Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

ጁን 2024 የ ዲሲ የሰባዊ መብቶች ቢሮ (የኦ-ኤችአር) መጽሄት- ውርሃዊ የዲሬክተር መልእክት  (Amharic)

Tuesday, June 18, 2024

ጁን 2024 ዲሲ የሰባዊ መብቶች ቢሮ (የኦ-ኤችአር) መጽሄት- ውርሃዊ የዲሬክተር መልእክት  

የተከበራችሁ ኗሪዎች፣ ጎረቤቶችና ጓዶች፡-

ጁንን ወር በምንቀበልበት ወቅት  ዋነኛ እሴቶቻችን ለሆኑት ሁለት በዓላት እውቅና ስንሰጥ ከፍተኛ ደስታና ኩራት ይሰማኛል፤ የፕራይድ  ወር (Pride Month) እና የስደተኞች የቅርስ ወር (Immigrant Heritage Month)። እነኚህ ሁለት በዓላት፤ ለማህበረሰባችን ቅርጽ የሰጠውን የካበተ ህብረ-ብሄራዊነታችንን ለማንጸባረቅ እንድንችልና ለእኩልነት፤ ለመከባበርና ካለአድልዎ ሁሉንም ለማካተት የምናደርገውን ትግል ቁርጠኛነት እንደገና እንድናረጋግጥ የተለየልዩ ዕድል ይሰጡናል።

የኩራት ወር (Pride Month) የኤል-ጂ-ቢ-ቲ-ኪው-አይ-ኤ+ (LGBTQIA+) ማህበረሰብን ታሪክ፣ ሰኬታማነት እና ቀጣይ ትግልን የሚያከብር ነው።  ይህ ወር፤ ራሳቸውን የመግለጽ መብታቸውን ለማስከበር ካለ እረፍት በቀጣይነት የታገሉትን ግለሰቦችንና አድልዎ የሌለበትን ማህበረሰብ ለመፍጠር የተካሄደውን ትግልና የተገኘውን ድል ያስታውሰናል። አድልዎን ለማስወገድ እንደሚታገል እንደ አንድ መንግስታዊ ተቋም ፤ የኤል-ጂ-ቢ-ቲ-ኪው-አይ-ኤ (LGBTQIA+) ማህበረሰብን የመደገፍና መብት የማስከበር እንዲሁም ሁሉም ሰው ካለአድልዎ በኩራት የሚኖርበትን ሁኔታ የመፍጠር ወሳኝ ሚና አለን።  ከዚህ ጋር በተያያዘም፤ ብዙዎችን የሚጠቅሙ አስፈላጊ መረጃዎችና ምንጮች ያሏቸው የኤል-ጂ-ቢ-ቲ-ኪው-አይ-ኤ (LGBTQIA+) የመረጃ አዲስ ፖርታል  LGBTQIA+ Resource Portal እና የዲሲ ምቹ የመጸዳጃ  ቤቶች (Safe Bathrooms DC) የሚል ጽሁፎችን አውጥቷል።

በዚህ በጁን ወር ሌላው የሚከበረው በዓል ደግሞ የስደተኞች ቅርስ ወር (Immigrant Heritage Month) በመባል የሚታወቀው ነው። በዚህ የስደተኞች ቅርስ ወር (Immigrant Heritage Month) በመባል በሚታወቀው ወር ስደተኞች ወደ አገራችን ይዘውት የመጡትን ባህላቸውን፣ ልምዶቻቸውን እና ታሪካቸውን እውቅና የምንሰጥበት የምናከብርበት ወር ነው። በቅርቡ የህዝብ ቆጠራ ጽህፈት ቤት ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምብያ ካሉት ተቀማጮች ውስጥ 14 ከመቶ በሌሎች አገሮች የተወለዱ ስደተኞች ናቸው። ይህም ስደተኞች በማህበረሰባችን ውስጥ ምን ያህል ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ያንጸባርቃል። የከተማችን ልዩና ጠንካራነት የተገነባውና አኇኇራችንን የካበት እንዲሆን ያደረገው የስደተኞች ችግርን የመቋቋም ችሎታ ነው። ዲሲ የሰባዊ መብቶች ቢሮ (የኦ-ኤችአር) ስደተኞች በየቀኑ ስለሚያጋጥሟቸው ችግሮች ለምሳሌ አንገብጋቢ የሆኑ መረጃዎችንና ምንጮችን ለማግኘት እክል የሚፈጥርባቸው  የቋንቋ ችግር (language barriers) ስለመሳሰሉት  በሰፊው እንነጋገራለን። በዚህ ወር  እርስበርስ መማማርና ሃሳብ መለዋወጥምን ያህል ጠቀሜታ እያስታወስን፤ እያንዳንዱ የማህበረሰባችን አባል ከሌሎች ጋር በእኩልነት ወደፊት እንዲራመድ የሚያደርግ ፍትሃዊ ዕድል እንዲያገኝ ጥረታችንን እንቀጥል።  

ልዩነቶቻንን የሚያከብርና ሁሉንም ሰው በእኩልነት የሚያካትት ማህበረሰብ በቁርጠኛነት እንፈጥራለን ስንል በቃላት ብች የሚገለጽ ብቻ ሳይሆን የምንወስዳቸው እርምጃዎችንና የምናወጣቸው ፖሊሲዎችን የሚያራምድ መርሗችን ነው።  በዚህ በጁን ወር እያንዳንዱ ሰው ለፕራይድ ወር እና  ለስደተኞች የቅርስ ወር ተብለው በተዘጋጁትና በሚካሄዱት በዲስትሪክቱ የተለያዩ ክስተቶችና እንቅስቃሴዎች ላይ እንድትሳተፉ ጥሪዬን አቀርባለሁ። ለሁላችንም ለውጥ ሊያመጡ በሚችሉ  ወይይቶች ላይ ተሳተፉ፣ ራሳችሁንና ሌሎችን ለማስተማር ጥረት አድርጉ፣ ለማህበረሰባችን ጥንካሬ የሚሰጠውን የካበት ህብረ-ብሄራዊነታችንን አናክብር።

በአብሮነት

ኬነት ሳንደርስ (Kenneth Saunders)

ዳይሬክተር