Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ohr

Office of Human Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የአፕሪል ወር 2023 የዳይሬክተር ማስታወሻ (Amharic)

Tuesday, April 25, 2023

ውድ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች እና ወዳጆች:-

በውርሃ አፕሪል፣ ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት፣ የቋንቋ ተደራሽነት፣ የልጆች ጤናን እና ዳግም ሚከሰቱ መልካም አጋሚዎችን ጨምሮ በማህረተሰባችን ውስጥ ብዙ የሚደነቁ እርምጃዎችን በማከናወን እያከበርን ነው።   የዚህ ወር መልዕክቴ የሚያተኩረው በፍትሃዊ የመኖሪያ ቤቶች ላይ ሲሆን፣ የቋንቋ ተደራሽነትን 19ኛ አመት በአሉ የሚከበርበትን መንገዶችን በተመለከተ ከቋንቋ ተደራሽነት ዳይሬክተራችን የተሰጠውን ማስታወሻ እንዲመለከቱ  አበረታታለሁ።

ከ55 አመታት በፊት፣ ፕሬዝዳንት ሊንደን ጆንሰን ዘርን፣ ቀለምን፣ ብሄርን፣ ሃይማኖትን፣ ጾታን፣ አካል ጉዳተኝነትን እና የዝምድና ትስስርን መሰረት ያደረገ የመኖሪያ ቤት ሽያጭ፣ ኪራይ እና ፋይናንስን በተመለከተ መድልዎ የሚከለክለውን፣ ፍትሃዊ መኖሪያ ቤቶች ህግ (FHA) ፈርመው ነበር። በ2021፣ የፕሬዘዳንት ባይደን የስራ አስፈጻሚ ትዕዛዝ/ኤግዚኩቲቨ ኦርደር/ የጾታ ዝንባሌን የጾታ ማንነትን ፣ የጾታ አገላለጽን ለማካተት እና  የጾታ ጥበቃን ለመተርጎም HUD አስፈልጎታል።

የእነዚህን ልዩነቶች ምንነት ማወቅ አስፈላጊ ነው ምክንያቱም በአካባቢያዊም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ፣ በነጭ ነዋሪዎች እና በጥቁር ነዋሪዎች መካከል እየጨመረ የመጣው የዘር ሃብት ልዩነት የሚያሳይ ሲሆን የእድልን ተደራሽነት፣ የድጋፍ ዘዴን እና ንብረትን ያንጸባርቃል። ይህ ማለት ጥቁር ሰዎች ልክ እንደ ነጭ አሜሪካውያን በተመሳሳይ መጠን ሃብት የመገንባት አቅም የላቸውም ማለት ነው። ለምሳሌ፣ የU.S. የህዝብ ቆጠራ ውሂብ እንደሚያሳየው በቤተሰብ የቤተሰብ ጥሪት/ሃብት ውስጥ ከነጭ ቤተሰቦች $139,300 ጋር ሲነጻጸር አማካይ የጥቁሮች የቤተሰብ የሃብት ስብጥር በግምት $12,780 ድርሻ አለው። የገቢ አለመመጣጠን ሲያድግ የቤት አልባነት እና የጥቁሮች የቤት ባለቤት በመሆን የትውልድ ሃብት መፍጠር አቅም አለመመጣጠንንም ጨምሯል።

በ1977 የወጣው፣ የዲሲ የሰብዐዊ መብቶች ህግ፣ የገቢ ምንጭን ጨምሮ፣ ከፍትሃዊ መኖሪያ ቤት ህግ የበለጠ ብዙ ጥበቃ የሚደረግላቸውን  ዘርፎች ላይ ያተኩራል።  ይህ ጥበቃ የመኖሪያ ቤት አቅራቢዎች በገቢ ላይ በተመሰረቱ የቤት ድጎማዎች ላይ በሚደገፉ አመልካቾች አድልዎ እንዳይፈጽሙ ይከለክላል።  በ2022፣ አንድ አዲስ ህግ ( ኢቪክሽን ሪኮርድ ሲሊንግ ኦቶሪቲ ኤንድ ፌይርነስ ኢን ሬንቲንግ አሜንድመንት አክት ኦፍ 2022 (ERSFRA) በመባል ይታወቃል) ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን፣ በፌደራል FHA ከተሸፈነው ባሻገር በመኖሪያ ቤቶች ውስጥ ጥበቃዎችን አካቷል። ለምሳሌ፣ በዚህ አዲስ ማስፋፊያ መሰረት በቀድሞ የብድር ጉዳዮች ወይም በቀድሞ የኪራይ ክፍያ ታሪክ ላይ በመመስረት ማመልከቻዎችን ውድቅ ማድረግ፣ እነዚህ ጉዳዮች የተነሱት ግለሰቡ የመኖሪያ ቤት ድጎማ ከመቀበሉ በፊት ከሆነ የአድልዎ አይነት ሊሆን ይችላል።  በተመሳሳይ፣ የመኖሪያ ቤት ድጎማዎችን ለሚጠቀሙ ግለሰቦች፣ ተለየ የገቢ ወይም የብድር ውጤትን የሚያስገድድ የፌደራል ህግ መስፈርት ከሌለ በስተቀር በገቢ ደረጃ እና በክሬዲት ውጤቶች ላይ የተመሰረተ ማስተባበያ አድልዎ አይነት ሊሆን ይችላል። በተጨማሪም፣ የመኖሪያ ቤት አቅራቢው በገቢ ላይ የተመሰረተ የመኖሪያ ቤት ድጎማዎች የማይጠቀሙ ሰዎችን የማያስከፍለው ማንኛውንም ክፍያዎች፣ ተቀማጭ ገንዘብ፣ ወይም ተጨማሪ ኪራይ መኖሪያ ቤት አቅራቢዎች ካስከፈሉ ህጉ መድልዎ መፈጸሙን እንደ እውነት እንደሚቆጠር በግልጽ አክሏል። የዲሲ ሰባዊ መብት ቢሮ/OHR/ ማስፈጸሚያ መመሪያን ቁጥር 23-03 በመመልከት ወይም በአፕሪል 27 በ6 pm (ከዚህ በታች ያለው መረጃ) ላይ በሚካሄደው የፍትሃዊ መኖሪያ ቤት ወርሃዊ የማድመጫ ላቦራቶሪ ላይ በመገኘት የገቢ ምንጭ መድልዎ በ ESAFRA እንዴት ተሻሽሎ እንደቀረበ የበለጠ ማወቅ ይችላሉ።

በመኖሪያ ቤት ውስጥ አድልዎ ከተፈጸመብዎት  የዲሲ ሰባዊ መብት ቢሮ/OHR/  ሊረዳዎ ዝግጁ ነው። ቅሬታ እንዴት ማስገባት እንዳለብዎ በተመለከተበለጠ መረጃ   እዚህ ማግኘት ይችላሉ