Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ የከተማአቀፍ በቋንቋ መረዳት ዘመቻን ይጀምራል

Tuesday, August 28, 2012
“እኔ እናገራለሁ” ካርዶች እና የህዝብ ግልጋሎት መግለጫዎች በስድስት ቋንቋዎች እንግሊዝኛ የማይናገሩ ሰዎችን ይረዳሉ

 

(ዋሽንግተን, ..) – የዲሲ የሰብአዊ መብት ቢሮ ዘርፍ የሆነው የዲሲ በቋንቋ መረዳት ፕሮግራም  ውስን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ለሚናገሩ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ መናገር ለማይችሉ የከተማው ነዋሪዎች መንግስት የሚሰጠውን አገልግሎቶች መጠቀም እንዲችሉ የጀመረውን ዘመቻ ዛሬ ያስተዋውቃል። የህዝብ አገልግሎት ማስታወቂያው አማርኛ፣ ቻይንኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ኮሪያኛ፣ ስፓኒሽኛ፣ ወይም ቬትናምኛ ለሚናገሩ የህበረተሰቡ አባላት በተወለዱበት ቋንቋ የትርጉም አገልግሎት በዲስትሪክቱ ኤጀንሲዎች የመሰጠት ግዴታ እንደአለባቸው ለማስታወቅ ነው። ከላይ የተገለጸውን ሂደት ለማቃለል የዲስትሪክቱ ሠራተኞች አስተርጓሚ ለህብረተሰቡ አካል በራሳቸው ቋንቋ እንዲያቀርቡ በማዘዝ፤ የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ በቅርቡ በቦርሳ ውስጥ የሚገቡ ካርዶችን አስራጭቷል።

“የቋንቋ መረዳት ፕሮግራማችን ከህብረተሰቡ አጋሮች ጋር በሚሰራው ስራ እንደገለጸው እንግሊዝኛ መናገር ለማይችሉ ወይም ውስን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ላላቸው ሰዎች አስፈላጊ የሆኑ መንግስት የሚሰጣቸውን የተለያዩ አገልግሎቶች ለመጠቀም አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል” ብለው የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ ዳይሬክተር ጉስታቮ ቬላሳኤዝ ተናግረዋል። የ”እኔ እናገራለሁ” ካርዶች በዲስትሪክቱ አገልግሎቶች እና በባለጉዳዩ መሀከል ያለውን ግንኙነት ለማቃለል የታሰቡ ሲሆኑ፤ የአንግሊዝኛ ቋንቋን በብቃት ለማይናገሩ የአስተርጓሚው አካላት ወይንም የተተረጎሙ ጽሁፎች በሌሉበት ጊዜ የዲሲ የሰብአዊ መብቶች ቢሮን እንዲጠይቁ ያበረታታል።

“እኔ እናገራለሁ” ካርዶችን ለማስተዋወቅ፣ የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ የእያንዳንዱ የስድስቱን ቋንቋዎች ተናጋሪ የህብረተስብ አካላት በቴሌቭዥን ያቀርባል። ተሳታፊዎቹ የእንግሊዝኛ ቋንቋ በደንብ ያለመናገር የሚያመጣውን ችግሮች እና የዲሲ በቋንቋ አገልግሎት ማግኘት ህግ ምን ያህል የመንግስት አገልግሎቶችን በበለጠ ለማግኘት እንደሚያስችል በሀገራቸው ቋንቋ ይገልጻሉ።  በተጨማሪም ማስታወቂያዎቹ ተመልካቾች “እኔ እናገራለሁ” ካርዶችን ከሰብዓዊ መብቶች ቢሮ  (በሁሉም ቋንቋዎች), ከአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ (በአማርኛ እና በፈረንሳይኛ), ከእስያ የፓስፊክ ደሴት ጉዳይ ቢሮ (በቻይና፣ ኮሪያ እና ቬትናም ቋንቋዎች) ወይም ከስፓኒሾች ጉዳይ ቢሮ  ወይም ከሰብዓዊ መብቶች ቢሮ  ድህረ-ገጽ እንዲያገኙ ያበረታታሉ።

