሞ ጀምሮ 1950፣ 60ዎቹ፣ እና 1970ዎቹን የሚያስረዱ የመቀመጥ፣ የአድማ፣ እና ሰልፎችን እስከማካሄድ፣ በብሄራዊ መዝሙር ወቅት በዝምታ እስከ መንበርከክ ድረስ፣ ጥቁር አሜሪካውያን ህይወታቸውን ለማሳደግ እና ለመጠበቅ ብዙ መንገዶችን ይፈልጉ ነበር።

እንደአለመታደል ሆኖ፣ ትናንሽ እርምጃዎች ተላለፈው የነበረ ቢሆንም፣ የዘር መድሎ የተስፋፋ እና የስርዐት ችግር መሆኑ ቀጥሏል። በዲስትሪክቱ ውስጥ፣ የ1977 የሰብዐዊ መብት ህግ በስራ፣ በትምህርት ተቋማት፣ በመኖሪያ ቤቶች እና በህዝብ መኖሪያ ቤቶች እና በመንግስት አገልግሎቶች ዘርፎች ካሉ ከሁለቱም የዘር መድልዎ እና የግል ገጽታ መድልዎ (ጸጉርን ጨምሮ) ይከላከላል። ሆኖም፣ ጥቁር ሴቶች፣ በተለይም፣ ከግማሽ በላይ በሆኑ የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ በስራ ቦታ የተፈጥሮ ጸጉራቸውን ለማድረግ ፈታኝ ሁኔታዎች ያጋጥማቸዋል። ከ2019 ጀምሮ፣ የማህበረሰቡ መሪዎች፣ ህግ አውጪዎች፣ እና ድርጅቶች በጸጉር አሰራር እና በሸካራነት ላይ ብቻ ተመስርቶ በስራ ቦታ የሚደረግ መድልዎን የሚከለክል ህግ ለማስተዋወቅ እንቅስቃሴ ጀምረዋል። ይህ ህግ በተደጋጋሚ የCROWN ህግ ተብሎ ይጠራል፣ ይህም ለተፈጥሮ ህግ የተከበረ እና ክፍት አለም መፍጠር የሚለውን ያመለክታል። በምክር ቤት ውስጥ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ በካሊፎርኒያ፣ ኮሎራዶ፣ ኮኔክቲከት፣ ዴላዌር፣ ኢሊኖይስ፣ ሉዊዚያና፣ ሜይን፣ ማሳቹሴትስ፣ ሜሪላንድ፣ ነብራስካ፣ ኔቫዳ፣ ኒው ጀርሲ፣ ኒው ዮርክ፣ ኦሪገን፣ ቴነሲ፣ ቨርጂኒያ፣ ዋሽንግተን እና የአሜሪካ ቨርጂን ደሴቶችን ጨምሮ፣ በሃገር ደረጃ በአብዛኞቹ ክልሎች ህግ ወጥቷል። በዋሽንግተን ምክር ቤት ውስጥ የCROWN ህግ የወደፊት እጣ ፈንታ እርግጠኛ ባይሆንም፣ በዋሽንግተን፣ D.C. ከተማ፣ ለDC እሴቶቻችን ቁርጠኞች ነን እንዲሁም በጸጉር ላይ የተመሰረተ መድልዎ ስህተት መሆኑን እናም የሰብአዊ መብቶች ቢሮ በDC የሰብአዊ መብቶች ህግ መሰረት እነዚህን ቅሬታዎች እንደሚቀበል እርግጠኞች ሆነን እንቀጥላለን

አገራችን የተፈጥሮ ጸጉር የማድረግ መብትን በሚያክል ቀላል ነገር ላይ መስማማት ካልቻለች፣ አሁንም በትምህርት፣ በጤና እንክብካቤ፣ እና በወንጀል ፍትህ ስርዐት በመሳሰሉት ዘርፎች ውስጥ እውነተኛ ፍትህ እና እኩልነትን ለማስፈን ብዙ እንደሚቀረን እናውቃለን።

ስለዚህ፣ በዚህ ወር እና በየወሩ፣ በዲሞክራሲያዊ ማህበረሰብ ውስጥ የራስን እድል በራስ ለመወሰን ጥቁር አሜሪካውያን ስላደረጉት ታሪካዊ እና ቀጣይነት ያለው ትግል እንድትማሩ አበረታታችኋለሁ። የት እንደነበርን እና ወዴት እንደምንሄድ ለመወያየት፣ “በዲስትሪክት ውስጥ እና ከዚያም ባሻገር ያለ ያለፈው፣ የአሁን እና የወደፊት የጥቁር ተቃውሞ” በሚል በፌብሩዋሪ 23 የሚኖረውን የትውልዶች የፓናል ውይይት ላይ ከእኛ ጋር በመቀላቀል መጀመር ይችላሉ። ይህ ከከንቲባው የአፍሪካ አሜሪካውያን ጉዳዮች ቢሮ ጋር በመተባበር በMLK ቤተመጽሃፍት የሚካሄድ የተቀላቀለ ዝግጅት ነው። ለምናባዊ ዝግጅት እዚህ እና በአካል በመገኘት ለሚካሄደው ዝግጅት እዚህ መመዝገብ ይችላሉ። በመጨረሻም፣ የትኛውም ቦታ ቢሆኑ፣ ሁሉን አቀፍ የሆነ አካባቢን እንዲያሳድጉ በግንኙነቶችዎ እና በባህሪዎ ጠንቃቃ እንዲሆኑ እጋብዝዎታለው። OHR ባለፈው አመት በርካታ አካታች የቋንቋ መመሪያዎችን ለማዘጋጀት ጠንክሮ ሰርቷል፣ እና የመጀመሪያውን “Words Matter፦ በዘር እና በጎሳ ማንነት ዙሪያ አካታች ቋንቋ መመሪያ”፣ የተባለው መመሪያ በቅርቡ ይለቀቃል። እባክዎ ይህን ድንቅ የትምህርት መርጃ ይጠብቁ።

በአንድነት፣