Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

አፕሪል 2024 የኦኤችአር ወርሃዊ ኒውስሌተር የዳይሬክተሯ/ሩ መልዕክት (Amharic)

Tuesday, April 23, 2024

ውድ ነዋሪዎች፣ጎረቤቶችና ወዳጆች

 

እኔ ኬኔዝ ሶንደርስ ስሆን ቀደም ሲል በከንቲባ አንቶኒ ዊሊያምስ የስራ ዘመን የኦኤች አር ዳይሬክተር በመሆን ሳገለግል ከነበረበት ጊዜ አንስቶ አብዛኞቻችሁ ታውቁኛላችሁ፡፡ አሁንም በከፍተኛ ቁርጠኝነት የኦኤች አር ጊዜያዊ ዳይሬክተር በመሆን ተመልሻለሁ፡፡ለፍትሃዊ እና እኩል መልካም እድሎች መስፈን ያለኝ ቁርጠኝነት የማይናወጥ ሲሆን በድጋሚ ማህበረሰባችንን ለማገልገል ዝግጁ ነኝ ፡፡

አፕሪል የተለያዩ ክንውኖችንን እና ድርጊቶችን የያዘ ወር ነው፣ በመጀመሪያ ዶክተር ማርቲን ሉትር ኪንግ እንደተገደሉ የወጣውን የ1968ቱ ፍትሃዊ የቤቶች ህግ በማስታወስ እና በተለያዩ ዘርን፣ የቆዳ ቀለምን፣ ኃይማኖትን፣ ጾታን፣ የአካል ጉዳትን እና ቤተሰባዊ ሁኔታን በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ በመመስረት የሚደረጉ የቤቶች አቅርቦት መድሎዎችን ለመከላከል በ1964 በወጣው የሲቪል መብቶች ህግ ላይ በመመስረት ፍትሃዊ የቤቶች አቅርቦት ወርን እናከብራለን፡፡ በፍትሃዊ የቤቶች ግብዓት ፖርታላችን ነዋሪዎችን አቅም ለመገንባት እና ለማብቃት የቤቶች አቅርቦት መብት ግብዓቶችን ያጠናቀርን ሲሆን፤ መብትዎን በተመለከተ በጥልቀት ለመፈተሽ እንዲችሉ ከቤቶች አቅርቦት አጋሮች ጋር ወደ ቨርችዋል ክብ ጠረጴዛ እንዲመጡ እንጋብዝዎታለን፡፡

 

ከዚህ በተጨማሪ ይህ ወር በቋንቋ ተደራሽነት ግንዛቤ ወር ላይ ግንዛቤን ያስጨብጣል፣ ሁለት አስርት ዓመታት ያስቆጠረውን እና ቋንቋ በፍጹም የሲቪል ህይወት ወይም ወሳኝ መረጃን በተመለከተ እንቅፋት ለመሆን እንደማይችል የሚያረጋግጠውንና ጉልህ ህግ የሆነውን የዲሲ የቋንቋ ተደራሽነት ህግ እናከብራለን፡፡ በከተማችን ውስጥ ይህንን ዓላማ ከሚያራምዱ የቋንቋ ተደራሽነት መርሆች ጋር ሊገናኙ ወደ ሚችሉበት ወደ እዚህ ዝግጅት በመምጣት ከእኛ ጋር ይቀላቀሉ፡፡

በመጨረሻም አፕሪል ተመላሽ ዜጎች በድጋሚ ለመቀላቀል በሚያደርጉት ስኬታማ ጉዞ የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች በተመለከተ ግንዛቤ የሚያስጨብጠውን የዳግም እድል ወር ነው፡፡ በተመላሽ ዜጎች ጉዳዮች፣ በዲሲ ተመልሶ የመግባት ህግ ኔትወርክ (አርኤኤን) እና በተጎጂዎች አገልግሎትና የፍትህ ቢሮ ላይ በከንቲባዋ ጽ/ቤት በሚመሩ ኢኒሼቲቮች አማካኝነት ከተማችን ከተመላሽ ዜጎች ጋር አብራ ትቆማለች፡፡ በድጋሚ ተመልሶ የመግባትን አስፈላጊነት እና እና ደህንነቱ የተጠበቀ ፣ እንዲሁም ስኬታማ ዳግም መቀላቀልንን በመደገፍ ረገድ ያላቸውን ሚና እውቅና ለመስጠት ኦኤችአር ነዋሪዎችን፣ የማህበረሰብ አካላትን እና ኤጀንሲዎችን እንዴት እንደሚደግፍ ለማወቅ የማህበራዊ ትስስር ገጻችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ፡፡

እነዚህ አሰፈላጊ ክንውኖችን የምናከብር ከመሆኑ አንጻር ከፊትለፊታችን የሚጠብቀንን ስራ ለይተን ማወቅ ያለብን ከመሆኑ ጎን ለጎን ለተገኙ ስኬቶችም እውቅና እንስጥ፣ በጋራ በምናደርገው ጥረት ጉልህ የሆኑ ኢፍትሃዊ ልዩነቶችን ለማስወገድ እና ሁሉም ሰው መብቱን ተገንዝቦ እንደሚጠቀም ለማረጋገጥ ለእኩልነትና ለፍትህ የምናደርገውን ጥረት እንቀጥላለን፡፡

 

በአብሮነት

ኬኔዝ ሶንደርስ