ሞኒካ ፓላሲዮ፣ የቋንቋ መረዳት ፕሮግራም ዲሬክተር “ይህ ዘመቻ የዲስትሪክቱን አገልግሎቶች ማግኝት ለሚገባቸው በሺ የሚቆጠሩ የዲሲ ተቀማጮች ይደርሳል” አሉ። “ሁለት የተለያዩ ሰዎች በቋንቋ ምክንያት መግባባት ሲያቅታቸው የሚከሰተውን ችግር አዲሶቹ የ‘እኔ እናገራለሁ’ ካርዶች ለመቀነስ እንደሚረዱ ሙሉ ተስፋ አለኝ ። ማንኛውም የተወሰነ እንግሊዝኛ መናገር የሚችል/ትችል ወይንም ምንም  እንግሊዝኛ መናገር የማይችል/ትችል ካርዶቹን በቦርሳው/ዋ ውስጥ ማስቀመጥ ይችላል/ትችላለች”።

“እኔ እናገራለሁ” ካርዶች እና አብረው የሚሄዱ የተሌቭዥን ፕሮግራሞች በሰብዓዊ መብቶች ቢሮ  ድህረ-ገጽ ohr.dc.gov/ispeak ላይ ይገኛሉ። የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ  አንግሊዘኛ ቋንቋን ለማይችሉ ወይም በብቃት ለማይናገሩ ነዋሪዎች የሚያደርገው እርዳታ በዚህ በልግ የ“እኔ እናገራለሁ” ካርዶችን በሚታተሙ ማስታወቂያዎች የብሄር ጋዜጣዎች ላይ በማውጣት ይቀጥላል። 

 

# # #

 

ስለ የቋንቋ መረዳት ፕሮግራም

የቋንቋ መረዳት ፕሮግራም የዲስትሪክት ኤጀንሲውን በ2004ቱ በቋንቋ መረዳት ደንብ መስማማት ይቆጣጠራል፣ እንዲሁም ይደግፋል። የቋንቋ መረዳት አባላት ለሁሉም የዲስትሪክት ኤጀንሲዎች ስልጠና እና ቴክኒካል እርዳታ ይስጣሉ፣ እንዲሁም ክህዝቡ ጋር ብዙ ግንኙነት አላቸው ከተባሉ ከ34 ዲስትሪክት ኤጀንሲዎች ጋር በቅርብ አብረው ይስራሉ። የቋንቋ መረዳት ፕሮግራም በሰብዓዊ መብቶች ቢሮ ሥር ይገኛል። ለተጨማሪ መረጃ የቋንቋ መረዳት ዳይሬክተር ሞኒካ ፓሊሲዮን በ(202) 727-3942 በመደወል ወይም [email protected]  ኢሜል በመላክ መጠየቅ ይችላሉ።

 

ስለ የኮሎምብያ ዲስትሪክት የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ

የኮሎምብያ ዲስትሪክት የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ የተመሰረተው ማግለልን ለማጥፋት፣ እኩል እድልን ለመጨመር እና በኮሎምብያ ዲስትሪክት የሚኖሩ ሰዎችን ወይንም የሚጎበኙትን ሰብዓዊ መብታቸውን ለመጠበቅ ነው። ኤጀንሲው የከተማ እና የፌደራል ሰብዓዊ መብቶች ህጎችን፣ የዲሲ ሰብዓዊ መብቶችን ደንብ፣ የህግ ሂደትን ተገልለናል ብለው ለሚያምኑ በማቅረብ ያስፈጽማል። በተጨማሪም የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ በዲስትሪክቱ ውስጥ ያሉ ሰባዓዊ መብቶችን በዳይሬክተሯ ጥያቄዎች በኩል ያስፈጽማል፣ ይህም የማግለል ልምዶች እና ህግጋት ሊሆኑ የሚችሉትን ለማወቅ እና ለመመርመር ያስችለዋል።